ፈልግ

የቻይና የሕዋ ምስል መመልከቻ ማዕከል የቻይና የሕዋ ምስል መመልከቻ ማዕከል 

ካርዲናል ፓሮሊን፣ ምድርን የሚያሰጉ ተግዳሮቶችን በጋራ መመከት እንደሚያስፈልግ አሳሰቡ

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ፣ ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊ፣ በጣሊያን አሲሲ ከተማ ከኅዳር 17 – 19/2014 ዓ. ም. በመካሄድ ላይ ለሚገኝ ብሔራዊ የተፈጥሮ ጥበቃ ጉባኤ መልዕክት አስተላለፈዋል። ብጹዕነታቸው በዚህ መልዕክታቸው፣ የጋራ መኖሪያ ምድራችን በእቅፏ እንደምትቀበል እናት እና ሕይወትን አብራን የምትጋራን እህት ናት ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በጋራ መኖሪያ ምድራችን ላይ የተደቀኑ ስጋቶችን በጋራ መመከት እንደሚያስፈልግ ያሳሰቡት ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊ፣ የአየር ንብረት ለውጦች፣ የምድራችን በረሃማነት፣ ብክለት እና የብዝሀ ሕይወት መጥፋት፣ እነዚህ በሙሉ የሰውን ልጅ እና የምድራችንን ሕይወት በሙሉ አደጋ ላይ የጣሉ አዳዲስ ተግዳሮቶች ናቸው" በማለት፣ በጣሊያን ውስጥ አሲሲ ከተማ ከኅዳር 17 – 19/2014 ዓ. ም. በመካሄድ ላይ ለሚገኝ ብሔራዊ የተፈጥሮ ጥበቃ ጉባኤ ባስተላለፉት መልዕክት አስረድተዋል።

ልዩ ልዩ የሃይማኖት መሪዎች እና ታዋቂ ሳይንቲስቶች ፣ የተቀናጀ የስነ-ምህዳር ትምህርት እና የጋራ እርምጃ መውሰድ አስፈላጊነትን የሚገልጽ ጠንካራ ሰነድ ፈርመው፣ በቅርቡ በእንግሊዝ ግላስጎው ከተማ ከጥቅምት 21 - ኅዳር 3/2014 ዓ. ም. በተካሄደው 26ኛ የተባበሩት መንግሥታት መሪዎች ጉባኤ ላይ ማቅረባቸውን ብጹዕ  ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን አስታውሰዋል።

የተቀናጀ የሥነ-ምህዳር መንገድ መከተል

የግጭት መንስኤዎችን በጋራ ማስወገድ እንደሚያስፈልግ የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፣ እነሱም “ስግብግብነት ፣ ግዴለሽነት ፣ ድንቁርና ፣ ፍርሃት ፣ ኢ-ፍትሃዊነት ፣ አለመተማመን እና አመጽ” ናቸው ብለዋል። ታኅሳስ 13/2013 ዓ. ም. በተካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የቅድስት መንበር አቋምን ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ መግለጻቸውን ያስታወሱት ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፣ ቅድስት መንበር የካርቦንዳይ ኦክሳይድ ልቀትን ወደ ዜሮ ማድረስ የሚለውን መርህ እንደምትደግፈው ገልጸው፣ “የተዋሃደ የሥነ-ምህዳር ትምህርትን ለማሳደግ ቁርጠኝነት መኖሩን ገልጸው ከብክንነት ባሕል ወደ እንክብካቤ እና ጥበቃ ባሕል መሸጋገር እንደሚያስፈልግ አስረድተዋል።

“እምነት እና ሳይንስ” በሚል አርዕስት የሐይማኖት መሪዎች እና የሳይንስ ጠበብት በቫቲካን ከተማ መስከረም 24/2014 ዓ. ም ስብሰባ ማካሄዳቸውን ያስታወሱት ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን፣ በስብሰባው ላይ ብዙ ባሕሎች ፣ መንፈሳዊ ጉዳዮች እና የተለያዩ ሳይንሳዊ መስኮች ሊገናኙ መቻላቸውን ገልጸው፣ የስብሰባው ተካፋዮች ከብክንነት ባሕል ወደ እንክብካቤ ባሕል ለመሸጋገር ጠንካራ ቁርጠኝነት እንዳላቸው መግለጻቸውን አስታውሰዋል።

ከአሁን በኋላ ጊዜን ማባከን አይቻልም

የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊ፣ ለጉባኤው ያስተላለፉትን መልዕክት ባጠቃለሉበት ወቅት እንደተናገሩት፣ በአየር ንብረት ቀውስ ስቃይ ውስጥ የወደቁ በርካታ ስዎች በመኖራቸው ከአሁን በኋላ ጊዜን ማባከን እንደማይቻል ገልጸው፣ የአየር ብክለትን እና የኮቪድ-19 ወርርሽኝ ያመጣውን ጫናን ለረጅም ጊዜ የተሸከሙት በተለይም ድሆች ፣ ከማኅበረሰቡ የተገለሉ ተጋላጭ ማኅበረሰቦች እና ስደተኞች መሆናቸውን አስታውሰዋል። "ወጣቶች ከእኛ ለውጥ ይፈልጋሉ" ያሉት የቅድስት መንበር ዋና ጸሐፊው፣ "ይህን ጠቃሚ የትምህርት፣ የባህል እና የስነ-ምግባር ፈተናን የምንጋፈጠው አሁን ነው" ብለዋል። 

27 November 2021, 16:11