ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቫቲካን ከባህሬን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ልዑል ሳልማን ቢን ሃማድ አል ካሊፋ በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቫቲካን ከባህሬን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ልዑል ሳልማን ቢን ሃማድ አል ካሊፋ በተገናኙበት ወቅት   (@VATICAN MEDIA)

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ከባህሬን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ልዑል ጋር በቫቲካን ተገናኙ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቫቲካን ከባህሬን ጠቅላይ ሚኒስትር እና ልዑል ሳልማን ቢን ሃማድ አል ካሊፋ ጋር መገናኘታቸው ተገለጸ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቫቲካን ሰኞ እለት መስከረም 19/2018 ዓ.ም የባህሬን ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑት ከልዑል ሳልማን ቢን ሃማድ አል ካሊፋ ጋር በግል መገናኘታቸው የተገለጸ ሲሆን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ጋር ያደረጉትን ውይይት ተከትሎ የቅድስት መንበር የዜናና ኅትመት ክፍል ባወጣው መግለጫ እንዳመለከተው፣ ልዑሉ የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ከሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊንን ጨምሮ ቫቲካን ከአለም መግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ምክትል ጸሐፊ የእኔታ አቡነ ሚሮስላው ስታኒስላው ዋካውስኪ ጋር ተገናኝተዋል።

መግለጫው በቅድስት መንበር እና በባህሬን መንግሥት መካከል ስላለው መልካም የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት በተመለከተ ከስምምነት መድረሳቸውን ያመላከተ ሲሆን “ከቫቲካን ዋና ጸኃፊ ጋር የነበራቸውን ቆይታ እና መልካም ውይይቶች” አድናቆት ተችሯቸዋል።

"ለባህሬን መንግሥት በሃይማኖቶች መካከል ውይይትን እና በመንግሥት ውስጥ ያሉ የተለያዩ ሃይማኖቶች በሰላም አብሮ መኖርን ለማስፋፋት የምያስችል ፖሊሲ ትኩረት ተሰጥቷል" ሲል መግለጫው አክሎ ያትታል።

በመጨረሻም መግለጫው “በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን ጦርነት በአስቸኳይ  ማስቆም እና በአገሮች መካከል ሰላም እንዲሰፍን ቁርጠኝነት እንደምያስፈልግ እና የመሳሰሉት በርካታ የጋራ ጉዳዮች ተነስተው ውይይት እንደተደረገባቸው" አክሎ ገልጿል።

 

29 Sep 2025, 16:16