ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅዳሜ ዕለት ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም ከጣሊያን ብሔራዊ ፀረ-አራጣ ምክር ቤት አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅዳሜ ዕለት ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም ከጣሊያን ብሔራዊ ፀረ-አራጣ ምክር ቤት አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት   (@Vatican Media)

ር.ሊ.ጳ. ሊዮ አራጣ ‘የሰውን ልብ ያበላሻል’ እና 'ድሆችን ባሪያ ያደርጋል' ሲሉ መናገራቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ አራጣ ድሆችን ባሪያ የሚያደርግ እና የሰውን ልብ የሚያበላሽ ከባድ ኃጢአት እንደሆነ በመገለጽ ተግባሩን ያወገዙ ሲሆን ለፍትህ እና ለምህረት እንደገና ቁርጠኝነትን ይጠይቃል እናም የቤተክርስቲያንን ፀረ-አራጣ ጥረት በኢዮቤልዩ አመት የተስፋ ምልክት አድርጎ መቀበል እንደሚገባ ገልጸዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ አራጣን ሕይወትን፣ ቤተሰብንና ማኅበራትን የሚያወድም “ከባድ ኃጢአት” ሲሉ አውግዘዋል፤ ይህንንም “የሰው ልብ መበላሸት” አቅመ ደካማ ሰዎችን የሚበዘብዝ እና የሰውን ክብር የሚጎዳ ነው ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ቅዳሜ ዕለት ጥቅምት 08/2018 ዓ.ም ከጣሊያን ብሔራዊ ፀረ-አራጣ ምክር ቤት አባላት ጋር በተገናኙበት ወቅት ባደረጉት ንግግር የአራጣ ተጎጂዎችን ለመርዳት እና ሥነ ምግባራዊ ኢኮኖሚያዊ ልምዶችን ለማስፋፋት ለሰላሳ ዓመታት ላደረጉት ተግባር እና ላሳዩት ቁርጠኝነት አመስግነዋል። በግለሰብም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ ያለው አራጣ ድሆችን እና የተገለሉ ሰዎችን እያሰቃየ ያለውን “አሳማሚ እና ጥንታዊ ቁስል ሆኖ ይቀራል” ሲሉ አስጠንቅቋል።

አራጣ የሒሳብ ጉዳይ ብቻ አይደለም።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “የአራጣ ክስተት የሰውን ልብ መበላሸትን ያመለክታል” ብለዋል ። ነቢዩ ኢሳይያስን በመጥቀስ፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ብዝበዛን እንደሚያወግዙና አማኞችን “የግፍን ሰንሰለት በጥሰው የተጨቆኑትን ነፃ አውጡ” በማለት ጥሪ እንዳቀረበ አስታውሷል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ሰዎችን ባሪያዎች እስኪሆኑ ድረስ የሚጨቁኑ ሰዎች አመለካከት ከአምላክ ፈቃድ ምንኛ የራቀ ነው! አራጣ የሂሳብ ጉዳይ ብቻ አይደለም- ቤተሰብን የሚያጠፋ፣ አእምሮንና ልብን የሚበላ አልፎ ተርፎም ሰዎችን ወደ ተስፋ መቁረጥ ወይም ራስን ማጥፋት የሚያስከትል ከባድ ኃጢአት ነው” በማለት ተናግሯል።

አራጣ ብዙውን ጊዜ በኢኮኖሚ ችግር ውስጥ ላሉ ሰዎች የሚሰጠውን እርዳታ እንደሚመስል በመናገር አስጠንቅቋል፣ ነገር ግን ብዙም ሳይቆይ “ለመሆኑ ራሱን ይገልጣል። መዘዙ በተለይ “እንደ የቁማር ሱስ ሰለባ በሆኑ ወይም የህክምና ወይም የገንዘብ ድንገተኛ አደጋዎች በተጋረጡ ቤተሰቦች ላይ” እንደሚወድቅ ተናግሯል።

መላው ህዝብ በባርነት ሊገዛ ይችላል

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ማስጠንቀቂያቸውን ከግለሰባዊ ጉዳዮች አልፈው “መላውን ሕዝብ ማንበርከክ የሚችሉ አራጣ የገንዘብ ሥርዓቶችን” አውግዘዋል።

የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮን በመጥቀስ “በንግድ ሥራ ላይ የተሰማሩትን በወንድሞቻቸውና በእህቶቻቸው በሰው ልጆች መካከል ረሃብና ሞት የሚያስከትል በአራጣና በነጋዴነት የሚሠሩትን” አስታውሷቸዋል። እንዲህ ያሉት ድርጊቶች “የኃጢአትን መዋቅር” የሚፈጥሩ እና “ከባድ ኃላፊነት” እንደሚሸከሙ ተናግሯል።

“በጣም ዕድለኛ ያልሆኑት ሰዎች በራሳቸው ሰዎች አይደሉምን? አቅመ ደካሞች ሰዎች የእኛ የሰዎችን ክብር አይጋሩምን? ጥቂት አጋጣሚዎችን አግኝተው የተወለዱት በሕይወት ለመትረፍ ብቻ ነውን?” ሲሉ ጥያቄ ያነሱት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ለእነዚህ ጥያቄዎች የምንሰጠው መልስ የሕብረተሰባችንን እና የወደፊት ሕይወታችንን ዋጋ የሚወስን ነው፣ ወይም ሥነ ምግባራዊና መንፈሳዊ ክብራችንን እናስመልሳለን፣ ወይም ወደ ቆሻሻ ጉድጓድ ውስጥ እንወድቃለን ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

በምህረት ላይ የተመሰረተ ተልእኮ

የጸረ-አራጣ ምክር ቤቱን ቀጣይነት ላለው አገልግሎት እያመሰገኑ፣ ርዕሰ ሊቀ ጳጳስ ሊዮ አሥራ አራተኛ በዚህ ቅዱስ ዓመት ውስጥ ሥራቸውን “የተስፋ ምልክት” ብለው ገልጸውታል፣ ይህም ከምሕረት ኢዮቤልዩ መንፈስ ጋር ሙሉ በሙሉ የተጣጣመ ነው ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዘኬዎስ የወንጌል ታሪክ ላይ በማሰላሰል፣ ልክ እንደ ቀረጥ ሰብሳቢው መንፈሳዊ ለውጥ ማምጣት እና መለወጥ፣ አንድ ሰው ያለምክንያት የክርስቶስን ፍቅር ሲያገኝ እውን ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል። “ትርፍ ግባችን በሚሆንበት ጊዜ ሌሎች ፊታቸውን ያጣሉ እና የመበዝበዣ መሣርያዎች ይሆናሉ። እናም በመጨረሻም እኛ ራሳችንን እና ነፍሳችንን እናጣለን” ብሏል።

አክለውም “አራጣ የሚከፍሉ ሰዎችን ከእዚህ ተግባር መመለሳችን በዚህ ምክንያት ለሚሰቃዩ ሰዎች ምን ያህል ቅርበት እንዳለን ለማሳየት አስፈላጊ ነው” ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ንግግራቸውን ሲያጠቃልሉ፣ አራጣን በመዋጋት ላይ የተሰማሩትን የቤተክርስቲያኗን አባቶች በመደገፍ እና በወንጌል በመነሳሳት በድፍረት እና በአንድነት እንዲጸኑ አበረታቷቸዋል።

20 Oct 2025, 14:14