የፍራንቺስካዊያን ካህናት በቅድስት ሀገር ለሚኖሩ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ድጋፍ ይሰጣሉ የፍራንቺስካዊያን ካህናት በቅድስት ሀገር ለሚኖሩ ክርስቲያኖች መንፈሳዊ ድጋፍ ይሰጣሉ 

‘ሮዚንግ ሴንተር’ የተባለው ተቋም ቅድስት ሀገር ውስጥ የሚገኙ ክርስቲያኖችን ሕይወት አስመልክቶ ሪፖርት አቀረበ

‘ሮዚንግ ሴንተር’ ተብሎ የሚታወቀው በሰላም ግንባታ እና የሃይማኖት ተቋማት የጋራ ውይይት ላይ የሚሰራው ተቋም በ 2016 ዓ.ም. በቅድስት ሀገር ክርስቲያኖች ላይ የተፈፀመውን የጥቃት ድርጊቶች የሚያሳይ አዲስ ዘገባ ማውጣቱ ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በቅድስት ሀገር በክርስቲያኖች ላይ የሚደርሰውን ጥቃት አስመልክቶ ዓመታዊው ሪፖርት ሰኞ አመሻሽ ላይ በኢየሩሳሌም የቀረበ ሲሆን፥ ይህ ሪፖርት የተዘጋጀው ለዓመታት በእስራኤል እና በፍልስጤም በሚኖሩ ክርስቲያኖች ላይ ተባብሶ የቀጠለውን ጥቃት በኢየሩሳሌም የአይሁድ እና የክርስቲያን ግንኙነት ማዕከል (JCJCR) በኩል ሲከታተል የቆየው ‘ሮዚንግ ሴንተር’ በተባለው የሰላም ግንባታ እና የሃይማኖት ተቋማት ውይይት ማዕከል እንደሆነ ተገልጿል።

በሪፖርቱ መሰረት በ 2016 ዓ.ም. ብቻ በክርስቲያኖች ላይ 111 ጥቃቶች ወይም የጥቃት ድርጊቶች የተመዘገቡ ሲሆን፥ ይህም በካህናቱ ላይ የሚሰነዘረውን ጥቃት እንደሚያካትት ነገር ግን በተወሰኑት ላይ እንደሆነ ተገልጿል።

አብዛኞቹ ጥቃቶች ግለሰቦች ላይ ያነጣጠሩ ሲሆኑ፥ ነገር ግን 35 የሚሆኑ ክሶች በአብያተ ክርስቲያናት፣ በገዳማት እና በሕዝብ ሃይማኖታዊ ምልክቶች ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ያሳያሉ።

በሁሉም ጉዳዮች ማለት ይቻላል፣ ወንጀሉን የፈጸሙ ሰዎች ተለይተው ሲታዩ የሃይማኖት-ብሔርተኛ አክራሪነት ክበቦች አባል የሆኑ ወጣት ኦርቶዶክሳዊ አይሁዶች መሆናቸው ታውቋል ተብሏል።

በእስራኤል መንግሥት ፖሊሲ ውስጥ እያደገ የመጣው የሃይማኖት-ብሔራዊ ጽንፈኝነት ተጽዕኖ ለአናሳ ሃይማኖቶች በተለይም ለክርስቲያኖች የማያቋርጥ ስጋት መፍጠሩ ይነገራል ።

ሮዚንግ ሴንተር ባደረገው ጥናት መሰረት 48 በመቶ የሚሆኑት ከ30 ዓመት በታች የሆኑ ክርስቲያን ወጣቶች ክልሉን ለቀው ለመሰደድ እያሰቡ መሆናቸውን ተናግረዋል። ከእነዚህም ውስጥ 77 በመቶ የሚሆኑት ደግሞ ዋናው ምክንያታቸውን ሲገልጹ፥ ክርስቲያኖች በሚደርስባቸው አድልኦ እና ጥቃት እንዲሁም አጠቃላይ የማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ሁኔታ መበላሸት እንደሆነ ተናግረዋል።

የሪፖርቱ አንድ ክፍል ከእስራኤል ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ቢሮ የወጣ አንድ አጠቃላይ ስታቲስቲክስን የሚተነትን ሲሆን፥ በ2016 ዓ.ም. የእስራኤል ህዝብ 10 ሚሊዮን መድረሱን እና ከእነዚህ ውስጥ 7.7 ሚሊዮን አይሁዶች ሲሆኑ 2.1 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ አረቦች ናቸው ይላል።

በእስራኤል የሚኖሩ ክርስቲያኖች 180,000 ብቻ ሲሆኑ፥ ከእነዚህም ውስጥ 80 በመቶ የሚሆኑት አረብ እንደሆኑና የአረብ ክርስቲያኖች በእስራኤል ውስጥ ከጠቅላላው የአረብ ህዝብ 7 በመቶውን እንደሚይዝ ተብራርቷል።

በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ብቻ 591,000 አይሁዶች እንደሚኖሩ፣ ይህም የአጠቃላይ ህዝቡን 61 በመቶ እንደሚሸፍን፥ የአረቦች ቁጥር ሲታይ ደግሞ 385,000 እንደሚሆኑ፣ ከእነዚህም ውስጥ ክርስቲያኖች 13,000 ብቻ እንደሆኑ እና በኢየሩሳሌም ውስጥ በሙስሊሞች እና በክርስቲያኖች መካከል ያለው ጥምርታ 96 በመቶ በ 4 በመቶ እንደሆነ መረጃው ያሳያል።

ካለፈው ዓመት ጋር ሲነጻጸር የአይሁድ ሕዝብ ግማሽ በመቶ መጨመሩ እና የአረብ ሕዝብ ግን በመንግሥት እየተስፋፋ ባለው ከተማውን “አይሁዳዊ” የማድረግ ፖሊሲ ጋር በሚስማማ መልኩ በዚያው ልዩነት መቀነሱ ተገልጿል።

የእስራኤል መንግስት በአሁኑ ጊዜ በምስራቅ እየሩሳሌም ላሉ አዲስ የአይሁድ ሰፈራዎች እቅድ እያፀደቀ ሲሆን፥ ይህም ወደ 11,500 አካባቢ አዳዲስ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት ያካትታል።

በተመሳሳይ ሁኔታ 29 በመቶ የሚሆኑ የቅድስት ከተማ ነዋሪዎች “ኦርቶዶክስ አይሁዶች” መሆናቸው የታወቀ ሲሆን፥ ይህም ማለት በአሁን ወቅት ኢየሩሳሌም ውስጥ ካለው አጠቃላይ የአይሁድ ህዝብ ብዛት ከግማሽ በላይ ይወክላሉ ተብሏል።

በሮዚንግ ሴንተር ተንታኞች እንደተገለጸው እነዚህ አዝማሚያዎች የሚያሳዩት እየሩሳሌምን እና ቅድስቲቱን ምድር ሆን ተብሎ አይሁዳዊ የማድረግ ዝንባሌ እንዳለ ያመለክታሉ ተብሏል።

እነዚህ አዝማሚያዎች የሕግ ማዕቀፉን ያገኙት “መሠረታዊ ሕግ” ተብሎ ከሚጠራው የእስራኤል ህግ ሲሆን፥ እስራኤል ሕገ መንግሥት ባይኖራትም ነገር ግን ‘መሠረታዊ ሕጎች’ በመባል የሚታወቁ ሃያ ወሳኝ ሕጎች እንዳሏት እና በተለይም በ 2010 ዓ.ም. የወጣው መሠረታዊ ሕግ “እስራኤልን የአይሁድ ሕዝቦች ሃገር” በማለት ይገልፃል።

ይህ ህግ በ 1984 ዓ.ም. በተለይም “ሰብአዊ ክብር እና ነፃነት” የሚል ርዕስ ተሰጥቶት ከወጣው መሰረታዊ ህግ ጋር ሲነጻጸር የተለያዩ ሃይማኖቶችን ከማካተት አንፃር ሲታይ በከፍተኛ ሁኔታ ማሽቆልቆሉን ያሳያል ተብሏል።

በ 2010 ዓ.ም. የወጣው መሰረታዊ ህግ ዜጎችን ወደ አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ በመከፋፈል በህዝቡ መካከል ያለውን የመከፋፈል ሁኔታ አሳሳቢ ያደርገዋል የተባለ ሲሆን፥ ይህም በአክራሪ አንጃዎች የሚፈጸሙትን የጥቃት ሁኔታዎችን የሚያነሳሳ ሊሆን ይችላል ተብሏል።

ሌላው ጉዳይ ምንም እንኳን ለትምህርት ቤቶች፣ ለወጣቶች ማዕከላት ወይም ለመንፈሳዊ ነጋዲያን የሚያገለግሉ የእንግዳ ማረፊያ ቤቶች ላይ የሚሰራ ባይሆንም ለአምልኮ ቦታዎች ብቻ የሚፈቀዱትን “በቁጥር አናሳ የሆኑ” ሃይማኖታዊ ድርጅቶች ላይ የሚተገበረውን የግብር ሥርዓት ይመለከታል።

ከማዘጋጃ ቤት ባለስልጣናት እና ከክርስቲያን ማህበረሰቦች፣ ከሁሉም በላይ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የቅድስት ሃገር ጠባቂ ገዳም መካከል በርካታ የህግ አለመግባባቶች የሚታዩ ሲሆን፥ ይህም የንብረት ባለቤትነት መብትን በተመለከተ ክፍተት እንዳለ ያሳያል ተብሏል።

በቅድስት ሀገር በተለይም በገሊላ እና በሰሜን አከባቢ ያሉ ክርስቲያኖችን እጅግ በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ያስገባው የመጨረሻው ጉዳይ በአንዳንድ የአረብ ሃገራት ስር የሰደደው እና ከተደራጁ ወንጀለኞች ጋር ግንኙነት ያላቸው የአመፅ መስፋፋት እንደሆነ ተገልጿል።

ባለፈው ዓመት ብቻ ከማፊያ ቡድኖች ጋር በተያያዘ የወንጀል ድርጊቶች ወደ 230 የሚጠጉ ሰዎች የተገደሉ ሲሆን፥ በዚህም ምክንያት በተፈጥሯቸው ሰላማዊና ሕግ አክባሪ የሆኑት በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ክርስቲያኖች ለሌላ የውጥረትና የችግር ምንጭ መዳረጋቸው ተገልጿል።
 

04 Apr 2025, 14:56