ባለ ጠጋው ሰው እና ድኻው አልዓዛር ባለ ጠጋው ሰው እና ድኻው አልዓዛር 

የጥቅምት 02/2018 ዓ.ም 26ኛው መደበኛ እለተ ሰንበት ንባባት እና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የእለቱ ንባባት

1.    ት. አሞፅ 6፡1.4-7

2.    መዝሙር 145

3.    1ጢሞ. 6፡11-16

4.    ሉቃስ 16፡19-31

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል

ባለ ጠጋው ሰው እና ድኻው አልዓዛር

“በሐምራዊና በክት ልብስ የሚሽቀረቀር አንድ ሀብታም ሰው ነበረ፤ ዕለት ዕለትም እየተመቸው በቅንጦት ይኖር ነበር። 20አልዓዛር የሚባል አንድ ድኻ ሰው ደግሞ በቁስል ተወርሶ በደጁ ተኝቶ ነበር፥ ከሀብታሙም ማዕድ ከሚወድቀው ፍርፋሪ ለመጥገብ ይመኝ ነበር፤ ውሾች እንኳ መጥተው ቁስሎቹን ይልሱ ነበር። ድኻውም ሞተ፤ መላእክትም ወደ አብርሃም እቅፍ ወሰዱት፤ ሀብታሙም ደግሞ ሞተና ተቀበረ። በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ፥ አልዓዛርንም በእቅፉ አየ። እርሱም እየጮኸ ‘አብርሃም አባት ሆይ! ማረኝ፤ በዚህ ነበልባል እሠቃያለሁና የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ላክልኝ፤’ አለ። አብርሃም ግን ‘ልጄ ሆይ! አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም ነገሮችህን እንደተቀበልህ አስብ፤ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል፤ አንተም ትሠቃያለህ። ከዚህም ሁሉ በላይ ከዚህ ወደ እናንተ ማለፍ የሚፈልጉ እንዳይችሉ፥ ወዲያ ያሉ ደግሞ ወደ እኛ እንዳይሻገሩ በእኛና በእናንተ መካከል ታላቅ ገደል ተደርጎአል፤’ አለ። እርሱም ‘እንግዲያውስ፥ አባት ሆይ! ወደ አባቴ ቤት እንድትልከው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው’ አለ። አብርሃም ግን ‘ሙሴና ነቢያት አሉላቸው፤ እነርሱን ይስሙ፤’ አለው። እርሱም ‘አይደለም፥ አብርሃም አባት ሆይ! ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሓ ይገባሉ፤’ አለ። ‘ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ሰው ቢነሣ አያምኑም፤’ አለው።”

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

ውድ ወንድሞቼ እና እህቶቼ፣

የኢየሱስ ቃላቶች እግዚአብሔር ዓለምን በእያንዳንዱ ጊዜ እና በሁሉም ቦታ እንዴት እንደሚመለከት ይገልጽልናል።በወንጌል (ሉቃስ 16፡19-31) ውስጥ እንደ ተጠቀሰው የእግዚአብሔር ዓይኖች ድሀና ባለ ጠጋ ሰው እንደሚመለከቱ ሰምተናል፥ አንዱ በራብ ሲሰቃይ እና ሲሞት ሌላውም በፊቱ በቁንጣን ተይዞ፣ ያማረ ልብስ በእየለቱ ሲለብስ፣ እና ሲበላ ሲጠጣ፣ የሌላኛውን ቁስል ውሾች ይልሱ ነበር (ሉቃ. 16፡19-21)።  ነገር ግን ጌታ የሰዎችን ልብ ይመለከታል፣ እና በዓይኖቹ በኩል፣ የተቸገረውን እና ግዴለሽ የሆነውን ለይተን ማወቅ እንችላለን። ከቤቱ ደጃፍ ማዶ በፊቱ ያለው አልዓዛር ተረሳ፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ወደ እርሱ ቅርብ ነው ስሙንም ያስታውሳል። በሌላ በኩል ደግሞ በብዛት በቅንጦት የሚኖረው ሰው ስም -አልባ ነው፣  ምክንያቱም ባልንጀራውን በመርሳት እራሱን አጥቷል። በልቡ አሳብ ውስጥ ስምጥ ብሎ፣ በምድራዊ ነገሮች የተሞላ እና ፍቅር አልባ ሰው ነበር። ንብረቱ ጥሩ ሰው አያደርገውም።

ክርስቶስ የሚነግረን ታሪክ፣ በሚያሳዝን ሁኔታ፣ ዛሬ በጣም ጠቃሚ ነው። በዛሬው ዓለም ሀብት ወይም ድሎት ደጃፍ ላይ በጦርነት እና በብዝበዛ የተጠቁ የመላው ህዝቦች ሰቆቃ ቆመዋል። ባለፉት መቶ ዘመናት ጊዜያት ውስጥ ምንም የተለወጠ ጉዳዩ ያለ አይመስልም፣ ፍትህን ከዘነጋው ስግብግብነት፣ ለጋስነትን ከሚረግጥ ትርፍ በፊት እና የድሆችን ስቃይ ከማየት ይልቅ ባለጠግነት ከሚመርጡ ሰዎች ፊት ስንት አልዓዛሮች ይሞታሉ! ሆኖም ወንጌሉ የአልዓዛር ስቃይ ወደ ፍጻሜው እንደሚመጣ አረጋግጦልናል። ህመሙ የሚያበቃው የሀብታሙ ፈንጠዝያ እንዳበቃ ነው፣ እናም እግዚአብሔር ለሁለቱም ፍትህን ይሰጣል፡- "ድሀው ሞተ መላእክቱም ወደ አብርሃም ጎን ወሰዱት፤ ባለ ጠጋው ደግሞ ሞቶ ተቀበረ" (ሉቃስ 16፡22)። ቤተክርስቲያን ልባችን ይመልስ ዘንድ ይህን የጌታን ቃል ሳትታክት ታውጃለች።

ውድ ወዳጆቼ፣ በአስደናቂ አጋጣሚ፣ ይህ የወንጌል ክፍል በቅዱስ የምሕረት ዓመት በካታኪስቶች ኢዮቤልዩ ወቅት ታውጇል። የቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ለኢዩቤሊዩ በዓል ወደ ሮም ለመጡ ምዕመናን ባደረጉት ንግግር እግዚአብሔር ለእኛ ሲል እኛን ከክፉ ነገር ሁሉ ለማዳን አንዲያ ልጁን ሰጥቶን አድኖናል ብለው ነበር። የእግዚአብሔር የማዳን ሥራ የተልእኮአችን መጀመሪያ ነው፣ ምክንያቱም እራሳችንን ለሁሉም አገልግሎት እንድንሰጥ ስለሚጋብዘን ነው። የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ለካቴኪስቶች እንዲህ ብሏቸው ነበር፣  ይህ ማእከል ነው "ሁሉም ነገር የሚሽከረከርበት፣ ይህ የሁሉንም ነገር ሕይወት የሚሰጥ፣ ይህ የልብ ምት የፋሲካ አዋጅ ነው፣ የመጀመሪያው አዋጅ፥ ጌታ ኢየሱስ ተነስቷል፣ ጌታ ኢየሱስ ይወዳችኋል፣ እናም ነፍሱን ለእናንተ ሰጥቷል፣ ሕያው ሆኖ የተነሳው እርሱ ለእናንተ ቅርብ ነው፣ እናም በየቀኑ ይጠብቃችኋል ብለው። እነዚህ ቃላት በወንጌል ውስጥ በሀብታሙ ሰው እና በአብርሃም መካከል የተደረገውን ውይይት እንድናሰላስል ይረዱናል። የሀብታሙ ሰው ወንድሞቹን ለማዳን ያቀረበው ልመና ለእኛ የተግባር ጥሪ ይሆናል።

ባለጠጋው ሰው ከአብርሃም ጋር ሲነጋገር፡ “ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሓ ይገባሉ" (ሉቃስ 16፡30) በማለት ጮኸ። አብርሃም እንዲህ ሲል ይመልሳል፡- “ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ሰው ቢነሣ አያምኑም፤’ አለው” (ሉቃስ 16፡31)። እንግዲህ አንዱ ከሙታን ተለይቶ ተነስቷል፡ ኢየሱስ ክርስቶስ። ስለዚህ የቅዱሳት መጻሕፍት ቃላቶች ኅሊናችንን ለማንቃት እንጂ ሊያሳዝኑን ወይም ተስፋ ሊያስቆርጡን አይፈልጉም። ሙሴን እና ነቢያትን ማዳመጥ ማለት የእግዚአብሔርን ትእዛዛት እና ተስፋዎች ማስታወስ ማለት ነው፣ ከእሱ መንፈሳዊ ፀጋ ማንም የተገለለ አይደለም። ወንጌሉ የሁሉም ሰው ሕይወት ሊለወጥ እንደሚችል ያሳውቀናል፣ ምክንያቱም ክርስቶስ ከሙታን በመነሳቱ ነው። ይህ ክስተት የሚያድነን እውነት ነው፥ ስለዚህም መታወቅና መታወጅ አለበት። ግን ያ በቂ አይደለም መወደድም አለበት። ፍቅር ልባችንን ለእግዚአብሔር ቃል እና ለባልንጀራችን በር በመክፈት ይለውጠናልና ወንጌልን እንድንረዳ የሚያደርገን ፍቅር ነው።

በዚህ ረገድ፣ እንደ ካታኪስቶች፣ እናንተ የእሱ ምስክሮች የሆናችሁ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት ናችሁ። የአገልግሎታችሁ ስያሜ "ካትቼይን" ከሚለው የግሪክኛ ቋንቋ ግስ የመጣ ሲሆን ትርጉሙም “ጮክ ብሎ ማስተማር፣ ማስተጋባት” ማለት ነው። ይህ ማለት ካታኪስት ቃሉን የምያስተጋባ ሰው ነው - እሱ ወይም እሷ በራሱ ህይወት የሚናገሩት ቃል ማለት ነው። ስለዚህ የመጀመሪያዎቹ ካታኪስቶች ወላጆቻችን ናቸው፡ መጀመሪያ ያነጋገሩን እና እንድንናገር ያስተማሩን። የአፍ መፍቻ ቋንቋችንን እንደተማርን ሁሉ የእምነት አዋጅን ለሌላ ሰው ሊሰጠን አይችልም፣ የምንኖርበት ቦታ፣ ከሁሉም በላይ በቤታችን፣ በቤተሰብ ጠረጴዛ ዙሪያ ይከሰታል። ድምጽ ሲኖር፣ ምልክት ወደ ክርስቶስ የሚመራ ፊት፣ ቤተሰብ የወንጌልን ውበት ይለማመዳል።

ሁላችንም እንድናምን ተምረናል፣ ከኛ በፊት ባመኑት ምስክርነት የተነሳ ማለት ነው። ከልጅነት፣ ከጉርምስና ፣ ከወጣትነት ፣ ከጎልማሳነት እና ከእርጅና ጀምሮ፣ በዚህ የኢዮቤልዩ ጉዞ ላይ እንዳደረጋችሁት ሁሉ በዚህ የህይወት ዘመን ጉዞ እየተካፈሉ ካታኪስቶች በእምነታችን ጉዞ ያጅቡናል። ይህ ተለዋዋጭነት መላውን ቤተ ክርስቲያን ያካትታል። የእግዚአብሔርን ሰዎች ወንዶችንና ሴቶችን ወደ እምነት ጎዳና ሲያመጡ፣ “የእውነታዎች እና የተነገሩትን ቃላት እንድንረዳ ያደርጋል። ይህ የሚሆነው አማኞች ባደረጉት ማሰላሰል እና ጥናት ነው፣ እነዚህን ነገሮች በልባቸው በሚያከብሩ (ሉቃስ 2፡19፣ 51 የመልከቱ) በሚለማመዱበት መንፈሳዊ እውነታዎች ጥልቅ ግንዛቤ እና በቃሉ የእውነት ስጦታ የተቀበሉ ሰዎች በመስበክ ነው።  በዚህ ሕብረት ውስጥ፣ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ  ከግለኝነት እና ከክርክር የሚጠብቀን “የጉዞ መመሪያ መጽሐፍ” ነው፣ ምክንያቱም የመላው የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን እምነትን ይመሰክራል። እያንዳንዱን አማኝ በሐዋርያዊ እንክብካቤ ተግባራት ጥያቄዎችን በማዳመጥ፣ በትግሎች ውስጥ በመካፈል እና በሰው ልጅ ህሊና ውስጥ ለሚኖረው የፍትህ እና የእውነት ፍላጎት በማገልገል ይተባበራል።

ካታኪስቶች የሚያስተምሩት እንደዚህ ነው - በጣሊያንኛ ቃል በቃል፣ “ምልክት በመተው”። እምነትን ስናስተምር መመሪያን ብቻ ሳይሆን የሕይወትን ቃል በልባችን እናስቀምጣለን፣ ይህም የመልካም ሕይወት ፍሬ እንዲያፈራ ነው። እንዴት ጎበዝ ካታኪስት መሆን እንዳለበት ለጠየቀው ዲያቆን ዲዮግራቲያስ፣ ቅዱስ አውግስጢኖስ እንዲህ ሲል መለሰ፡- “የሚሰማህ በማዳመጥ እንዲያምን፣ በማመን ተስፋ እንዲያደርግ፣ እናም ተስፋ በማድረግ ፍቅርን እንዲሰጥ ሁሉንም ነገር ግለጽ" ሲል መልሶለት ነበር።

ውድ ወንድሞች እና እህቶች፣ ይህንን ግብዣ በልባችን እናድርገው! ማንም የሌለውን መስጠት እንደማይችል እናስታውስ። በወንጌል የተጠቀሰው ባለጸጋ ለአልዓዛር ምጽዋትን ቢሰጥ ኖሮ ለድሆች ብቻ ሳይሆን ለራሱም መልካም ያደርግ ነበር። ያ ስም የለሽ ሰው እምነት ቢኖረው ኖሮ እግዚአብሔር ከሥቃይ ሁሉ ያድነው ነበር። ነገር ግን ከዓለማዊ ሀብት ጋር ያለው ቁርኝት የእውነተኛውን እና ዘላለማዊውን ጥቅም ተስፋ ነፍጎታል። እኛም በስግብግብነትና በግዴለሽነት ስንፈተን በዛሬው ጊዜ ያሉት አብዛኞቹ “አልዓዛር” የኢየሱስን ቃላት ያስታውሱናል። በተለይ በዚህ ኢዮቤልዩ ወቅት፣ ለሁሉም የመንፈሳዊ ለውጥ ማምጫ ጊዜ እንዲሆንና  የይቅርታ ጊዜ፣ ለፍትህ ቁርጠኝነት እንዲኖረን እና ለሰላም ልባዊ ምኞት እንዲኖረን ለእኛ ውጤታማ ካታኪስቶች ሆናችው እንደምታገለግሉን እርግጠኞች ነን።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ አባ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

 

11 Oct 2025, 11:50