ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ኢየሩሳሌምን በጎበኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ኢየሩሳሌምን በጎበኙበት ወቅት  

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ በሃይማኖት ተቋማት መካከል የምደረግ ውይይት ‘የዘመናችን ትክክለኛ አዎንታዊ ምልክት’ ነው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ዓለም አቀፍ የአይሁድ ሃይማኖታዊ ምክክር ኮሚቴ በተዘጋጀው ውይይት ላይ እንደ ተናገሩት ክርስቲያኖች እና አይሁዶች እርስ በርስ መገናኘታቸው እና በምዕራቡ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉ አሉታዊ አዝማሚያዎችን ለመከላከል በጋራ መሥራት አስፈላጊ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ “በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚደረጉ ውይይቶች የዘመኑ አዎንታዊ ምልክቶች ናቸው” በማለት ተናግረው “እግዚአብሔር ራሱ ጥበብ በተሞላበት እቅዱ ውስጥ በሃይማኖት መሪዎች እና በሌሎች በርካታ ሰዎች ውስጥ መልካም የሆኑ ተግባራትን የመፈለግ ፍላጎት እንዳደረበት አመላካች ምልክት ነው” ብለዋል። የሀይማኖት ልዩነትን በማክበር እርስ በርስ መተዋወቅና መወያየት” እንደ ሚያስፈልግም አክለው ገልጸዋል።

አብረው ለመመስከር ተጠርተዋል።

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ አስተያየት ከዓለም አቀፉ የአይሁድ ሃይማኖታዊ ምክክር ኮሚቴ ጋር በተደረገው ስብሰባ ላይ በጽሑፍ የቀረበ ነው። በጉልበታቸው ላይ ያጋጠማቸው ህመም በመባባሱ የተነሳ በስብሰባው ላይ በአካል መገኘት ባይችሉም መልእክታቸውን ግን በተወካያቸው በብፁዕ ካርዲናል ኩርት ኮች አማካይነት ለኮሚቴው በይፋ አስተላልፈዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ “አይሁዶችና ክርስቲያኖች በምዕራቡ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚታዩትን አንዳንድ አሉታዊ አዝማሚያዎች ለመቋቋም በተደጋጋሚ እርስ በርስ መገናኘታቸው በጣም አስፈላጊ ነው” በማለት ተናግሯል፤ “አይሁዶችና ክርስቲያኖች ስለ አምላክ እንዲመሰክሩ ተጠርተዋል” ብለዋል። የምሕረት እና የፍትህ ፣ ሁሉንም ሰው የሚወድ እና ለሁሉም ሰው የሚያስብ አንድ አማላክ እንዳለን መመስከር ይገባል ብለዋል።

ጥቃት እና ጥላቻ ከእምነት ጋር የማይጣጣሙ ነገሮች ናቸው

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱም “የእኛ ሃይማኖታዊ ባህሎቻችን አለመግባባቶችን ፣ ልዩነቶችን እና ግጭቶችን እንድንፈታ የሚጠይቁን በተጋላጭ መንገድ በአድልዎ ሳይሆን ነገር ግን በሰላማዊ ዓላማ እና በሁሉም ዘንድ ተቀባይነት ያለው የስምምነት ነጥቦችን እና ቦታዎችን ለማግኘት ነው” ብለዋል ።

በእርሱ መሐሪ እና ቸር በሆነው አምላክ ውስጥ ጥላቻ እና ዓመፅ “ከእኛ እምነት ጋር የማይጣጣሙ ናቸው” በማለት አጥብቆ ተናግሯል፣ እናም “ሁሉንም ፀረ-ሴማዊነት ለመቃወም” የቤተክርስቲያን ያላትን ቁርጠኝነት እንደገና አድሷል።

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በማጠቃለያ መልእክታቸው ላይ “በዓለማችን ወንድማማችነት እና ሰላም እንዲሰፍን የሚያስችል ልዩ መንገድ ነው” ብለዋል ። “ጌታ በዚህ የውይይት እና የወንድማማችነት ጎዳና ላይ እንዲመራን ጸሎት እንዲደረግ ቅዱስነታቸው ጠይቀዋል።

01 July 2022, 14:53