ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ እምነት እና ምክንያት እርስ በርስ የሚደጋገፉ መሆናቸውን ገለጹ
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን
“እምነት እና ምክንያታዊነት የማይቃረኑ ብቻ ሳይሆን እርስ በርስ በሚያስደንቅ ሁኔታ የሚደጋገፉ ናቸው” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ ዓለም አቀፍ የፍልፍፍና ኮንግረስ ለባህሎች፣ ለፍልስፍና፣ ለክርስትና እምነት እና ለላቲን አሜሪካ አገራት ያደረገው አስተዋጽዖ” በሚል ርዕሥ በፓራጉዋይ “Nuestra Señora de la Asunción” ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ሲካሄድ ቆይቶ ዓርብ ለተጠናቀቀው ኮንግረስ በላኩት መልዕክት፥ በቅዱሳን እና በቀደሙት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት የቀረበውን አመለካከት ደግመዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ ዓለም አቀፍ ባለሙያዎችን ላሰባሰበ ከፍተኛ የአካዳሚክ ስብሰባ ተካፋዮች በላኩት መልዕክት መጀመሪያ ላይ፥ “ክርስቲያናዊ የፍልስፍና አስተሳሰቦች የአህጉሪቱን ባህል በመቅረጽ፣ ከእምነት ጀምሮ በጊዜያችን ባሉ ተግዳሮቶች ላይ ያለውን ሚና እና አስፈላጊነት ለመተንተን እና እርስ በርስ ለመገናኘት፣ ለማጥናት፣ ለመወያየት እና ለማቀድ የሚያስችል ቦታን ለማዘጋጀት እንደሚፈልግ ተናግረዋል።
በውስጥ ያለውን ተስፋ ግምት ውስጥ ማስገባት
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፥ በቅድሚያ “እርስ በርስ መገናኘት” በሚለው ላይ በማሰላሰል እንደተናገሩት፣ “ፍልስፍና በአረማዊ አውድ ውስጥ የተገኘ በመሆኑ ምክንያታዊ ነጸብራቁ የክርስትና እምነት ንጽህናን ሊበክል ይችላል የሚሉ በፍልስፍና ላይ እምነት የጣሉ ሰዎች ፈተናን የሚቃወም የተመሰገነ ዓላማ ነው” ብለዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አጽንኦት ሰጥተው ሲናገሩ፣ ቅዱስ አጎስጢኖስ “ፍልስፍና በጠቅላላው መወገድ አለበት ብሎ የሚያስብ ሁሉ ጥበብን መውደድ የለብንም የሚል ነው” ብሎ ማሳሰቡን ገልጸው፥ በመሆኑም ምእመኑ የተለያዩ የፍልስፍና ትምህርት ቤቶች ከሚያቀርቧቸው ሃሳቦች ሳይርቅ ነገር ግን ከቅዱሳት መጻሕፍት ጀምሮ በሃሳባቸው ላይ መነጋገር እንዳለበት እና በዚህም ፍልስፍናዊ አስተሳሰብ የእምነትን ስጦታን ከማይጋሩት ጋር ለመገናኘት ዕድል ይሆናል” ብለዋል።
አማኝ ፈላስፋ የሚያከናውነው መልካም ነገር
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ በእግዚአብሔር ከታሪክ፣ ከፍልስፍና እና ከሌሎች ዓይነት ጭፍን ጥላቻዎች ጋር የተቆራኘ መሆኑን ከተሞክሮዬ አውቃለሁ” ሲሉ በምሬት ተናግረው፥ “ፍልስፍናን ወደ ይቅርታ መጠየቂያ መሣሪያነት መቀየር እንደማይገባ በማስጠንቀቅ፥ ፍልስፍናን በመመርመር ሊገኝ የሚችል ትልቅ ጥቅም መኖሩን ጠቁመዋል።
“አማኝ ፈላስፋ ሊያከናውን የሚችላቸው በጎ ነገሮች እጅግ ብዙ ናቸው” ያሉት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ በሕይወት ምስክርነት ሆነ ሐዋርያው ቅዱስ ጴጥሮስ፥ “ነገር ግን ክርስቶስን ጌታ አድርጋችሁ በልባችሁ ቀድሱት፤ በእናንተም ስላለች ተስፋ ምክንያት ለሚጠይቋችሁ ሁሉ መልስ ለመስጠት ሁልጊዜ የተዘጋጃችሁ ሁኑ” በማለት ማበረታታቱን አስታውሰዋል።
የፍልስፍና ከፍታ እና አደጋዎቹ
ሁለተኛው ዓላማ በፍልስፍና ዙሪያ ምርመራን ማካሄድ ሲሆን፥ ይህም በመለኮታዊ ጸጋ አማካይነት ወደ እኛ ሊመጡ ከሚችሉት ጋር "በምክንያታዊነት" ግራ ከሚያጋቡ የሕይወት ውጣ ውረዶች ድረስ፣ በዘመናችን እውቀትን ለማግኘት ተብሎ ለሚደረግ ግምታዊ ምክንያት ትንታኔን እንድንሰጥ ያስችለናል” ብለዋል።
“ፍልስፍና የሰውን ልጅ የማሰብ ችሎታ የሚጠይቅ በመሆኑ ከፍ ሊል እንደሚችል መዘንጋት የለብንም” ብለው ነገር ግን ወደ ጨለማ አዘቅት ውስጥ ሊወርድ እንደሚችል መዘንጋት የለብንም ብለዋል።
“ምክንያታዊ ወይም ፍልስፍናዊ የሚባሉት ነገሮች በሙሉ ተመሳሳይ እሴት እንደሌላቸው የገለጹት ቅዱስነታቸው፥ ፍሬያማነቱ የሚለካው ከመሆን እውነት ጋር በመስማማት እና አእምሮን ሁሉ ለሚያበራው ፀጋ ባለው ተቀባይነት ነው” ብለዋል።
እምነት እና ምክንያት እርስ በርሳቸው ይደጋገፋሉ
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ለሁሉም ሰው ካላቸው ልባዊ ርኅራሄ፥ የፍልስፍና ትምህርት የተከበረ ተግባር በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠረውን የሰው ልጅ ክብር፣ በመልካም እና በክፉ መካከል ያለውን ግልጽ ልዩነት፣ ወደ ፈጣሪና አዳኝ ወደ ሆነው እግዚአብሔር የሚያመራው የእውነታው አስደናቂ አወቃቀር ይበልጥ ግልጽ እንዲሆን የበኩላችንን አስተዋጽኦ ማድረግ አለብን” ብለዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ ቀጣዩ የውይይት እርምጃ መሠረታዊ ነው በማለት እንደተናገሩት፥ “ይህም ለታላላቅ አሳቢዎች፣ ለነገረ መለኮት ምሁራን እና ለክርስቲያን ፈላስፋዎች እጅግ ፍሬያማ መሆኑን አሳይቷል” ብለው፥ የሰው ልጅ ምክንያታዊነት በፈጣሪው የተገለጠ ስጦታ እንደሆነ እና የአእምሯችን ጥልቅ ምርምር ወደ ጥበብ እንደሚመራ እና ይህ ጥበብ በፍጥረት የተገለጠ እና አብ ከገለጠልን ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር በመገናኘት ላይ ነው” ብለዋል።
“በዚህ ዕይታ መሠረት የ2ኛው ክፍለ ዘመን ፈላስፋና ሰማዕት በሆነው በቅዱስ ዩስጢኖስ መታየቱን፥ በኋላም እንደ ቅዱስ ቦናቬንቸር እና ቅዱስ ቶማስ አኩዊናስ ባሉ ታዋቂ ሰዎች ቀጥሏል” ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ አስረተዋል።
በዚህ ስሜት ከእርሳቸው በፊት የነበሩት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ 2ኛ እንደ ጎርጎሮሳውያኑ በ1998 ዓ. ም ይፋ ባደረጉት “እምነት እና ምክንያት” ወይም “Fides et Ratio” በተሰኘ ሐዋርያዊ ቃለ-ምዕዳናቸው ላይ “በሥነ መለኮት ጥበብ እና በፍልስፍና እውቀት መካከል ያለው የጠበቀ ግንኙነት የተገለጠውን እውነት በመፈተሽ ረገድ ከክርስቲያን ወጎች የመጀመሪያዎቹ ውድ ሃብቶች መካከል አንዱ ነው” ብለዋል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ፥ መልዕክታቸውን ሲያጠቃልሉ፥ በዛሬው ዓለም ክርስቲያን አሳቢ ለትክክለኛው የፍልስፍና ጥሪ እንደ ታማኝ እና ጽኑ የጥበብ ፍለጋ ሕያው ማስታወሻ እንዲሆን ተጠርቷል” ብለዋል።
