ፈልግ

የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ሲደረግ የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ሲደረግ  

ብጹዕ ካርዲናል ጋምቤቲ፣ ቤተክርስቲያን የወንጌል መስካሪዎች ቤት መሆኗን አስገነዘቡ

ለቫቲካን ከተማ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ረዳት አስተዳደሪ የሆኑት ብጹዕ ካርዲናል ማውሮ ጋምቤቲ፣ ዘንድሮ የሚከበረውን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ ለቅድስት መንበር ሠራተኞች የመስዋዕተ ቅዳሴ ጸሎት በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ መርተዋል። ብጹዕነታቸው በመስዋዕተ ቅዳሴው ጸሎት ወቅት ባደረጉት ስብከት ቤተክርስቲያን የወንጌል ምስክሮች ቤት መሆኑን አስገንዝበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት መታሰቢያ በዓልን የማክበር አስፈላጊነት ባስረዱበት ስብከታቸው፣ የብርሃነ ልደቱ በዓል እግዚአብሔር የሰጠንን አስደናቂ ሕይወት ለመገንዘብ ልባችንን የምንከፍትበት ወቅት መሆኑን አስርድተዋል። በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ዙሪያ እንግዶችን የሚያገለግሉ፣ ​​የአትክልት ሥፍራዎችን የሚንከባከቡ፣ የቫቲካን ሙዚዬሞችን በፍቅር እና በጥንቃቄ የሚጠብቁ መኖራቸውን የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ማውሮ ጋምቤቲ፣ ሠራተኞቹ ቤተ ክርስቲያንን እና ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳትን በኅብረት የማገልገል ተልዕኮ አስፈላጊነት በድጋሚ አረጋግጠዋል።

እግዚአብሔር የዓለም ብርሃን እና ሕይወት

በትንቢተ ኢሳይያስ መጽሐፍ በምዕ. 54፡ 7 ላይ “ለጥቂት ጊዜ ተወሁሽ፣ በታላቅ ምሕረት ይቅር እልሻለሁ” ተብሎ የተጻፈውን በማስታወስ ቤተክርስቲያን አስቸጋሪ የጨለማ ወቅቶችን በማሳለፍ ላይ የምትገኝ ብትሆንም የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ልደት፣ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ቅርብ በመሆኑ የደስታ ሕይወትን የሚያጎናጽፍ መሆኑን ብጹዕ ካርዲናል ጋምቤቲ አስረድተዋል። እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያሳየውን ርኅራኄ እና ፍቅር ያስታወሱት ብጹዕነታቸው፣ ሕይወትን የሚሰጥ እግዚአብሔር ሕይወቱ በእያንዳንዳችን ውስጥ እንዲያበራ በማድረግ ብርሃነ ልደቱ ሁል ጊዜ እግዚአብሔር በውስጣችን መገኘቱን ያረጋግጥልናል ብለዋል።

ቤተ ክርስቲያን የፍጹማን ሳትሆን የወንጌል መስካሪዎች ቤት ናት

በእያንዳንዱ ሰው ልብ ውስጥ ሕይወት እንዲኖር በማለት ብጹዕ ካርዲናል ማውሮ ጋምቤቲ የገለጹት መልካም የብርሃነ ልደቱ በዓል ምኞት ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ጋር በመሆን እምነትን በመጠበቅ የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የእምነት ምስክሮች ለመሆን የተሰጠ ተልዕኮ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፣ ይህ ተልዕኮ ይበልጥ ግልጽ በሆነ መንገድ ወደ ዓለም ሁሉ ለመውሰድ የተሰጠ ተልዕኮ መሆኑ ተገልጿል። በሰው ልጆች ዘንድ የሚታዩ የጥፋት እና የፍርሃት ስሜቶች መኖቸውን የገለጹት ብጹዕ ካርዲናል ማውሮ ጋምቤቲ፣ እነዚህ የጥፋት እና የፍርሃት ስሜቶች ቤተክርስቲያንን በተጓዘችባቸው መንገዶች ሁሉ ያጋጠሟት መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም የተነገረንን ትንቢት በመረዳት ለሌሎች ማካፈል እንደሚገባ፣ ቤተክርስቲያን የፍጹማን ሳትሆን መልካም ዜናን የሚመሰክሩ ክርስቲያኖች ቤት መሆኗን ገልጸው፣ በድፍረት፣ በፍርሃት እና በትዕቢት ምክንያት ከእግዚአብሔር ያልራቀው ቅዱስ ጴጥሮስ የእምነት ምስክር እንጂ የፍጹምነት ምስክር እንሳልነበረ አስረድተዋል።

ማንነትን ለይቶ ማወቅ

የብርሃነ ልደቱ በዓል ሲደርስ ማንነትን መለየት ያስፈልጋል ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ማውሮ ጋምቤቲ፣ ከመጥመቁ ዮሐንስ ሰዎች አንዱ ወይም እንደ ሙሴ ሕግ መምህራን የማያምኑ እና የማይጠመቁ፣ የእግዚአብሔር የማዳን ዕቅድ እንዲፈጸም ከማይፈቅዱ አንዱ በመሆን አቋም መውሰድ አስፈላጊ ነው ብለዋል። እንደ ሄሮድስ ቁጡዎች፣ ማርያምን እና ዮሴፍን እንደማይቀበሉ እንደ ቤተልሔም ነዋሪዎች ትኩረታቸው የተከፋፈለ፣ ትሑት ሠራተኞች፣ እንደ እረኞች ወይም እንደ ማርያም እና ​​እንደ ዮሴፍ ለእግዚአብሔር ፈቃድ ራስን ክፍት በማድረግ ሕይወትን እንደሚጠብቁ መሆን ያስፈልጋል ብለዋል።

18 December 2021, 15:51