ፈልግ

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በዓለም የድሆች ቀን ያቀረቡት መስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ በዓለም የድሆች ቀን ያቀረቡት መስዋዕተ ቅዳሴ ሥነ-ሥርዓት 

የቤተክርስቲያን አስተምህሮ ተግባራዊ ለማድረግ በቂ ግንዛቤ ሊኖር እንደሚገባ ተገለጸ

በሮም ከተማ የሚገኝ ታላቁ የቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ አስተዳዳሪ ብፁዕ ካርዲናል ፍራንችስኮስ ሞንተሪሲ፣ የቤተክርስቲያንን አስተምህሮን ተግባራዊ ለማድረግ በቅድሚያ ግንዛቤው ሊኖር እንደሚገባ አስታወቁ። በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ተግባራዊነት ላይ በማስተንተን ሃሳባቸውን የገለጹት ብፁዕ ካርዲናል ፍራንችስኮስ ሞንተሪሲ፣ “የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ” በሚለው ላይ በማስተንተን፣ በዛሬው ዓለም ክርስቲያን መሆን ምን ማለት እንደሆነ በማስረዳት የጻፉት መጽሐፍ፣ 23 ብጹዓን ካርዲናሎች ያበረከቱት ልዩ ልዩ አስተያየቶች ውጤት መሆኑ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

“ካቶሊካዊነት በተግባር ሊታይ ይችላል፣ ነገር ግን ተግባራዊ ለማድረግ በቤተክርስቲያን አስተምህሮ ላይ በቂ ዕውቀት ሊኖር ይገባል” ያሉት ብፁዕ ካርዲናል ፍራንችስኮስ ሞንተሪሲ፣ በሮም የሚገኝ የቅዱስ ጳውሎስ ባዚሊካ አስተዳዳሪ ሲሆኑ፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ መጽሐፍን ከደረሱ 23 ካርዲናሎች መካከል አንዱ መሆናቸው ታውቋል። በሮም ከተማ በሚገኝ በመንፈስ ቅዱስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ዛሬ ማታ ለአንባቢያን የቀረበው አዲሱ መጽሐፍ፣ በዛሬው ዓለማችን በክርስትና ትርጉም ዙሪያ ለሚነሱ ክርክሮች መልስ ለመስጠት የሚደረገውን ተነሳሽነት የሚደግፍ መሆኑ ታውቋል።  

ሬስ ማኛ በሚባል ማኅበር እና በቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳዎሎስ ዳግማዊ ፋውንዴሽን እገዛ የታተመው ይህ መጽሐፍ ያስፈለገበት ምክንያት የካቶሊክ ቤተክርስቲያንን አስተምህሮ የበለጠ ለመረዳት የሚያስችል መሆኑን ያስረዱት ካርዲናል ፍራንችስኮስ ሞንተሪሲ፣ "መጽሐፉ እነዚህን ጭብጦች በልዩ ሁኔታ በማስተዋወቅ ፣ በተለይም ለዕለት ተዕለት ሕይወት እና ከሁሉም ለመንፈስ ቅዱስ እና ለቅዱሳት ምስጢራት ትኩረትን እንድንሰጥ ያግዛል” ብለዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ አስተያየታቸውን ያካፈሉት “አቬኔር” የተሰኘ ካቶሊካዊ ጋዜጣው ዳይሬክተር ክቡር አቶ ማርኮ ታርኩኒዮ፣ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፣ ሁሉም ሰው ሁሉንም ነገር እንደሚያውቅ በሚያስብበት ወቅት ለክርስቲያኖች ጥንካሬን የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል። 

በቤተክርስቲያን በኩል የሚሰጥ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ለክርስቲያኖች የሚሰጠው ጥንካሬ እና ብርታት ለእምነታቸው የማዕዘን ድንጋይም እንደሆነ የሚያምኑት ክቡር አቶ ማርኮ ታርኩኒዮ፣ "በዲጂታሉ የመረጃ መንገዶች በኩል የሚሰራጩ መረጃዎችን መሠረት ያደረገ እውነት የተበታተነ እና የሚኖረውም ተቀባይነት አጠራጣሪ እንደሆነ አስረድተዋል። ነገር ግን በሌላ ወገን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ፣ የእምነት አባቶች ለምዕመናን የሚያካፍሉት የክርስቲያን ማኅበረሰብ የሕይወት ተሞክሮ በብዙ ዓመታት ውስጥ የተሰጠንን መንፈሳዊ አስተምሮ በጥልቀት ለመመልከት ዕድል የሚሰጥ መሆኑን አስረድተዋል።

የክርስቲያናዊ እይታ ይዘትን በተመለከተ፣ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ መሠረታዊ ነገር ፍቅርን የሚመለከት መሆኑን የገለጹት ክቡር አቶ ማርኮ ታርኩኒዮ፣ ማንኛውም የፍፁም ክርስቲያናዊ በጎነት ልምምድ የሚመነጨው ከፍቅር ብቻ እንደሆነ እና የመጨረሻ ግቡም ፍቅር መሆኑን ገልጸው፣ በመገናኛ ብዙሃን በኩል የሚመጣውን መከፋፈል ማሸነፍ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል።

29 November 2021, 14:38