ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፤ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፤ 

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ክርስቲያናዊ ማንነት የትምህርት ሁሉ መሪ መሆኑን ገለጹ

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በስፔይን ማድሪድ ለተካሄደው የመምህራን ጉባኤ መልዕክት ልከዋል። ቅዱስነታቸው ለመምህራኑ በላኩት መልዕክት፥ ክርስቲያናዊ ማንነት ለትምህርት ዋና መሠረት መሆኑንም አስታውሰዋል። ኢየሱስ ክርስቶስ የማስተማር ሥራ መሪ እንደሆነ እና የሰዎችን ባህሪንም ሆነ እውቀትን ለመቅረጽ ዋና መሪ መሆኑን አስታውሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ቅዳሜ ኅዳር 13/2018 ዓ. ም. በስፔይን መዲና ማድሪድ በሚገኘው “በኑዌስትራ ሲኞራ ዴል ቡዌን ኮንሴዮ” ኮሌጅ በተካሄደው ጉባኤ ላይ ለተገኙት የጉባኤው ተሳታፊዎች በላኩት የቪዲዮ መልዕክት፣ ዘመናዊውን ትምህርት ያጋጠመውን ፈተና ለመውጣት ላሳዩት ቁርጠኝነት መምህራንን አድንቀዋል።

“በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ውስጥ ያላችሁ ተልዕኮ አዳዲስ ትውልዶችን እና በውስጣቸው ለሚገኙት ማኅበረሰቦች ጠንካራ ሕያው ኃይል ነው” ብለው፥ የጉባኤውን ጭብጥ በማስመልከት እንደተናገሩት፥ “ማንነት ከሌለ ትምህርት ሊኖር አይችልም” ብለዋል።

ክርስቲያናዊ ማንነት ጌጥ ሳይሆን ለትምህርት ሂደት ትርጉም፣ ዘዴ እና ዓላማ መሆኑን አስረድተዋል።

የሁሉ መሪ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው

“መርከበኞች በሰሜኑ ኮከብ እንደሚመሩ ሁሉ የክርስትና ትምህርት መሪ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው” ሲሉ አስረድተው፥ ትምህርት መሪ ከሌለው የተለመደ ይሆን እና የሰውን ልጅ የመለወጥ ኃይሉን ሊያጣ ይችላል” ብለዋል።

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ አክለውም፥ በትምህርት ውስጥ እምነትን እና ምክንያት የማስገባት አስፈላጊነት አፅንዖት ሰጥተዋል።

እምነት እና ምክንያት ትምህርትን የሚቃረኑ ሳይሆን ነገር ግን እውነታን ለመረዳት፣ ባህሪን ለመቅረጽ እና ብልህነትን ለማዳበር ተጓዳኝ መንገዶች እንደሆኑ አስረድተው፥ የትምህርት ልምዶች ለሁሉም ቤቱ በሆነ ማህበረሰብ ውስጥ ሳይንስን፣ ታሪክን፣ ሥነ ምግባርን እና መንፈሳዊነትን ማካተት እንዳለባቸው አሳስበዋል።

በቤተሰብ፣ በቁምስና፣ በትምህርት ቤቶች እና በአካባቢው እውነታዎች ውስጥ እውነተኛ ትብብር መኖር እያንዳንዱን ተማሪ በእምነት እና በመማር ሂደት ውስጥ በተጨባጭ ይከተሉታል” ብለዋል።

ቤተ ክርስቲያን በትምህርት ላይ ያላት የእናትነት ሚና

በሁለተኛው የቫቲካን ጉባኤ እንደተገለጸው፥ የቤተ ክርስቲያንን የእናትነት ሚና ያስታወሱት ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ “ቤተ ክርስቲያን አማኞችን የምታፈራ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽራ፣ እጅግ ቅዱስ ከሆነው መሥራቿ የተሰጣትን የመምራት እና የማስተማር አደራን የምትጠብቅ፣ ልጆቿን የምታስቀድም እና የምትደግፍ በእናትነት ድጋፍ የግለሰቦችን እና የሕዝቦችን ሕይወት የምትመራ እናት ናት” ብለዋል።

የትምህርት እጅግ አስፈላጊ

የቀድሞው ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ጳውሎስ ስድስተኛ “Gravissimum educationisወይም “የትምህርት አስፈላጊነት” በሚል ርዕሥ ይፋ ያደረጉት ሐዋርያዊ መልዕክት 60ኛ ዓመት መታሰቢያን በማስመልከት ባስተላለፉት መልዕክት፥ መምህራን ሥራቸውን የቤተ ክርስቲያኗ አስፈላጊ ተልዕኮ አካል አድርገው እንዲመለከቱት በማበረታታት፥ “ትምህርት ማኅበራዊ አገልግሎት ብቻ ሳይሆን የቤተ ክርስቲያኗን ማንነት እና ጥሪን የሚገልጽ ነው” ብለዋል።

 

24 Nov 2025, 14:42