ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (ANSA)

ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ጥላቻንና ዓመፅን እናሸንፍ ማለታቸው ተገለጸ!

ሐሙስ መሰከረም 10/2018ዓ.ም ላይ በይፋ የሚለቀቀው "ሊዮ 14ኛ የዓለም ዜጋ፣ የ 21ኛው ክፍለ ዘመን ሚስዮናዊ" ለተሰኘው መጽሃፍ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ለጋዜጠኛ ኤሊዝ አን አለን ከሰጡት ቃለ ምልልስ የተቀነጨቡ ጹሑፎች ታትመዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የጳጳሱ ሚና እና ብዙ ቃል ኪዳኖች የስልክ ጥሪ ከማድረግ ጀምሮ የህዝብ ገጽታ እና ከዚያም ሰላም የተሰኙ ገጽታዎች ቅዱስነታቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ከታዩበት ጊዜ ጀምሮ ለሰላም ያቀረቡት ጥሪ በዚህ ዓለም በግጭቶች እና “ከንቱ ግድያዎች” በተሰበረ አለም ውስጥ “ብቸኛ መልስ” ነው። እናም ከዚያ፡ ለንግግር ያቀረቡት ጥሪ፣ ሲኖዶሳዊነት እና ለዋልታ ረገጥ አስተሳሰቦች እንደ “የመርዝ ማርከሻ" ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል፣ በተጨማሪም በመጨረሻም የአሜሪካ/የፔሩ የማንነት ሁኔታ እና በመጪው የዓለም ዋንጫ ወቅት ውይይት እና ንግግር የማድረግ አስፈላጊነትን አጉልተው ለማሳየት ቀን ከሌሊት በመትጋት ላይ ናቸው።

 ሁለት መቶ ስልሳ ሰባተኛው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ባደረጉት ቃለ ምልልስ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ከክሩክስ ጋዜጠኛ ኤሊዝ አን አለን ጋር በነበራቸው ቆይታ በቅድመ-እይታ ከተገለጹት ተከታታይ ክፍሎች ውስጥ የተወሰኑት እነዚህ ናቸው።

ውይይቱ በከፊል በካስቴል ጋንዶልፎ እና በእርሳቸው መኖሪያ ቤት ውስጥ ከትደረጉት ቃለ ምልልሶች መካከል የሚከተሉት ይገኙባቸዋል።

በሰሜን አሜሪካ እና በፔሩ መካከል

እሑድ መስከረም 04/2018 ዓ.ም የቅዱስ አባታችን 70ኛ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ፣ የቃለ ምልልሱ የተለያዩ ክፍሎች መታተም ስለ ሮበርት ፍራንችስኮስ ፕሪቮስት፣ (ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ)፣ ከሰሜን አሜሪካ ከትውልድ አገራቸው እና ከፔሩ የሚስዮናዊነት የእንቅስቃሴያቸው ምድር ጋር ካለው ትስስር ጀምሮ አዲስ ዝርዝሮችን ያሳያል።

“እኔ በግልጽ አሜሪካዊ ነኝ እናም እኔ አሜሪካዊ እንደሆንኩ ይሰማኛል፣ ነገር ግን ፔሩን፣ የፔሩ ህዝብን በጣም እወዳለሁ፣ ስለዚህም ይህ የማንነቴ አካል ነው” ሲሉ ተናግሯል።

'ብዙ እየተማርኩ ነው'

እ.ኤ.አ. በግንቦት 8/2025 ዓ.ም የተረከቡትን የቅዱስ ጴጥሮስን መንበር በተመለከተ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “አሁንም ትልቅ የመማሪያ መስመር ከፊቴ ያለ ይመስለኛል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ እንዳሉት "የሐዋርያዊ እንክብካቤ መስጫ ክፍል" እስካሁን ድረስ በጣም ቀላል ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በመቀጠል "የዚህ ሥራ አጠቃላይ አዲስ ገጽታ በዓለም በመሪዎች ደረጃ ትክሻ ላይ የተጣለ ነው" ያሉ ሲሆን “የቤተ ክርስቲያን ድምጽ ጉልህ ሚና በሚጫወትበት በዚህ ወቅት ከተለያዩ መንግስታት መሪዎች፣ ከዓለም ሀገራት ጋር ያደረኩት የስልክ ውይይት ወይም ስብሰባ ሰዎች ያውቃሉ" ሲሉ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተጨማሪም ስለ ቅድስት መንበር ዲፕሎማሲያዊ ሚና ብዙ እየተማሩ እንደሆነ ገልፀዋል፣ “እነዚህ ነገሮች ለእኔ አዲስ ናቸው፣ በማንኛውም መልኩ … ብዙ እየተማርኩ ነው እናም በጣም እየተፈታተነኝ ነው፣ ነገር ግን አልተቸገርኩም" ሲሉ አብራርተዋል።

የቅድስት መንበር የሰላም ጥረት

ሰላምን ለማስፈን የሚደረገውን ጥረት በተመለከተ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ - በዩክሬን ስላለው ጦርነት ለተነሳው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ - በመጀመሪያ እና በቅርብ ወራት ውስጥ የተጀመረውን የሰላም ጥሪ በማስታወስ “ሰላም ብቸኛው መልስ ነው” በማለት ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ገልጸዋል።

"ከእነዚህ አመታት በኋላ የተፈጸመው ግድያ ከሁለቱም ወገን ሰዎች በብዛት አልቀዋል - በዚያ ልዩ ግጭት ውስጥ፣ ነገር ግን በሌሎች ግጭቶች ውስጥ እንኳን ሳይቀር - እኔ እንደማስበው ሰዎች እንደምንም ብለው መንቃት አለባቸው፣ ይህን ለማስቆም ሌላ መንገድ አለ" ብለዋል።

በሩሲያ እና በዩክሬን መካከል የሚደረገውን ድርድር የማስተናገድ እድልን ጨምሮ ቫቲካን በግጭቶች ውስጥ አስታራቂ ለመሆን ያቀረበችውን ተማጽዕኖዎች በተመለከተ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሲናገሩ “ጦርነቱ ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ቅድስት መንበር፣ እውነተኛ ገለልተኛ አቋም እንዲያዝ ከፍተኛ ጥረት አድርጋለች” ብለዋል።

ተፋላሚ ወገኖች ‘በቃ!’ እንዲሉ ማድረግ

ለርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳቱ፣ ዛሬ ቅድሚያ የሚሰጠው ጉዳይ “ለበርካታ የተለያዩ ተዋናዮች… በጦርነቱ ላይ ያሉ ወገኖች ጦርነት ‘በቃ’ እንዲሉ ለማድረግ ጠንክረን መግፋት እና ልዩነቶቻችንን የምንፈታበት ሌላ መንገድ መፈለግ እንደሚገባን ግንዛቤ ማስጨበጥ ይኖርብናል ብለዋል።

ያም ሆኖ “እኛ ተስፋ እናደርጋለን፤ መቼም ቢሆን ተስፋ መቁረጥ እንደማንችል አምናለሁ” ብሏል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ስለ “መጥፎ ተዋናዮች” እና “ፈተናዎች” መኖራቸውን እውቅና ሲሰጡ፣ ያም ሆኖ “ሰዎች ለውጥ የሚያመጡትን ከፍ ያሉ እሴቶችን፣ እውነተኛ እሴቶችን እንዲመለከቱ ማበረታታት ይቻላል” ብለዋል።

እናም፣ “ተስፋ ሊኖራችሁ ይችላል፣ እናም ለመግፋት እና ለሰዎች ‘ይህን በተለየ መንገድ እናድርገው’ ለማለት እየሞከርን ነው ብለዋል ቅዱስነታቸው።

ዋልታ ረገጥ ሐሳቦች፣ ቀውሶች፣ መከፋፈል

ስለዚህ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “ውይይት” እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፣ ከዓለም መሪዎች እና ከተለያየ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር በመገናኘት የውይይት አስፈላጊነትን ማጉላት ያስፈልጋል ብለዋል።

"በንድፈ ሀሳብ ደረጃ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ከእነዚህ ጉዳዮች ውስጥ ብዙዎቹ የሚስተናገዱበት ቦታ መሆን አለበት" ብሏል። “እንደ አለመታደል ሆኖ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ቢያንስ በዚህ ወቅት፣ በባለብዙ ወገን ጉዳዮች ላይ ህዝቦችን የማሰባሰብ አቅሙን ያጣ መሆኑ በአጠቃላይ እውቅና ያገኘ ይመስላል።

ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “የሰው ልጅ እየከፋ ያለውን ግፍ እና ጥላቻን ማሸነፍ እንዳለበት እራሳችንን ማሳሰባችንን መቀጠል አስፈላጊ ነው" ሲሉ በአጽኖት ይገልጻሉ።

የምንኖረው ዋልታ ረገጥ አመለካከት በሚንጸባረቅበት ጊዜ ውስጥ መሆኑን በመገንዘብ - በተለይም እ.አ.አ ከ2020 ዓ.ም ቀውስ በኋላ እና እንዲሁም በመጥፋት ላይ በሚገኙ እሴቶች ዙሪያ - ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንዲህ ብለዋል: "የሰው ልጅ ሕይወት፣ የቤተሰብ እና የህብረተሰብ እሴት" እጅግ በጣም አስፈላጊ ናቸው ብለዋል።

በተጨማሪም “በሠራተኛው ክፍል የገቢ ደረጃ እና ባለጸጋዎች በሚያገኙት ገንዘብ መካከል ያለው ልዩነት ያለማቋረጥ ሰፋ ያለ ልዩነት እንዳለ” ጠቁሟል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ከ60 ዓመታት በፊት የነበሩት ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ሠራተኞች ከሚቀበሉት ከአራት እስከ ስድስት እጥፍ የሚበልጡ ሊሆኑ ይችላሉ፤ በመጨረሻ ያየሁት አኃዝ ግን በአማካይ ሠራተኞች ከሚቀበሉት በ6,600 እጥፍ ይበልጣል” ብለዋል።

በዚህ ነጥብ ላይ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በተጨማሪም አሜሪካዊው ሥራ ፈጣሪ እና የቴስላ እና የስፔስኤክስ መስራች ኤሎን ማስክ የዓለም የመጀመሪያ ትሪሊዮነር እንደሆነ አንብብያለሁ ብለዋል፡- “ይህ ማለት ምን ማለት ነው? ይህስ ምን ማለት ነው? ከአሁን በኋላ ዋጋ ያለው ብቸኛው ነገር ሐብት ከሆነ፣ ትልቅ ችግር ውስጥ ነን…” ብለዋል።

ሲኖዶሳዊነት በጋራ ወደፊት መንገድ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ስለ ሲኖዶሳዊነት ፅንሰ-ሀሳብ ለተነሳው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ብዙ ጊዜ አሳልፈዋል፣ እሱም “እያንዳንዱ እና እያንዳንዱ የቤተክርስቲያን አባል በጸሎት፣ በማሰላሰል… ሂደት፣ ድምፅ እና ሚና ይኖረዋል ማለት ነው" ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “አንዳንድ ሰዎች በዚህ ስጋት ተሰምቷቸዋል” ብለዋል። አንዳንድ ጊዜ ጳጳሳት ወይም ካህናት ‘ሲኖዶሳዊነት ሥልጣኔን ሊወስድብኝ ነው’ ብለው ሊሰማቸው ይችላል ያሉ ሲሆን ነገር ግን፣ “ሲኖዶሳዊነት የሚለው ይህን አይደለም፣ እና ምናልባት የእናንተ ሥልጣን ምን እንደሆነ ያላችሁ ሀሳብ በተወሰነ መልኩ ትኩረት የለሽ እና የተሳሳተ ሊሆን ይችላል” በማለት ያስረዳሉ።

ይልቁንም ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “እኔ እንደማስበው፣ “ሲኖዶሳዊነት አንድ ላይ ተሰባስበን ማኅበረሰብ እንደምንሆን እና እንደ ቤተ ክርስቲያን ኅብረት እንደምንፈልግ የሚገለጽበት መንገድ ነው፣ ስለዚህም ቤተ ክርስቲያን ቀዳሚ ትኩረቷ በተቋማዊ የሥልጣን ተዋረድ ላይ ሳይሆን ‘እኛ በአንድነት’፣ ‘ቤተ ክርስቲያናችን’ በሚለው ስሜት ላይ ነው ማተኮር የሚገባን ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እንዳሉት ይህን አስተሳሰብ “በአሁኑ ጊዜ ለዓለም ብዙ ማስተማር” ይኖርብናል ያሉ ሲሆን ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድ ዓይነት ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ለመቀየር መሞከር አይደለም፣ በአሁኑ ጊዜ በዓለም ዙሪያ ያሉ ብዙ አገሮችን ብንመለከት፣ ዴሞክራሲ ለሁሉም ነገር ፍፁም መፍትሔ አይደለም ብለዋል።

ይልቁንም “የቤተ ክርስቲያን ሕይወት ምን እንደ ሆነ ስለመረዳት፣ ‘ይህን አንድ ላይ ማድረግ አለብን’ ስለማለት ነው” የምያስረዳን ብለዋል።

እ.አ.አ የ2026 ዓለም ዋንጫ

ቃለ ምልልሱ እ.አ.አ የ2026 ዓ.ም የፊፋ የዓለም ዋንጫን ይዳስሳል፣ ጋዜጠኛ አለን ሰሜን አሜሪካ ከፔሩ ጋር ስትጫወት ለማን እንደሚደግፉ ቅዱስነታቸውን ጠይቆ ነበር።

“ጥሩ ጥያቄ” ነው ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ መልስ መስጠት የጀመሩ ሲሆን፡- “ምናልባት ፔሩን እመርጣለሁ ምክንያቱም ከፔሩ ጋር ባለኝ ጥሩ ግንኙነት የተነሳ ነው፣ ነገር ግን እኔ የጣሊያን ቡድን ትልቅ አድናቂ ነኝ....." ሲሉ ቅዱስነታቸው ምላሽ ሰጥተዋል።

ከዚያም በእርሳቸው የትውልድ ሥፍራ አካባቢው ታዋቂ  የቤዝቦል ቡድን የሚያደርጉትን ትልቅ ድጋፍ በመጥቀስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፣ “ሰዎች እኔ የኋይት ሶክስ ደጋፊ መሆኔን ያውቃሉ፣ ነገር ግን እንደ ጳጳስ፣ እኔ የሁሉም ቡድኖች ደጋፊ ነኝ" ማለታቸው ተገልጿል።

15 Sep 2025, 16:10