ፈልግ

በነዋሪዎች ላይ የሚደርስ የመፈናቀል አደጋ በነዋሪዎች ላይ የሚደርስ የመፈናቀል አደጋ 

በዓለማችን ከ360 ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖችን ስደት እንደሚደርስ ተነገረ

“Open Doors” የተባለ ለትርፍ ያልተመሠረተ ድርጅት ድርጅት፣ በዓለማችን መፈናቀል እና ስደት የሚደርስባቸውን ክርስቲያኖችን የተመለከተ ዓመታዊ ሪፖርት ይፋ አድርጓል። ድርጅቱ በሪፖርቱ፣ በ58 አገራት ውስጥ ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት ብቻ መኖሪያቸውን ጥለው እንዲሰደዱ መገደዳቸውን አስታውቋል። ከመስከረም 21/2013 ዓ. ም. እስከ መስከረም 20/2014 ዓ. ም. ድረስ የተገደሉት ክርስቲያኖች ቁጥር 5,898 እንደሆነ፣ በተያያዘ ምክንያት የወደሙ ወይም እንዲዘጉ የተደረጉት ቤተ ክርስቲያኖች እና ሕንታዎች ቁጥር 5,110 መሆኑን አስታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ባሁኑ ጊዜ በ76 አገራት ውስጥ በክርስቲያኖች ላይ ከፍተኛ ስደት እና መከራ እንደሚደርስ ታውቋል። በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስተባባሪነት ሰኔ 13/2014 ዓ. ም. የሚከበረውን ዓለም አቀፍ የስደተኞች ቀን ምክንያት በማድረግ የአገር ውስጥ ተፈናቃዮችን እና ስደተኞችን ጨምሮ 100 ሚሊዮን ሰዎች መፈናቀላቸውን፣ “ስደተኛ ቤተ ክርስቲያን” የተባለ ድርጅት እ. አ. አ. በ2022 ዓ. ም. ሪፖርቱ አስታውቋል። “ስደተኛ ቤተ ክርስቲያን” በመባል የሚታወቅ ለትርፍ ያልተቋቋመ ድርጅቱ፣ በስደት መንስኤዎች እና መፍትሄዎቻቸው ላይ የመስክ ጥናቶችን በማካሄድ ዕና የቁሳቁስ ድጋፎችን እያቀረበ ከ60 ዓመታት በላይ ማስቆጥሩ ታውቋል። በመጀመሪያዎቹ 58 አገራት ውስጥ ክርስቲያኖች በሃይማኖታቸው ምክንያት ብቻ ከመኖሪያቸው በግዳጅ እንዲፈናቀሉ መደረጋቸውን ገልጾ፣ ከ 5 አገራት ከተፈናቀሉት ክርስቲያኖች መካከል 46% ከፍተኛ ስደት እና መከራ  የደረሰባቸው፣ ከ2/3 በላይ ወይም 68% የሚደርሱት መድልዎ የደረሰባቸው መሆኑን አስታውቋል። ክርስቲያኖች በብዛት በሚሰደዱባቸው 50 አገራት ላይ ባደረገው ጥናት እ. አ. አ ከጥቅምት 1/2020 እስከ መስከረም 30/2021 ዓ. ም. ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ከ360 ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች በእምነታቸው ምክንያት ከፍተኛ ስደት እና መድልኦ የደረሰባቸው መሆኑን የድርጅቱ በዘንድሮ ሪፖርቱ አስታውቋል።

የቁጥሮች መረጃዎች

“Open Doors” የተሰኘ ለትርፍ ያልቆመ ድርጅት በሪፖርቱ፣ የመስክ ጥናቱን ባካሄደባቸው የጊዜ ገደብ 5,898 ክርስቲያኖች መገደላቸውን እና ይህም እ. አ. አ በ2021 ዓ. ም. ከተገደሉት 4,761 ጋር ሲነጻጸር አራት ከመቶ መጨመሩን ገልጿል። በተያያዘ ምክንያት የወደሙ ወይም እንዲዘጉ የተደረጉት ቤተ ክርስቲያኖች እና ሕንታዎች ቁጥር 5,110 መሆናቸውን አስታውቆ ይህም 14% ጭማሪ ማሳየቱን አስታውቋል። ያለፍርድ ተይዘው የታሰሩት ክርስቲያኖች 6,175፣ የታገቱት ክርስቲያኖች ቁጥር 3,829 ሲሆን ይህ ቁጥር ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር ከ 1,710 በላይ ብልጫ ማሳየቱን ሪፖርቱ አመልክቷል። እ. አ. አ የ2022 ዓ. ም. ሪፖርት መሠረት ክርስቲያኖች ከቤታቸውና ከማኅበረሰባቸው እንዲፈቀሉ ሆን ተብሎ የተዘጋጀው የሃይማኖት ስደት፣ ክርስትናን ከአንድ ማኅበረሰብ ወይም አገር ለማጥፋት የታለመ ዘዴ ውጤት መሆኑን ሪፖርቱ ገሃድ አድርጓል። ዘዴው በአንዳንድ መልኩ በግልጽ የተፈጸመ ሕዝባዊ ዘዴ እንደሆነ፣ በሌላ ወገን ደግሞ ምስጢራዊ እና መደበኛ ያልሆነ መንገድ እንደሆነ ሪፖርቱ ገልጾ፣ የሃይማኖት ስደት የግድ በድንበር ብቻ የሚቆም አለመሆኑን፣ የግዳጅ መፈናቀል እና ስደት ክርስቲያኖችን በማንኛውም ወቅት ሊደርስባቸው እንደሚችል አስረድቷል።

በዓለም ዙሪያ የተፈናቀሉ ክርስቲያኖች

ከሰሃራ በታች ባሉ የአፍሪካ ሀገራት ክርስቲያኖች ላይ ስደትን እና መፈናቀልን የሚያደርሱ አገራት ካሜሩን፣ ሕዝባዊት  ዴሞክራሲያዊት ኮንጎ፣ ኤርትራ እና በተለይም እስላማዊ አክራሪ ቡድኖች በንብረት፣ በከብት እና በመሬት ላይ ያነጣጠሩባት ናይጄሪያም እንደምትገኝ ታውቋል። በመካከለኛው ምስራቅ እና በሰሜን አፍሪካ በዋናነት ከእምነት ጋር በተያያዙ ምክንያቶች አገራቸውን ጥለው የሚሄዱ ክርስቲያኖች ብዙውን ጊዜ ከፍተኛ የእስልምና እምነት ተከታዮች ቁጥር ካሉባቸው አገራት እንደሆነ ታውቋል። በዚህም መሠረት ከፍተኛ መፈናቀል የሚታይባቸው አገራት ኢራን እና ሶርያ ሲሆኑ፣ ባለፉት አስርት ዓመታት ውስጥ በቁጥር ዝቅተኛ በሆኑ የክርስቲያን ማኅበረሰቦች ላይ የተፈጸመው ጥቃት በርካታ ክርስቲያኖችን አገራቸውን ለቀው እንዲሰደዱ ማስገደዱ ታውቋል። በእስያ አህጉር ከፍተኛ የክርስቲያኖች ስደት የተመዘገበባቸው አገራት፥ አፍጋኒስታን፣ ምያንማር እና ፓኪስታን ሲሆኑ በእነዚህ አገራት የሚኖሩ ክርስቲያኖች ቤታቸውን እና አገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ ወይም እንዲፈናቀሉ የሚያደርጉ ቤተሰቦች እና የአካባቢው ማኅበረሰቦች መሆናቸው ታውቋል።

በላቲን አሜሪካ አገራት ክርስቲያኖች ላይ ለሚደርስ ስደት ምክንያቱ በዋናነት የፀጥታ ማጣት እና ወንጀል ሲሆን፣ ወንዶች በወንጀለኛ ቡድኖች ተቀጥረው እንዲሰሩ ወይም በመኖሪያ አካባቢያቸው በሚነሳ ዓመፅ ታፍነው ሲወሰዱ፣  ሴቶች እና ልጃገረዶች የፆታ ጥቃት ሰለባ ሊሆኑ እንደምሚችሉ ታውቋል። በእነዚህ ምክንያቶች ከፍተኛ የክርስቲያኖች መፈናቀል እና ስደት የሚታይባቸው የላቲን አሜሪካ አገራት፥ ኮሎምቢያ እና ሜክሲኮ ሲሆኑ፣ እንደ ኩባ፣ ኒካራጓ እና ቬንዙዌላ ባሉ ፈላጭ ቆራጭ መንግሥት ባለባቸው አገራት ውስጥ፣ የቤተ ክርስቲያን መሪዎች እና ምዕመናን በመንግሥት ላይ ጉልህ የሆነ ሕዝባዊ አመጽ ወይም ጸረ-መንግሥት ተቃውሞችን የሚሳተፉ ከሆነ ለስደት እንደሚዳረጉ ታውቋል።

16 June 2022, 15:47