ITALY-VATICAN-POPE-HEALTH

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ጤናቸው በተረጋጋ ሁኔታ ላይ መሆኑ ተገለጸ!

የቅድስት መንበር የዜና ማሰራጫ ጽ/ቤት ረዕቡ የካቲት 12/2017 ዓ.ም አመሻሽ ላይ ባወጣው ዘገባ እንዳመለከተው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የጤና ሁኔታ እየተሻሻለ መምጣቱን የገለጸ ሲሆን በዛሬው እለት ከቅርብ ግብረአበሮቻቸው ጋር መገናኘት ችለዋል፣ የጣሊያን ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ቅዱስነታቸውን እንደ ጎበኙም ተገልጿል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የቅድስት መንበር ኅትመት ጽ/ቤት ረቡዕ የካቲት 12/2017 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ "የቅዱስ አባታችን የጤና ሁኔታ የተረጋጋ ነው። በሕክምና ባለሙያዎች የተገመገሙት የደም ምርመራዎች፣ በተለይም በመተንፈሻ የአካል ክፍላቸው ላይ ትንሽ መሻሻል ያሳያል" ሲል መግለጫው አክሎ ገልጿል።

 

21 Feb 2025, 10:22