ፈልግ

ኢየሱስ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ በወላጆቹ የሙሴን ሥርዓት ለመፈጸም ወላጆቹ ሊያስግርዙት ወደ ቤተመቅደስ ወሰዱት፡፡ ኢየሱስ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ በወላጆቹ የሙሴን ሥርዓት ለመፈጸም ወላጆቹ ሊያስግርዙት ወደ ቤተመቅደስ ወሰዱት፡፡   (Copyright by MaxPixel)

ኢየሱስ በተወለደ በስምንተኛው ቀን ተገረዘ

ኢየሱስ ከተወለደ ከስምንት ቀን በኋላ በወላጆቹ የሙሴን ሥርዓት ለመፈጸም በወላጆቹ ተሸኝቶ ሊገረዝ ወደ ቤተመቅደስ ሄደ፡፡ ከተወለደ ስምንት ቀን ካለፈው በኋላ ስሙ ኢየሱስ ተስሎ ተጠራ፡፡ ይህ መልአክ ገና ሳይጸነስ የሰጠውና ያወጣለት ስም ነው (ሉቃ. 2፣21) ፡፡ እግዚአብሔር ዕብራውያን ሕዝቡ እንደመሆናቸውና ከሌሎች የዓለም ሕዝቦች እንዲለያቸው ብሎ መልእክት ግርዛትን ሰጣቸው፡፡ እንግዲህ በግርዛት ሕዝቡ መሆናቸውን አሳወቅቸው፡፡ በመጽሐፈ ሌዋውያን በአገልጋዩ በሙሴ በኩል እንደተጻፈው “ሕፃን በስምንተኛው ቀን እንዲገረዝ ይሁን” (ሉቃ. 12፣3) ሲል አዘዛቸው፡፡ ከዚህ ቀጥሎ ደግሞ “እንግዲህ የልባችሁን እድፍ ግረዙ ልባችሁን አታጠንክሩ$ (ዘዳ. 10፣11) አላቸው፡፡ እግዚብሔር አምላክ ልብህን ግረዘው እንዲሁም የልብህን ሁሉ ይህ ደግሞ በልብህ ሁሉ በነፍስህ እግዚአብሔር አምላክህን እንድታፈቅረው አንተም ብዙ ዘመን እንድትኖር ነው” (ዘዳ. 30፣6) እያለ ተናገራቸው፡፡ እንዲሁም ሕዝቅኤል “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል ወንድ የሆነ ልጅ ሥጋውን ያልተገረዘ ወደ ቤተመቅደስ አይግባ፤ እንዲሁም በእስራኤል ልጆች መሐል ያለ የባዕድ ሀገር ተወላጅ” (ሕዝ. 45፣9) ይላል፡፡

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ግርዛት ለእስራኤላውያን ከትልልቅ ሥርዓቶች አንዱ ነበር፡፡ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶሰ ምንም እንኳ ግርዛት የማያስፈልገው ቢሆንም ሕግን ለመፈጸመ እንደ ሙሴ ሕግ የግርዛት ሥርዓትን እንደ ማንኛውም ተራ ሕፃን ፈጸመ፡፡ “ሰው ሆነ ያለኃጢአት የሰውን ሥራ ሁሉ ፈጸመ” (ቅዳ. ዘአግ ጐሥዓ) ጊዜው ሲደርስ እግዚአብሔር ከሴት የሚወለድ በሕግም የሚሄድ ልጁን ላከው፡፡ የኢየሱስ ግርዛት ሁለት ነገሮችን ያስተምሩናል፡፡

1ኛ/ ሕግን ማክበር እንደሚገባን

2ኛ/ መንፈሳዊ ግርዛት ማለት ከኃጢአት መንጻት እንደሚገባን

ሀ/ ሕግን ማክበር ኢየሱስ የብሉይ ኪዳንን ሕግ ለመሻር በደንብ ይችል ነበር ግን አልፈለገም፤ አከበረው እንጂ አልናቀውም፤ ከዚህ የቃል ኪዳን ሕግ አልወጣም፡፡ የማይመለከተኝ ቢሆንም ለአዳም ልጆች ምሳሌና ትምህርት እንዲሆን ልፈጽመው አለና ፈጸመ፡፡ እኔ ኦሪትንና ነቢያትን ለመፈጸም እንጂ ለመሻር ወይም ለማፍረስ አልመጣሁም” (ማቴ. 5፣17) ይል ነበር፡፡ እርሱ አምላክ ከሕግ በላይም ሆኖ እያለ ሁሉን ሕግ ለመፈጸሙ ለእኛ የሕግን አክብሮት ምሳሌ ይሰጠናል፡፡ እኛ ብዙ ጊዜ ደጋግመን በቀላሉ ሕግን እንጥሳለን እናፈርሳለን፡፡ ይህ ሕግ ይህ ሥርዓት የድሮ በመሆኑ ጊዜ ያለፈበት ነው፣ ጥሩ አይደለም፣ አይጠቅምም የማይረባ ስለሆነ ብናፈርሰውና ብንጥሰው ምንም ጉዳት አያመጣም፣ የሚያሰጋ አይደለም በሚል ደካማ መንፈስ ንቀን እንረግጠዋለን፡፡ ባለን አቅም ተግባራዊ እንዳናደርገው ምክንያት በመፍጠር እንሸሻለን፡፡ በደኀንነትና በፍጽምና ጐዳና ወደፊት ልንገሰግስ አደገኛ የሆነውን ስንፍና እንዳናስገባ ብንፈልግ ኢየሱስን አተኩረን አንመልከት እንከተለውም፡፡

ለ/ መንፈሳዊ ግርዛት የሥጋ ግርዘትን መንፈሳዊነት ማመልከት አለበት፡፡ እግዚአብሔር ዕብራውያን ከሥጋ ግርዘት ጋር የመንፈስ ግርዘት እንደሚያስፈልግ ያስጠነቅቃቸው ነበር፡፡ “እንግዲህ የልባችሁን እድፍ አስወግዱ ግረዙ፣ እግዚአብሔር ልብህንና የልብህን ዘር ይግረዝ” (ሮሜ. 9፣29) የሚል አደራ እናገኛለን፡፡ እግዚብሔር የሕዝቡን ልብ ከኃጢአት ሊገርዝ ሊጠራ ይፈልግ ነበር፤ የልብ ግርዘት የመንፈስ ዕብደትን ማስወገድ ነው፡፡

የመንፈስ ግርዘት በክርስቶስ ተገርዛችህኋል፡፡ “የሕግ ግርዘት በክርስቶስ እንጂ በሰው የተደነገገ አይደለም” ይላል ቅዱስ ጳውሎስ፡፡ ቅዱስ አውጉስጢኖስም ደግሞ “ወንድሞቼ ሆይ! እኛ ደኀንነትን ብንፈልግ መገረዝ ያስፈልገናል፡፡ መንግሥተ ሰማያትን ለመውረስ ብንፈልግ ሥጋችንን መቅጣት ያስፈልገናል” (ቆላ. 2፣11) እያለ ይመክረናል፡፡

በመንፈስ ሳንገረዝ ለእግዚአብሔር ብቁዎች ለመሆን አንችልም፡፡ አስራኤላውያን በግርዘት የእግዚብሔር የተመረጠ ሕዝብ ሆኑ፤ ለእርሱ ተሰጡ፡፡ እኛ ከኃጢአት ከተገረዝን ለእግዚብሔር ብቁዎች እንሆናለን፡፡ ልባችን ከክፉ ሐሳብና ምኞት ከነጻ በኋላ በጸጋ ያጌጠ ማኀደረ ስለሚሆን በእርሱ ተደስቶ ያርፋል፡፡ መንፈሳችን ከዓለም በተገረዘ የእግዚብሔር መንፈስ ይሞላልና ሕይወታችን ከፈቃዱ ተስማምቶና ተግባብቶ ይሄዳል፡፡

14 January 2022, 16:24