በቤተ ክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ የተካሄደው የቬሮና ፌስቲቫል በቤተ ክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ የተካሄደው የቬሮና ፌስቲቫል 

ር. ሊ. ጳ. ፍራንችስኮስ ሌሎችን በፍቅር እና በማስተዋል መርዳት እንደሚገባ አሳሰቡ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ የቤተ ክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ 13ኛ ዓመት መታሰቢያ በዓል በማስታወስ ባስተላለፉት መልዕክት፥ ካቶሊካዊ ምዕመናን ሌሎችን በማስተዋል እና በፍቅር እንዲረዱ በማለት ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

በጣሊያን ዓመታዊው የቤተ ክርስቲያን ማህበራዊ አስተምህሮ ፌስቲቫል በቬሮና ከተማ ዓርብ ኅዳር 14/2016 ዓ. ም. ተከፍቷል። ዘንድሮ የተከበረው ፌስቲባሉ፥ “#soci@ally free” (#soci@lmente liberi) “በማኅበራዊነቱ ነጻ የሆነ” በሚል መሪ ጭብጥ ላይ ያተኮረ እንደነበር ታውቋል።

በእንግሊዝኛው ቃል “ሶሻሊ” በሚለው ቃል ውስጥ ዲጂታል የመገናኛ ሥርዓትን የሚትገልጽ የ “አት” ምልክት፥ ዛሬ ላይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የሄደውን በተለይም የዲጂታል ባሕል በግል ሰቦች እና በማኅበረሰቦች መካከል ባለው ግንኙነቶች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደሩን አስረድተዋል።

“ምልክቱ ከሌሎች ሰዎች ጋር ያለውን መቀራረብ እና መገናኘት ከማመልከት በተጨማሪ፥ በአንድ ሰው ልብ ውስጥ ያለውን ምስጢር ለመጠበቅ ያለውን ነፃነትን የሚገልጽ ነው” ሲሉ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አብራርተዋል። ማኅበራዊ ሚዲያ በፈተና የምንወድቅበት “ወጥመድ” መሆን እንደሌለበት፥ ይልቁንም የሰዎችን የጋራ አንድነት ለመጠበቅ ያለመ ማድረግ አለብን ብለዋል።

የግል ተሳትፎ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ በማቴ. ምዕ. 14 ላይ እንደተጻፈው፥ ኢየሱስ ክርስቶስ አምስት ሺህ ሰዎችን በአምስት እንጀራ እና በሁለት ዓሣ ብቻ እንደመገባቸው በማስታወስ፥ የኢየሱስ ክርስቶስን አስተምህሮ በማጉላት አስተምህሮዎቹ መስዋዕትነትን የሚጠይቁ ቢሆኑም በችግር ወቅት በግል ወደ ሕዝቡ ዘንድ የመጣውን የእግዚአብሔር አብ ዕርዳታ የሚያስታውሰን መሆኑን ገልጸዋል።

“የኢየሱስ ክርስቶስ መልዕክት እውነት ነው” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ፥ ምክንያቱም እርሱን ለሚሰሙት ሰዎች ባለው ፍቅር ላይ የተመሠረተ ስለ ሆነ ነው” ብለዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ ሰዎችን ካስተማራቸው በኋላ የሚያፈልጋቸውን አውቆ የሚበላ ነገር እንዳሟላላቸው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ አስታውሰዋል።

በፍቅር የተሞላ እና አስተዋይነት ያለው ተሳትፎ

ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻውን እንዳልሆነ ነገር ግን በእርሱ ሥራ ውስጥ እንዲተባበሩ ከተጠሩት ደቀ መዛሙርት ጋር እንደሚሠራ፥ ሌሎችን በማስተዋል እና በፍቅር እንዲያግዝ ደቀ መዝሙሩ የተጠራበት ነፃነት እንደሆነ ቅዱስነታቸው አስረድተው፥ “የሚተባበረውን ሰው በጥቂቱም ቢሆን የማያካትት የወንጌል ስጦታ የለም” በማለት አክለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ዓመታዊውን በዓል የሚሳተፉት በሙሉ ለጋራ ጥቅም የሚሆኑ  ተግባራትን እና ውጥኖችን ለማሳደግ በጥበብ በመሥራት “soci@ally free” ወይም በማኅበራዊነቱ ነጻ የሆነ የሚለውን ጭብጥ ወደ ተግባር መተርጎም እንደሚችሉ ተስፋ በማድረግ መልዕክታቸውን ደምድመዋል።

 

25 Nov 2023, 16:43