ፈልግ

በቤርሊን እ. አ. አ በ1936 ዓ. ም. የተካሄደው የወዳጅነት ኦሎምፒክ ውድድሮች በቤርሊን እ. አ. አ በ1936 ዓ. ም. የተካሄደው የወዳጅነት ኦሎምፒክ ውድድሮች 

አቶ ፓስኳሌ፣ ስፖርት የእውነተኛ ወዳጅነት አስተማሪ መሆኑን ገለጹ

በጀርመን ቤርሊን ከተማ እ. አ. አ በ1936 ዓ. ም. የተካሄደው የኦሎምፒክ ውድድሮች በታሪክ ውስጥ የማይረሱ ትዝታዎችን አስቀምጦ ማለፉን እና በውድድሩ የተሳተፉ ሁለት የጃፓን፣ አንድ የሰሜን አሜሪካ እና አንድ የጀርመን ተወዳዳሪዎች መኖራቸውን “የጸጋ ፍለጋ” በሚል ርዕሥ የሚታወቅ ዩትዩብ ማኅበራዊ ሚዲያ ዝግጅት አስታአባባሪ የሆኑት አቶ ፓስኳሌ ቴዎሊ፣ ቅዳሜ ሐምሌ 24/2013 ዓ. ም ተከብሮ የዋለውን ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ቀን ምክንያት በማድረግ ከቫቲካን የዜና አገልግሎት ጋር ማደረጉት ቃለ ምልልስ አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ቀን ተከብሮ የዋለው፣ በጃፓን ውስጥ የኦሊምፒክ ውድድሮች በመካሄድ ላይ ባሉበት ወቅት መሆኑ ታውቋል። ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ቀን በየዓመቱ ሐምሌ 23 ቀን እንዲከበር የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ እ. አ. አ በ2011 ዓ. ም. መወሰኑ ይታወሳል። የመንግሥታቱ ድርጅት በዓሉ በዚህ ቀን እንዲከበር የወሰነው ዓለም አቀፍ ወዳጅነት እንቅስቃሴ እ. አ. አ 1958 ዓ. ም. ለመጀመሪያ ጊዜ የተመሰረተው በፓራጓይ ተወላጅ በሆኑት በክቡር አቶ ራሞን አርቴሚዮ ብራቾ መሆኑ ይታወሳል።  ዓላማውም የሰላም ባህልን መሠረት በማድረግ ወዳጅነትን ማራመድ ስለ ነበር፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ከሃምሳ ዓመታት በኋላ ሐምሌ 23 ቀን ዓለም አቀፍ የወዳጅነት ቀን በየዓመቱ እንዲከበር በማለት ወስኗል።

ያ ባለ ሁለት ቀለማት ሜዳሊያ

ወዳጅነትን በስፖርት ዘርፍም ማሳደግ ይቻላል ያሉት አቶ ፓስኳሌ ቴዎሊ፣ ወዳጅነትን በነጠላ የሚደረጉ ውድድሮችን ጨምሮ በቡድን በሚደረጉ ጨዋታዎችም ማሳደግ የሚቻል በመሆኑ፣ የጋራ ስፖርታዊ ፍቅርን በቡድን አባላት፣ በአሠልጣኞች እና በአትሌቶች መካከል ማሳደግ ከመቻል ባሻገር በተቃዋሚዎች መካከል የተወለዱ ስፍር ቁጥር የሌላቸው የወዳጅነት ታሪኮች መኖራቸው ይታወቃል።  ከስፖርታዊ ውድድሮች ጋር በተያያዘ ሊረሱ እና ከሰዎች ልብ ሊጠፉ የማይችሉ በርካታ የኦሎምፒክ ውድድር ገጠመኞች አሉ። እ. አ. አ በ1936 ዓ. ም በጀርመን ቤርሊን ከተማ የተካሄደውን የኦሊምፒክ ውድድርን የምናስታውስ ከሆነ እስከ ዛሬ ጥሩ ምሳሌ ሆነው የቆዩ ሁለት ታሪካዊ ገጠመኞች መናራቸውን “የጸጋ ፍለጋ” በመባል የሚታወቀውን የዩትዩብ ማኅበራዊ ሚዲያ ዝግጅት አስታአባባሪ አቶ ፓስኳሌ ቴዎሊ ከቫቲካን የዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስታውሰዋል።

ለፍፃሜው ውድድር ሶስት አትሌቶች የቀረቡበት የዋልታ ዝላይን ያስታወሱት አቶ ፓስኳሌ ቴዎሊ፣ የዚህ ውድድር አሸናፊ የሆነው አሜሪካዊ ተወዳዳሪ ቢሆንም ተመሳሳይ ውጤትን ለማስመዝገብ በስተጀርባ ሁለት ጃፓናዊ አትሌቶች እንደነበሩ አስታውሰዋል።

እ. አ. አ. በ 1936 ዓ. ም ለሁለቱም የብር ሜዳልያ አሸናፊነት ሽልማት የመስጠት ዕድል ስላልነበረ ሁለተኛውን እና ሦስተኛውን ቦታ የሚወስዱትን ለመለየት የማጣሪያ ጨዋታ እንዲደረግ መድረጉን አቶ ፓስኳሌ አስታውሰው፣ ነገር ግን ጃፓናዊያናኑ ተወዳዳሪዎች ተመሳሳይ ውጤት ካመጡ በኋላ በመካከላቸው ሌላ ውድድር ለማካሄድ ፍላጎት አልነበራቸውም። ዳኞችም በበኩላቸው ሁለቱ ተወዳዳሪዎች ባደረጉት የዝላይ ብዛት ላይ በመመርኮዝ ለኒሺዳ የነሐስ፣ ለኦ የብር ሜዳሊያን ሸልመው ነበር።

ይሁንና ተወዳዳሪዎቹ ወደ ጃፓን ሲመለሱ ሁለቱም ወደ ጌጣጌጥ መደብር ሄደው ሜዳልያዎቻቸው በግማሽ እንዲቆርጡ በማድረግ እያንዳንዳቸው አንድ ክፍል በብር እና ሁለተኛው በነሐስ እንዲቀረጽ አደረጉ። ሱዌ ኦ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ሰለባዎች መካከል አንዷ ስትሆን ኒሺዳ ሁለቱንም ሜዳሊያዎች በግሏ ይዛቸው መቆየቷል አቶ ፕስኳሌ አስታውሰዋል። የኦኢ ሜዳልያ ዛሬ በዓለም ላይ ታዋቂ ከሆኑት የስፖርት ሙዚየሞች መካከል በአንዱ ውስጥ በክብር ተቀምጦ የሚገኝ መሆኑን እና በኦሎምፒክ ጨዋታዎች ታሪክም ልዩ ሥፍራ የሚሰጠው መሆኑን አስታውሰዋል።

በወቅቱ በተደረገው የኦሎምፒክ ጨዋታዎች የተወዳደሩ ሁለት አትሌቶች፣ እነርሱም አንድ ጀርመናዊ እና አንድ አሜሪካዊ ተወዳዳሪዎች መኖራቸውን ያስታወሱት አቶ ፓስኳሌ ቴዎሊ፣ እነዚህ ተወዳዳሪዎች ከውድድሩ በፊትም እርስ በእርስ የሚተዋወቁ እንደነበር አስታውሰው፣ በኦሊምፒ ውድድሮች አራት የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ የሆነው አሜሪካዊ ጄስ ኦዌን በኦሊምፒክ ታሪክ ውስጥ የማይዘነጋ አንድ መልዕክት ጽፎ ማስቀመጡን አስታውሰዋል። በውድድሩ አስደናቂ ውጤቶችን እያስመዘገበ ለፍጻሜ ደረጃ የደረሰው ኦዌን በመጨረሻው ዕለት ችግር እንዳጋጠመው የተገነዘበው ጀርመናዊው ተወዳዳሪ ሉዝ ሎንግ፣ ኦዌንን የአሸናፊነት ዕድል እንዳያመልጠው ጠቃሚ ምክሮችን በመለገስ ለአሸናፊነት ማብቃቱን አስታውሰዋል። በዚህም ሁለቱ ተወዳዳሪዎች በመካከላቸው የነበረውን ወንድማማችነት የበለጠ ለማሳደግ መብቃታቸውን አስታውሰው በየጊዜው በሚላላኩት የጽሑፍ መልዕክት ወዳጅነታቸውን ጠብቀው ያቆዩ መሆኑን አስታውሰዋል። ጀርመናዊው የኦሊምፒክ ጨዋታዎች ተወዳዳሪ የነበረው ሎንግ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ላይ በመሳተፍ ከመሞቱ አስቀድሞ ለአሜሪካዊ ወዳጁ ለሆነው ኦዌን በጻፈው የመጨረሻ መልዕክት፣ ጦርነቱ ሲያልቅ ወደ ጀርመን በማቅናት፣ በመካከላቸው የነበረውን ወዳጅነትን ጦርነትም ቢሆን ሊያስቀር እንደማይችል ለልጁ እንዲነግር ማሳሰቡን አቶ ፓስኳሌ ቴዎሊ አስታውሰዋል።

 

“የኦሊምፒክ ጨዋታ ውድድሮች ውበት ይህ ነው” በማለት የገለጹት አቶ ፓስኳሌ ቴዎሊ፣ የኦሊምፒክ ውድድሮቹ በታሪክ የማይደገሙ ትዝታዎችን፣ አስፈላጊ ከሆኑ እሴቶች ጋር የተቆራኙ እና የማይረሱ ታሪኮች ምስክሮች እንድንሆን የሚያድረጉ መሆናቸውን ከቫቲካን የዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አስረድተዋል።

02 August 2021, 17:15