ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ የተላለፈ የሐዘን መግለጫ
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤጥቅምት አጋማሽ 2018 ዓ.ም. በኦሮሚያ ክልል ምዕራብሀረርጌ ሚደግዱ አስተርዮ ማርያም ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ በተፈጸመው ግድያ የካቶሊካውያን ሕይወት ማለፉን እና ንብረት መቃጠሉን በታላቅ ሐዘን ሰምተናል። በተጨማሪም በኦሮሚያ ክልል በአርሲ ዞን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምዕመናን ላይ ተመሳሳይ ግድያ መፈጸሙን ተቋማቱ ባወጡት መግለጫ ሰምተናል።
ቤተ ክርስቲያናችን ይህን ዓይነቱን ኢ-ሰብዓዊ ተግባር አጥብቃ ታወግዛለች፤ በመሆኑም የዜጎችን ሰላም እና ደህንነት ለማረጋገጥ መንግሥት አስቀድሞ አስፈላጊውን የሕግ ማስከበር ሥራ እንዲሠራ ቤተ ክርስቲያናችን ጥሪዋን ታቀርባለች።
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ በዚህ እጅግ አሳዛኝ ተግባር ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖቻችን ዘለዓለማዊ እረፍትን ያገኙ ዘንድ እየጸለየች የተሰማንን ሐዘን ለመላው ካቶሊካውያን፣ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ለተጎዱ ቤተሰቦች ፈጣሪ እውነተኛ መጽናናት እንዲሰጥልን ከልብ እንመኛለን።
04 Nov 2025, 12:03