ፈልግ

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሃይማኖታቸው ምክንያት ስደት ለሚደርስባቸው ሰዎች እንጸልይ ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በየወሩ ለወሩ የሚሆን የጸሎት ሐሳብ ይፋ በማድረግ ምዕመኑ እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሰዎችሁሉ ከእርሳቸው ጋር በመንፈስ በመተባበር ጸሎት እንዲያደርጉ ጥሪ እንደ ሚያቀርቡ የሚታወቅ ሲሆን በዚህ መሰረት ቅዱስነታቸው ለጥር ወር 2014 ዓ.ም ይሆን ዘንድ ያቀረቡት የጸሎት ሐሰብ በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ውስጥ በሚገኙ ሕዝቦች ላይ በሐይማኖታቸው ምክንያት ስደት እየደርሰባቸው ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ጸሎት እንዲደረግ ጥሪ ማቅረባቸው ተገልጿል፣ በዚህ በቅርቡ በተጀመረው የጎርጎሮሳዊያኑን የቀን አቆጣጠር 2022 ዓ.ም የመጀመሪያ ወር ይሆን ዘንድ ባቀረቡት የጸሎት ሐሳብ ሃይማኖታዊ አድልዎ እና ስደትን ለመዋጋት ሲሉ የሃይማኖት ነፃነት በአምልኮ ነፃነት ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ከወንድማማችነት ጋር የተቆራኘ መሆኑን አስታውሰዋል።

የዚህ ዜና አቅርቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

“በዚህ የሰለጠነ ማህበረሰብ ውስጥ እምነታቸውን በይፋ በመናገራቸው ብቻ ስደት የሚደርስባቸው ሰዎች እንዲኖሩ እንዴት መፍቀድ እንችላለን?” በማለት ነበር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ለጥር ወር የሚሆን ወርሃዊ የጸሎት ሐሳብ በቪዲዮ ባቀረቡት መልእክት የተናገሩት።

“በአሁኑ ጊዜ ብዙ በቁጥር አነስተኛ የሆኑ ሰዎች የሚከተሏቸው ሰዎች ሃይማኖቶች አድልዎ ወይም ስደት ሊደርስባቸው የሚችለው እንዴት ነው?” በማለት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ጥያቄ አቅርበዋል።

የጥር ወር የጸሎት ሐሳብ የጳጳሱ ዓለም አቀፍ የጸሎት አውታረ መረብ አገልግሎት የሆነውን የጳጳሱን ቪዲዮ ሰባተኛውን ዓመት መጀመሩም ተገልጿል።

ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ማክሰኞ በታኅሳስ 26/2014 ዓ.ም ባስተላለፉት መልእክት ሰዎች እምነታቸውን በአደባባይ በመናገራቸው ብቻ ማሳደድ “ኢሰብዓዊ ያልሆነ” እና “እብድት” ነው ብለዋል።

ዓለም አቀፍ ክስተት

የዚን ወር የተጽሎት ሐሳብ መልእክት የሚደግፈው የካቶሊክ ግብረ ሰናይ ድርጅት “የሃይማኖት ነፃነት በዓለም” በሚለው ዓመታዊ ዘገባው በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ከሦስት አገሮች መካከል በአንዱ ውስጥ የሃይማኖት ነፃነት የሚጣስ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ ሁለት ሦስተኛውን አጠቃላይ የዓለም ሕዝቦች ተጠቂ እያደረገ የሚገኝ ክስተት ነው።

ከ646 ሚሊዮን በላይ ክርስቲያኖች የሃይማኖት ነፃነትን በሚጥሱ አገሮች ውስጥ ይኖራሉ ሲል ኤሲኤን ዘግቧል።

ለሌሎችን እንደ ወንድም እና እህት እውቅና መስጠት

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “የሃይማኖት ነፃነት በአምልኮ ነፃነት ላይ ብቻ የተገደበ ሳይሆን ልዩነታቸውን እንድናደንቅ እና እንደ እውነተኛ ወንድሞችና እህቶች እንድንገነዘብ ያደርገናል” ሲሉ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

እንደ ሃይማኖታዊ ልዩነቶች ያሉ ጉልህ ልዩነቶች እንኳ “ወንድማማችና እህትማማቾች የመሆንን ታላቅ አንድነት ሊያደበዝዙ አይገባም” ያሉ ሲሆን “የወንድማማችነትን መንገድ እንምረጥ። ምክንያቱም ወይ ወንድም እና እህቶች ነን ወይም ሁላችንም ተሸንፈናል” ሲሉ ተናግረዋል።

በዚህ በቅርቡ በተጀመረው የጎርጎሮሳዊያኑ 2022 ዓ.ም የመጀመሪያ ወር ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “መድልዎ የሚደርስባቸው እና ሃይማኖታዊ ስደት የሚደርስባቸው ወንድሞችና እህቶች በመሆን የሚገኘውን መብትና ክብር በሚኖሩባቸው ማህበረሰቦች ውስጥ እንዲያገኙ እንድንጸልይ” ይጋብዙናል።

10 January 2022, 13:00