ር.ሊ.ጳ ሊዮ ተጽዕኖ ፈጣሪዎች በሰዎች ልብ መካከል ግንኙነት እንዲፈጠር ማገዝ አለባቸው አሉ!
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በቅዱስ ጴጥሮስ ባዚሊካ ውስጥ ለዲጂታል ሚስዮናውያን እና ለካቶሊክ ተፅዕኖ ፈጣሪዎች የኢዮቤልዩ አካል በመሆን መስዋዕተ ቅዳሴ ለመካፈል ከዓለም ዙሪያ በተውጣጡ ወጣቶች ተሞልቷል። መስዋዕተ ቅዳሴውን የመሩት የመጀመርያ የስብከተ ወንጌል ሥርጭት እና አዲስ ልዩ አብያተ ክርስቲያንትን ጉዳይ የሚመለከተው የቅድስት መንበር ዋና ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲና ሉዊስ አንቶኒዮ ታግሌ እንደ ነበሩ ተገልጿል።
በስብከታቸው ካርዲናል ታግሌ “ተፅእኖ” በሚለው ቃል ላይ እና በትክክል ለካቶሊኮች እና ለዲጂታል ሚሲዮናውያን ይህ ቃል ምን ማለት እንደሆነ አስረድተዋል።
ዛሬ 'ተጽዕኖ' ምን ማለት ነው?
ካርዲናል ታግሌ ሁሉም ተጽኖ ፈጣሪ እንደሆኑ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፣ እናም በተመሳሳይ ጊዜ፣ ሁሉም ሰው ተጽዕኖ ይደረግበታል። "የእለት ተእለት ህይወት የተዘበራረቁ ተፅእኖዎች ውጤት ነው" ሲሉ ካርዲናል ተናግረዋል፣ በቤተሰቦቻችን፣ በአካባቢያችን፣ በትምህርት ቤቶች እና በሌሎች ማህበራዊ ተቋሞቻችን በየጊዜው ተጽእኖ እየደረሰብን መሆኑን ጠቁመዋል።
እነዚህ የሕይወት ገፅታዎች ሲበላሹ እነሱ ደግሞ በማንነታችን እና በምንፈጥረው ማህበረሰብ ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ ያሉት ካርዲናል ታግሌ ከእዚያ በላይ “ምድርና አካባቢው በእኛ ላይ ተጽዕኖ በሚያሳድሩበት ጊዜ የእኛ እንቅስቃሴ በፕላኔቷ ላይም ተጽዕኖ ያሳድራል" ሲሉ መናገራቸውም ተገልጿል።
ይህ የኢዮቤልዩ ዝግጅት “በዘመናችን ያለው ዓለማችን ሊፈጽመው የሚፈልገውን ተጽዕኖ እንዲቃኝ የሚያደርገውን ዓላማ ለመመርመር” ግብዣ እንደሆነ አጥብቆ ተናግሯል። በአለም ላይ ማየት የምንፈልገው ለውጥ በሌሎች ላይ ተጽእኖ ለማድረግ ከምንመርጥበት እና ከጀርባው ካለን ተነሳሽነት ጋር በቀጥታ የተያያዘ ነው።
አንዳንዶች ሰዎችን ለማማለል የውሸት ማስታወቂያ ይጠቀማሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ አስፈራርተው ገንዘብ ወይም ጉቦ ይቀበላሉ። ሌሎች ደግሞ በዙሪያቸው ባሉት ሰዎች ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ ጦርነትን፣ የቦምብ ጥቃትን፣ ሰው ሰራሽ ረሃብን ይጠቀማሉ ሲሉ ተናግረዋል።
ተጽዕኖ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ነው።
ብፁዕ ካርዲናል ታግሌ ለጥያቄው መልስ ለመስጠት ወደ እለቱ ንባብ ሐሳባቸውን አዙረው 'ተጽዕኖ' ማለት ምን ማለት ነው'? የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ ጥረት ያደርጉ ሲሆን ከእዚህ ጋር ተያያዢነት ያለው ጽሑፍ ወይም ኢሜል ከመላክ ይልቅ፣ እግዚአብሔር ልጁን እንደላከን ጠቁሟል።
የወንጌል መልእክት ኢየሱስ በፍቅሩ ተጽዕኖ እንዲያሳድርብን እንድንፈቅድ ያበረታታናል፣ በዚህም ለሌሎችን በጎ ነገር ማድረግ እንችላለን ያሉት ካርዲናል ታግሌ በቦታው የተገኙትን ምዕመናን “በኢየሱስ እና በመንፈስ ቅዱስ ያለው የእግዚአብሔር ፍቅር የተለያዩ መርዛማ ተጽእኖዎች ወደ ሰው ልብ እና ወደ ማህበረሰቡ ውስጥ እንዳይገቡ ተከላከሉ” ሲሉ መክረዋል።
የጳጳስ ሊዮ የሰላም ጥሪ
በቅዳሴው መጨረሻ ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ባዚሊካ ውስጥ ለተገኙት ወጣቶች በሦስት ቋንቋዎች በስፓኒሽ፣ በእንግሊዝኛ እና በጣሊያንኛ ንግግር አድርገዋል። በመልእክቱ “በጠላትነት እና በጦርነት በተበታተነው በዚህ ዘመን ምን ያህል ሰላም ያስፈልገናል” በማለት አጽንኦት በመስጠት ሁከት እንዲቆም በድጋሚ ጥሪ አቅርቧል።
ሰላምን ማወጅ የቤተክርስቲያኗም ሆነ በሮም ለኢዮቤልዩ የተሰበሰቡ ሁሉ ተልእኮ መሆኑን ደጋግመው ተናግረዋል። "በጦርነት አሰቃቂ ቦታዎች እና በባዶ ልብ ውስጥ የመኖርን ትርጉም እና የውስጥ ጣዕም፣ ለመንፈሳዊ ህይወት ጠቃሚ ይሆን ዘንድ ሰላምን በየቦታው መፈለግ፣ ማወጅ እና ማጋራት ያስፈልጋል " ሲሉ የተናገሩት ቅዱስነታቸው ስለዚህ፣ ዛሬ፣ ከመቼውም ጊዜ በላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አክለው እንደ ተናገሩት፣ ይህንን መልእክት እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ ለማዳረስ ዲጂታል ሚስዮናውያን አስፈላጊ መሆናቸውን አሳስበዋል።
ባህላችን ሰብዓዊ ሆኖ ይኑር
ወደዚህ ተልእኮ ለሚገቡ ሰዎች የሚገጥማቸው ልዩ ፈተና ሁል ጊዜ በበይነ መረብ መስመር ላይ በሚያገኙት እያንዳንዱ ሰው ውስጥ “መከራ የደረሰበትን የክርስቶስን ሥጋ” መፈለግ ነው ያሉት ቅዱስነታቸው ራሳችንን በቴክኖሎጂ ማህበረሰብ እና ባህል ውስጥ እንደምናገኝ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ተጽዕኖ ፈጣሪዎቹን “ይህ ባህል ሰብዓዊ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ የኛ እና የእያንዳዳችሁ ድርሻ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ሳይንስና ቴክኖሎጂ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን ውስጥ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ቢሆንም እንኳ “የሌሎችን ክብር ለመጉዳት” ሰው ሠራሽ ነገር ማድረግ የለበትም። ካቶሊኮች ተፅዕኖ ፈጣሪዎች እና ዲጂታል ሚስዮናውያን እንደመሆናችን መጠን የእኛ ተልእኮ "ክርስቲያናዊ ሰብአዊነትን" በባህላችን ውስጥ ማስተዋወቅ ነው ብለዋል።
ሂዱ እና የወዳጅነት በይነ መረቦችን ጠግኑ
በታሪክ ውስጥ፣ ብዙ የለውጥ ጊዜያት ነበሩ ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ቤተክርስቲያን መቼም ቢሆን በዚህ ረገድ ታዛቢ ሆና መኖር አለመረጠችም ያሉ ሲሆን በቴክኖሎጂ በተሞላው የዛሬው ባህል፣ ተግዳሮቱ “የዘመናችን አስተሳሰብና ቋንቋ ለማዳበር፣ ለፍቅር ድምፅ የሚሰጥ ይሆን ዘንድ” በጋራ መሥራት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ይዘቱን በቀላሉ ከመፍጠር በላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንዳሉት ከሆነ እነዚህ ዲጂታል ሚስዮናውያን በሰው ልጅ ልቦች መካከል ግንኙነትን እንዲፈጥሩ አሳስበዋል። ይህ ወደ ሌላ ጥሪ ይመራል - የተበጣጠሱ መረቦችን ወደ መጠገን ይመራናል፣ የግንኙነት መረቦች ፣ የፍቅር ፣ በነፃ የተቀበልነውን በነፃ ወደ መስጠት፣ ጥልቅ የሆነ ጓደኝነትን ወደ መመስረት ይመራናል ማለታቸው ተገልጿል።
ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዩ “ከራሳችን በላይ ለሌሎች ክፍት የሆነ ቦታ በልባችን ውስጥ ማዘጋጀት፣ ምንም ‘የማጣሪያ አረፋ’ የደካሞችን ድምጽ ሊያጠፋው አይችልም” የሚለውን የግንኙነት መረቦች እንድንጠግን ተጠርተናል። በዚህ አማካኝነት አንድ ነጠላ የእግዚአብሔር መረብ መፍጠር እንችላለን ሲሉ ተናግረዋል።
በማጠቃለያው ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በቦታው የተገኙትን ወጣቶች ለሥራቸው ሁሉ አመስግነው በዲጂታል መንገድ ወደ ምድር ጫፍ ለመድረስ በሚያደርጉት ጉዞ እንዲቀጥሉ አበረታቷቸዋል።
