ፈልግ

ቀዝቃዛው ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌዬር ጦር መሳሪያ እየበዛ መምጣቱ ተገለጸ! ቀዝቃዛው ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌዬር ጦር መሳሪያ እየበዛ መምጣቱ ተገለጸ! 

ቀዝቃዛው ጦርነት ከተጀመረ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የኒውክሌዬር ጦር መሳሪያ እየበዛ መምጣቱ ተገለጸ!

በግጭቶች እና የጦር መሳሪያዎች ላይ ግንባር ቀደም በመሆእ መልኩ ምርምር በማድረግ የሚታወቀው ተቋም  ይፋ ያደረገው አንድ ዘገባ እንደሚያሳየው የዓለም አቀፉ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ ስርጭት እና ምርት ከቀዝቃዛው ጦርነት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በሚቀጥሉት ዓመታት በመጠን እና በስርጭት ያድጋል ተብሎ ይጠበቃል ። እንደነዚህ ያሉ የጦር መሳሪያዎች ጥቅም ላይ ከዋሉ የሚያስከትሉት አደጋ ከአስርተ አመታት በላይ ከፍተኛ እንደሆነም ያስጠነቅቃል ሪፖርቱ።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በንግግራቸው፣ በመልእክቶቻቸው፣ በጳጳሳዊ መልእክታቸው እና ከተለያዩ አገራት መሪዎች ጋር በነበራቸው ግንኙነት ላይ ከኒውክሌዬር ጦር መሣሪያ ነፃ የሆነ ዓለም እንዲፈጠር ጥሪ ማቅረባቸውን እና በተደጋጋሚ እያቀረቡ እንደ ሚገኙ የሚታወቅ ሲሆን የኒውክሌር ጦር መሳሪያዎችን መጠቀም እና ማከማቸት “የማይታሰብ” እና በሰው ልጅ እና በፕላኔቷ ላይ አስፈሪ አደጋ መሆኑን በተደጋጋሚ መግለጻቸው ይታወሳል።

ሩሲያ ዩክሬንን ከወረረች ከሶስት ቀናት በኋላ እና ምዕራባውያን ለኪየቭ ድጋፍ ካሳዩ ከሶስት ቀናት በኋላ የሩሲያው ፕሬዝዳንት የሩሲያን የኒውክሌር መከላከያ በከፍተኛ ደረጃ በጥንቃቄ እንዲዘጋጅ ባደረጉበት ወቅት ሥጋቱ የበለጠ አጣዳፊ ሆነዋል።

አሳሳቢ አዝማሚያ

በአውሮፓ ያለው ጦርነት በአለም ውስጥ ዘጠኙ የኒውክሌር ጦር መሳሪያ የታጠቁ መንግስታት መካከል ውጥረትን እንዳባባሰ እና አሳሳቢ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ታዛቢዎች እና ተንታኞች ይስማማሉ።

ሰኞ ሰኔ 06/2014 ዓ.ም የስቶክሆልም አለም አቀፍ የሰላም ምርምር ኢንስቲትዩት (SIPRI) እ.አ.አ በጥር 2021 እና ጥር 2022 ዓ.ም መካከል የኑክሌር ጦር መሳሪያዎች ቁጥር በትንሹ ቢቀንስም፣ በኑክሌር ሀይሎች አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ በስተቀር፣ አለም አቀፍ የጦር መሳሪያ ፈጠራዎች በቅርቡ ለመጀመሪያ ጊዜ መጨመር ሊጀምሩ እንደሚችሉ ተናግሯል። በአሥርተ ዓመታት ውስጥ የታየ አስደናጭ ክስተት እንደ ሆነም አክሎ ገልጿል።

በእንግሊዘኛው ምጻረ ቃል “SIPRI” (የስቶክሆልም ዓለም አቀፍ የሰላም ምርምር ተቋም) እ.አ.አ በ2022 ዓ.ም ባወጣው አመታዊ ሪፖርት ላይ እንደ ገለጸው ከሆነ “ሁሉም ኑክሌዬር የታጠቁ መንግስታት የጦር መሳሪያ ማከማቻዎቻቸውን እያሳደጉ ወይም እያሻሻሉ ነው፣ እናም አብዛኛዎቹ የኑክሌዬር አረሮች እና የኑክሌር ጦር መሳሪያ በወታደራዊ ስልታቸው ውስጥ የሚጫወተው ሚና” እያደገ መምጣቱን ሪፖርት አመልክቷል።

ዊልፍሪድ ዋን የ SIPRI "የጅምላ ጥፋት መሳሪያ ፕሮግራም" ዳይሬክተር ናቸው። በሩስያ መንገድ ላይ ለቆሙት ሀገራት "በታሪክ ውስጥ ታይቶ የማይታውቅ" ሊሆኑ የሚችሉ የሩሲያ ወታደራዊ ምርጫዎች የሚያስከትለው መዘዝ እንዳሳሰባቸው ገልጿል።

ሩሲያ እና አሜሪካ የአለም ትልቁ የኒውክሌዬር ጦር መሳሪያ ባለቤት ናቸው።

ሩሲያ በዓለም ትልቁ የኒውክሌዬር ጦር መሳሪያ በድምሩ 5,977 የኒውክለር ጦር መሳሪያ አረሮች ያሏት ሲሆን ይህም ከዩናይትድ ስቴትስ በ550 ገደማ ይበልጣል። ሁለቱ ሀገራት ከ90% በላይ የአለም የኒውክለር ጦር መሳሪያ  ባለቤት ናቸው፣ ምንም እንኳን SIPRI ቻይና ከ 300 በላይ አዳዲስ ሚሳኤሎች በመስፋፋት ላይ ትገኛለች በማለት ቢገልጽም።

SIPRI እ.አ.አ በጥር 2021 እና በጥር 2022 ዓ.ም መካከል ያለው የአለምአቀፍ የኒውክሌዬር ጦር አረር ራሶች በትንሹ የቀነሰ ቢሆንም በግምት 3,732 የጦር አረር ራሶች በሚሳኤል እና በአውሮፕላኖች ውስጥ ተገጥመው በዚህ ተግባር ላይ ተሰማርተው እንደነበር እና ወደ 2,000 የሚጠጉ - የሩሲያ ወይም የዩናይትድ ስቴትስ ንብረት የሆኑ ሁሉም ማለት ይቻላል - ውስጥ  በከፍተኛ የዝግጁነት ሁኔታ ተቀምጠዋል ብሏል።

በዚህ ሪፖርት መሰረት በሌሎች የአለም ክፍሎች ያሉ የኒውክሌር ክምችቶችን እና ሙከራዎችን መፈተሽ እና መተንተን ቸል አላለም እና በህንድ እና በፓኪስታን መካከል ያለውን ቀጣይ ግጭት፣ በቻይና ህንድ ድንበር ላይ እየጨመረ ያለውን ጠላትነት እና የሰሜን ኮሪያን ቀጣይነት ያለው የኒውክሌር ጥረት እንደ ዋና ዋና አካላት አመልክቷል። በአሁኑ ጊዜ ዓለምን በጣም አሳሳቢ በሆነ ሁኔታ ውስጥ በማስቀመጥ ረገድ ትልቅ ሚና ይጫወታል ብሏል።

ለአለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድ የቀረበ ጥሪ

አስቸኳይ ዓለም አቀፍ እርምጃ እንዲወሰድ እና ቀጣይነት ባለው መልኩ በኒውክሌዬር የጦር መሣሪያ ዙሪያ ላይ አዲስ ፖሊሲ እንዲረቀቅ የጠየቁ የ SIPRI የቦርድ ሊቀመንበር እና የቀድሞ የስዊድን ጠቅላይ ሚኒስትር ስቴፋን ሎፍቨን ፣ “በዓለም ታላላቅ ኃይሎች መካከል ያለው ግንኙነት የበለጠ እየከፋ እና እየተባባሰ መጥቷል፣ የሰው ልጅ እና ፕላኔቷ ብዙ ጥልቅ እና አንገብጋቢ የጋራ ጉዳዮችን በሚያጋጥሙበት ጊዜ በአለም አቀፍ ትብብር ብቻ ሊፈቱ የሚችሉ ተግዳሮቶች ናቸው በማለት ተናግረዋል።

የኑክሌር ጦርነት ሥነ ምግባር የጎደለው ነው

ር.ሊ.ጳ ፍራንቸስኮስ ከኅዳር 12-16/2012 ዓ.ም ድረስ 32ኛውን ሐዋርያዊ ጉብኝታቸው በጃፓን ማካሄዳቸው የሚታወስ ሲሆን በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባደረጉት ንግግር “ለጦርነት ዓላማ የአቶሚክ ኃይልን ተጠቅሞ ጦርነት ማካሄድ ከመቼውም ጊዜ ይበልጥ ዛሬ፣ በሰው ልጆች ክብር ላይ ብቻ ሳይሆን የጋራ የመኖርያ ቤታችን በሆነች በምድራችን ላይ የሚፈጸም በደል ነው፣ የአቶሚክ ኃይል ለጦርነት መጠቀም ሥነ ምግባር የጎደለው ተግባር እንደመሆኑ መጠን፣ የአቶሚክ የጦር መሥርያ አምርቶ ማከማቸት በራሱ ሥነ ምግባር የጎደለው ተግባር ነው” በማለት መናገራቸው ይታወሳል። አክለውም “ስለሰላም ብቻ በማውራት ሰላምን ግን በተጨባጭ በምድር ላይ በሚኖሩ ሕዝቦች መካከል ለማምጣት ባለመቻላችን መጪው ትውልድ በእኛ ላይ እንደ ሚፈርድ”  መግለጻቸው የሚታወስ ሲሆን አክለውም “ሰላም በእውነት ላይ የተመሠረተ ፣ በፍትህ የተገነባ ፣ በልግስና የተሟላ እና ነጻነትን የሚያስገኝ መሆን አለበት” ማለታቸው ይታወሳል።

በእጆቻችን ላይ የሚገኙ የኒውክለር የጦር መሣርያዎችን እናስወግድ

“ይበልጡኑ ፍትሃዊ እና ደህንነቱ የተጠበቀ ማህበረሰብ መገንባት ከፈለግን በእጆቻችን ላይ የሚገኙትን የኒውክሌዬር የጦር መሣርያዎችን ማስወገድ ይኖርብናል” በማለት በንግግራቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው  “ግጭቶችን ለመፍታት እና ለግጭቶች መፍትሄ ለመስጠት የኒውክሌዬር ጦር መሳሪያ ይህንን ስጋት ለመቀረፍ የሚያስችል  ሕጋዊ የሆነ መስመር ነው ብለን በማሰብ የኒውክሌር የጦር መሳሪያዎችን ለማጋበስ በምናደርገው ሩጫ የተነሳ እንዴት ሰላምን ማረጋገጥ እንችላለን?” በማለት ቅዱስነታቸው ጥያቄ ማቅረባቸው ይታወሳል።  “እውነተኛ ሰላም የሚረጋገጠው የጦር መሳሪያዎችን በማስወገድ ብቻ አይደለም ፣ ምክንያቱም ሰላም ማለት የጦርነት አለመኖር ብቻ ማለት ስላልሆነ! በአንጻሩ ሰላም ማለት ከታሪክ እንደ ተማርነው እና እንደ ተረዳነው የፍትህ፣ የልማት፣ የአንድነት፣ የጋራ መኖሪያ ቤታችን የሆነችውን ምድራችንን መንከባከብ እና የጋራ ተጠቃሚነትን ማስፈን” ማለት በመሆኑ የተነሳ ጭምር ነው ብለዋል።

እ.አ.አ በነሐሴ 6/1945 ዓ.ም 8፡15 ደቂቃ ላይ በሂሮሺማ ከተማ ላይ በተጣለው የመጀመሪያው አቶሚክ ቦንብ በወቅቱ ከተማይቱን ሙሉ በሙሉ እንድትወድም ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ከእዚህም ጋር በተያያዘ መልኩ በእዚህ አቶሚክ ቦንብ አማካይነት በቅጽበት ከ70 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉ የሚታወስ ሲሆን ከእዚያም በመቀጠል ደግሞ የአቶሚክ ቦንቡ ባደርሰው የጨረር አደጋ ቀስ በቀስ የ 70 ሺህ ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ ይታወሳል።

ከእዚህ ከተጣለው የአቶሚክ ቦንብ መሣርያ ፍንዳታ የተረፈው ብቸኛው ሕንፃ የጄንባኩ ዶም በመባል የሚታወቀው የፈረሰ ሕንጻ ሲሆን ይህ ሕንጻ በሰው ልጆች ላይ እና በአጠቃላይ በሰብዓዊነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እና ውድመት ያስከተለ እጅግ አስከፊ የሆነ አደጋ መሆኑን ለማስታወስ፣ ይህ ስፍራ ዛሬ በሂሮሺማ የሰላም መታሰቢያ ፓርክ እምብርት ላይ ቆሞ ይታያል።

15 June 2022, 11:39