የጎአ ሀገረ ስብከት ካህን የሆኑት አባ ሳንፎርድ ሮድሪገስ ‘የአሲሲ ፍራንሲስ እና ካርሎ አኳይተስ ኢኮኖሚ ለወንድማማችነት’ ሽልማት በአሲሲ ተገኝተው ሲቀበሉ የጎአ ሀገረ ስብከት ካህን የሆኑት አባ ሳንፎርድ ሮድሪገስ ‘የአሲሲ ፍራንሲስ እና ካርሎ አኳይተስ ኢኮኖሚ ለወንድማማችነት’ ሽልማት በአሲሲ ተገኝተው ሲቀበሉ  

የጎአ ፕሮጀክት ለአደጋ ተጋላጭ ከሆኑ ወጣቶች ጋር በሰራው አመርቂ ሥራ ሽልማት መቀበሉ ተነገረ

የህንድ ግዛት በሆነችው ጎአ ከተማ ውስጥ ለአደጋ ተጋላጭ ከሆኑት እና ከጥቃት የተረፉ ወጣቶች እና ተጎጂዎች ጋር ዘርፈ ብዙ ስራዎች የሚሰራው የ ‘ሆፕ ፕሮጀክት’ (HOPE) 'የአሲሲ ፍራንሲስ እና ካርሎ አኳይተስ ኢኮኖሚ ለወንድማማችነት' ተብሎ የሚጠራ ሽልማት ማሸነፉ ተገልጿል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

እሑድ ግንቦት 17 ቀን 2017 ዓ.ም. “የአሲሲ ፍራንሲስ እና ካርሎ አኳይተስ ኢኮኖሚያዊ ወንድማማችነት” ተብሎ የሚጠራው ዓለም አቀፍ ሽልማት በጎረጎሳዊያኑ የ 2024-2025 ዓመት የሽልማት መርሃግብር አሲሲ በሚገኘው የቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን ውስጥ “HOPE” ለተሰኘው ፕሮጀክት መሸለሙ ተነግሯል።

የሆፕ ፕርጄክት ምንድነው (H.O.P.E.)
በእንግሊዘኛው ምህፃረ ቃል ‘ሆፕ’ (H.O.P.E.) ተብሎ የሚታወቀው ፕሮጀክት “ፈውስ፣ እድሎች፣ ጥበቃ እና ማጎልበት” የሚሉ ትርጉሞች በውስጡ ያዘለ ሲሆን፥ የተመሰረተውም የህንድ ግዛት በሆነችው ጎአ ውስጥ እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ ፕሮጄክት ከጊዜ ወደጊዜ እያደገ የመጣው የአካባቢው ካሪታስ ተነሳሽነቶች ጋር ተባብሮ በመስራቱ ሲሆን፥ ‘ቻይልድ ላይን’ በሚል ስያሜ በህፃናት ላይ በሚሰራቸው በርካታ ሥራዎችን ይታወቃል።

ይህ ፕሮግራም ለአደጋ የተጋለጡ ህጻናትን በተለይም በጣም ድሃ እና በጣም የተረሱ መንደሮችን ለማገዝ እና መልሶ ለማቋቋም የተዘጋጀ እንደሆነም ተገልጿል።

በ 2015 ዓ.ም. የምዕራባዊ ህንድ ግዛት የሆነው የጎአ ከተማ አስተዳደር ፕሮግራሙን ተቆጣጥሮት የነበረ ሲሆን፥ በዚህም ምክንያት ጥልቅ የሆኑ አለመግባባቶች በመፈጠራቸው፥ በካሪታስ ጎአ ውስጥ መስማት እና ማየት የተሳናቸው ሰዎች ላይ በሚሰራው የድጋፍ ሥራ ውስጥ የተሳተፉ ሰባት ወጣቶች እነዚህን አለመግባባቶች የሚፈታ ፕሮጀክት ለማቅረብ አብረው መስራት ጀምረው፣ በመጨረሻም ሆፕ ፕሮጄክትን መመስረታቸው ተገልጿል።

የፕሮጄችቱ ግብ የጥቃት ሰለባ የሆኑትን ወይም የተረፉትን እንዲሁም አንዳንዶቹ መስማት እና ማየት የተሳናቸው ዕድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ የሆናቸው ወጣቶችን ለመደገፍ ታልሞ የተመሰረተ ሲሆን፥ ፕሮጄክቱ ወጣቶች እርዳታ እና ድጋፍ ሲፈልጉ የሚደውሉበት የጥሪ ማዕከል እንዳለውም ጭምር ተገልጿል።

ኘሮጀክቱ ለሥነ-ምህዳር ተስማሚ የሆኑ እና በእጅ የሚሰሩ ምርቶችን ለማምረት የሚያስችል ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን የሚሰጥ ሲሆን፥ በዚህም በጠያቂዎች ፍላጎት መሰረት የተነደፉ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ የህክምና ቁሳቁሶችን ጨምሮ፥ የመጸዳጃ ቤት ወረቀት፣ ሳሙና፣ በእጅ የሚሰሩ እቃዎች እና ማሸጊያዎችን የመሳሰሉ ለአካባቢ ተስማሚ የሆኑ ምርቶችን ያመርታሉ።

እነዚህ ምርቶች በሃገሪቷ በጣም ታዋቂ ከሆኑት ውስጥ አንዱ የሆነው ታጅ ሆቴሎችን ጨምሮ፣ የተለያዩ አክሲዮኖች እና ገበያዎች የሆፕ ፕሮጀክት ምርቶችን በመውሰድ እና በመሸጥ ስኬታማ ሆነዋል።

ሆፕ (H.O.P.E.) ከአራት ፊደላትም በላይ ነው
የጎአ ሀገረ ስብከት ካህን የሆኑት አባ ሳንፎርድ ሮድሪገስ በአሲሲ ተገኝተው ሽልማቱን የተቀበሉ ሲሆን፥ ከሽልማቱ በሚገኘው 50,000 ዩሮ ተጠቃሚ በሚሆኑት 1,000 ወጣቶች ሥም ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

አሸናፊዎቹ የቁሳዊው ዓለምን የመካድ ምልክት እንዲሆን ቅዱስ ፍራንቺስኮ ልብሱን ሲያወልቅ የሚያሳይ ምስል ያለበት የአንገት ልብስ የተበረከተላቸው ሲሆን፥ አባ ሮድሪገስ “ሆፕ” የሚለው ቃል ከቃል በላይ እንዴት እንደሆነ ሲያብራሩ፥ “በወንድማማችነት አዲስ ኢኮኖሚ’ ሽልማት የንግዱን ዓለም በማሳተፍ የወደፊቱን ሰብዓዊ ክብር እና ነፃነት የሚገነባውን ሥነ-ምህዳር ለመደገፍ ለአደጋ ተጋላጭ ለሆኑ ሰዎች ተስፋ የሚሰጥ እንቅስቃሴ መሆኑን አብራርተዋል።

ካህኑ አክለውም የሆፕ ፕሮጀክት የሥራ ፈጠራ ሥልጠና “ወጣቶች ከህገ ወጥ አሰሪዎቻቸው ወይም ከጨቋኞቻቸው ራሳቸውን ችለው የሚኖሩበት መንገድ ስለሌላቸው ብቻ ተጎጂ በሆኑ አካባቢዎች እንዳይቆዩ ያደርጋል” ሲሉ አበክረው ተናግረዋል።

ቀጥሎ ያለው ነገር ምንድነው?
አባ ሮድሪገስ ሽልማቱ በዋትስአፕ መተግበሪያ በኩል የስልጠና እና የልማታዊ አስተዳደር መረጃ የሚጋራበት ዓለም አቀፍ የወንድማማችነት ማህበር እና “ለውጥ ፈጣሪዎች” ቡድን ለመፍጠር እንደሚያግዝ የተናገሩ ሲሆን፥ “ይሄንን ሽልማት ስንቀበል ዝም ብለን ለማስቀመጥ ሳይሆን፥ ወኪሎቹ ሆነን ልንሰራበት ነው” በማለት ከገለጹ በኋላ፥ የፕሮጄክቱ ምኞት በዚህ ተልዕኮ አማካኝነት የሚሰሩ “እያንዳንዱ የፈውስ ተግባር፣ እያንዳንዱ ህይወት አድን ተግባር እና የወንድማማችነት ጥረቶች’ በሙሉ ተስፋን በመላው ዓለም ሲያሰራጭ ማየት ነው ብለዋል።

ለክልላችን ተስፋ
ከዚህም ባሻገር በጎአ የሚገኙት የክልሉ ፕሬዝዳንት ይህንን ሽልማት መቀበል ለጎአ የተስፋ ምልክት መሆኑን ጠቁመው፥ የሆፕ ፕሮጀክት በድህነት ተስፋ መቁረጥ ላይ የማይቆም፥ ነገር ግን የሚፈታ የማይመስለውን ችግር ወደ ዘላቂ እና ሁለንተናዊ የልማት፣ የስራ እና የእድገት እድል ለመቀየር የሚያስችል ነው ብለዋል።

የሆፕ ፕሮጄክት ሽልማቱን መቀበሉን አስመልክተው አስተያየታቸውን ከሰጡት መካከል የጎአ እና የዳማን ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የምስራቅ ህንድ ሰባተኛው ፓትርያርክ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፊሊፔ ኔሪ አንቶኒዮ በሽልማቱ ሥነ ስርዓት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአሲሲው ሊቀ ጳጳስ ብጹእ አቡነ ዶሜኒኮ ሶሬንቲኖ በበኩላቸው የሽልማቱን አስፈላጊነት ገልፀው “በጎ አድራጎት ፖለቲካዊ በጎ አድራጎት በሚሆንበት ጊዜ ጠንካራ፣ የበለጠ ቀልጣፋ እና እውነተኛ ሊሆን እንደሚችል ይህ ሽልማት ጥሩ ማሳያ ነው ብለዋል።
 

27 May 2025, 14:41