ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በካስቴል ጋንዶልፎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምልሽ ሲስጡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በካስቴል ጋንዶልፎ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸው ጥያቄ ምልሽ ሲስጡ 

ር.ሊ.ጳ ሊዮ የመስከረም 27 መታሰቢያ ቀን ላይ እንደገና መነጋገርን መማር አለብን ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የዛሬ ሁለት አመት ገደማ መስከረም 27/2018 ዓ.ም ከሁለት አመታት በፊት ሃማስ በእስራኤል ያደረሰውን ጥቃት እና ከዚያ በኋላ ምን እንደተከሰተ በመግለጽ በቅርቡ ወደ ቱርክ እና ሊባኖስ የሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት ወደ መካከለኛው ምስራቅ የሰላም መልእክት ለማምጣት ያለመ ነው ብለዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"እነዚህ ሁለት አስጨናቂ አመታት ነበሩ። ከሁለት አመት በፊት በአሸባሪዎች ጥቃት 1,200 ሰዎች ተገድለዋል።በአለም ላይ ያለውን የጥላቻ መጠን ግምት ውስጥ በማስገባት ምን ማድረግ እንዳለብን እራሳችንን መጠየቅ አለብን። በሁለት አመታት ውስጥ 67,000 ፍልስጤማውያን ተገድለዋል። ጥላቻን መቀነስ አለብን" ማለታቸው ተገልጿል።

ሃማስ በእስራኤል ላይ የሽብር ጥቃት የተፈፀመበትን ሁለተኛ አመት አጋጣሚ ስንመለከት፣ ጋዛን ያወደመ እና በሺዎች ለሚቆጠሩ ፍልስጤማውያን ሰላማዊ ሰዎች ሞት ምክንያት የሆነው ግጭት መጀመሪያ አስመልክቶ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ የተናገሩት ቃል ነበረ።  

ይህንን አስተያየት ቅዱስነታቸው የሰጡት ማክሰኞው መስከረም 27/2018 ዓ.ም  በካስቴል ጋንዶልፎ በሚገኘው የቪላ ባርቤሪኒ መግቢያ በር ውጪ ላይ ጳጳሱን እየጠበቁ ለነበሩት ጋዜጠኞች የተናገሩት ነው።

ፀረ-ሽብርተኝነት እና ፀረ-ሴማዊነት አቋም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ሁለቱንም ማለትም ሽብርተኝነትን እና በቅርቡ የተከሰቱትን ፀረ-ሴማዊነት አውግዘዋል፣ የሰላምን የወንጌል መልእክት በማረጋገጥ ሁሉም ሰው ለሰላም እንዲተጋ ጠይቀዋል።

"በሽብር ተግባር ውስጥ የተሰማሩ ቡድኖችን መቀበል እንደማንችል እርግጠኛ ነን፣  በዓለም ላይ ያለው የጥላቻ ስልት ሁል ጊዜ ውድቅ መደረግ አለበት። በተመሳሳይም ፀረ-ሴማዊነት እየጨመረ መሆኑ የምያሳስብ ጉዳይ ነው። ሁልጊዜ ሰላምን እና የእያንዳንዱን ሰው ክብር ማክበር አለብን። ይህ የቤተክርስቲያን መልእክት ነው" ሲሉ ተናግረዋል።

የማያቋርጥ የጸሎት ኃይል

በመጨረሻም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቅድስት ምድር ያለው ደም አፋሳሽ ግጭት እንዲያበቃ ምእመናን ሁሉ መጸለያቸውን እንዲቀጥሉ ጋብዘዋል፣ እናም ቤተክርስቲያኗ ውይይት እና እርቅን ለማስፋፋት ያላትን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል።

“ቤተክርስቲያኗ፣ በጥቅምት ወር ሁሉም ሰው ለሰላም እንዲጸልይ ጠይቃለች፤ እንዲሁም በማንኛውም ጊዜ ውይይቶችን ለማበረታታት ቤተክርስቲያን የምትገኝበትን መንገድ እንፈልጋለን” ብሏል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ብፁዕ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ለቫቲካን መገናኛ ብዙኃን በሰጡት ቃለ ምልልስ የእስራኤል ኤምባሲ የሰጠውን ወሳኝ ምላሽ አስመልክቶ ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፣ “ካርዲናሉ በዚህ ጉዳይ ላይ የቅድስት መንበር አቋም በግልጽ ገልጸዋል” ብለዋል።

የቱርክ ጉዞ፡ የአንድነት ጊዜ

የቅድስት መንበር የእትመት እና የዜና ክፍል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ወደ ቱርክ እና ሊባኖስ የሚያደርጉትን የመጀመሪያ ሐዋርያዊ ጉዞ እ.አ.አ ከኅዳር 27 እስከ ታኅሣሥ 2/2025 ዓ.ም እንደሚሆን  በይፋ አሳውቀዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወደዚህ ዓይነት አሳሳቢ እና ፖለቲካዊ ውጥረት ወዳለበት አካባቢ የሚጓዙበትን ምክንያት እንዲያብራሩ በጋዜጠኞች ተጠይቀዋል።

“የቱርክ ጉዞው ያነሳሳው ከኒቂያ ጉባኤ በኋላ ያሉትን 1,700 ዓመታትን ለመዘከር እና አመታዊ በዓል ላይ ለመገኘት ነው። ይህ በጣም አስፈላጊ ወቅት ነው ብዬ አምናለሁ፣ የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በሕይወት እያሉ ሊያደርጉት የፈለጉት ጉዞ ነው። ለመላው ክርስቲያኖች ይህ የእምነት እውነተኛ አንድነት ጊዜ ይሆናል። ይህን ታሪካዊ አጋጣሚ እንዳያመልጠን ነው። ነገር ግን ወደ ኋላ ለመመልከት አይደለም - ወደ ፊት መመልከት ነው የሚገባን" ሲሉ በቱርክ የምያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት በተመለከተ ቅዱስነታቸው ገልጸዋል።

የወንጌልን መጽናናትን ወደ ሊባኖስ ለመውሰድ

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሊባኖስ ጉብኝታቸው በዋነኛነት የታሰበው እ.አ.አ በነሐሴ 4/2020 ዓ.ም በቤሩት ወደብ ላይ ከደረሰው ፍንዳታ በኋላ በሐዘን የተመታውን ህዝብ መጽናናትን ለመስጠት ነው ሲሉ የተናገሩት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ "በሊባኖስ ውስጥ፣ በመካከለኛው ምስራቅ፣ ብዙ መከራ በደረሰባት ሀገር ውስጥ፣ በመካከለኛው ምስራቅ ያለውን የሰላም መልእክት እንደገና ለማወጅ እድል አገኛለሁ። የቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ወደዚያ መሄድ ፈልጎ ነበር። ከፍንዳታው በኋላ የሊባኖስን ህዝብ በጽናት ከታገሡት ሁሉ በኋላ ማቀፍ ፈልጎ ነበር። ይህንን የሰላም እና የተስፋ መልእክት ለማምጣት እንሞክራለን" ሲሉ ቅዱስነታቸው ተናግረዋል።

 

08 Oct 2025, 11:31