ወደ ቱርክ ሐዋርያዊ ጉዞ፡ የመጀመሪያው ቀን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሕዳር 18 እስከ ሕዳር 23/2018 ዓ.ም ድረስ የርዕሰ ሊቃነ ጵጵስና ዘመናቸው ከጣሊያን ውጪ የመጀመሪያ የሆነውን ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማድረግ በቀደም ተከተል ወደ ቱርክያ እና ሊባኖስ የምያደርጉትን ጉዞ ትላንት ማለትም ሕዳር 18/2018 ዓ.ም ወደ ቱርክ በማቅናት መጀመራቸው ይታወሳል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ወደ ቱርክ ባደረጉት ሐዋርያዊ ጉዞአቸው የመጀመሪያ ቀን ከአገሪቱ የሲቪል ባለሥልጣናት ጋር ከተገናኙ በኋላ ቤተክርስቲያንና የቱርክ ዜጎች የመገናኘትና የመነጋገር ባህል እንዲገነቡ ጥሪ ካቀረቡ በኋላ ቀኑን አጠቃለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐሙስ ዕለት በቱርክ ዋና ከተማ አንካራ መድረሳቸው የሚታወስ ሲሆን ይህ ጉዞ በቱርክ እና ሊባኖስ የምያደርጉት የስድስት ቀናት ቆይታ የመጀመርያው ክፍለ ጊዜ ነው። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በቱርክ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር መህመት ኑሪ ኤርሶይ ጋር በስታንቡል አውሮፕላን ማረፊያ በደረሱበት ወቅት መገናኘታቸው ተገልጿል። ይፋዊ የአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ ከተፈጸመ በኋላ ቅዱስ አባታችን የሙስጠፋ ከማል አታቱርክን መካነ መቃብር ጎብኝተው በቱርክ ሪፐብሊክ መስራችና የመጀመሪያ ፕሬዝዳንት መካነ መቃብር ላይ የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ጉብኝታቸውን ለማስታወስ “በወርቃማው መጽሐፍ” ላይ ሲፈርሙ በእንግሊዝኛ “ቱርክን ለመጎብኘት በመቻሌ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፣ እናም ለዚህች ሀገርና ለሕዝቧ የተትረፈረፈ ሰላምና ብልጽግና እማጸናለሁ" የሚል ጽሑፍ አኑረዋል።

ከፖለቲካ እና ከሲቪል መሪዎች ጋር የተደረጉ ስብሰባዎች
ከፖለቲካ እና ከሲቪል መሪዎች ጋር የተደረጉ ስብሰባዎች   (ANSA)

ከፖለቲካ እና ከሲቪል መሪዎች ጋር የተደረጉ ስብሰባዎች

በቱርክ የመጀመሪያው ቀን በአብዛኛው ከፖለቲካ እና ከሲቪል ባለስልጣናት ጋር በተደረጉ ስብሰባዎች የተሞላ ነበር።

የአታቱርክ መታሰቢያ ጉብኝትን ተከትሎ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ በፈረስ ጠባቂዎች ቡድን ወደ ፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግሥት ታጅበው ከሄዱ በኋላ ከቱርክ ሪፖብልክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ጋር መገናኘታቸው ተግልጿል።

28 Nov 2025, 16:31