ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ  (@Vatican Media)

ለሊባኖስ እና ለዓለም ተስፋ

የቫቲካን ዜና የአርታኢ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አንድሪያ ቶርኔሊ ሊባኖስ በመከራው ወቅት እንኳን የሰጠችውን የተስፋ መልእክት ላይ ትንታኔ የሰጡ ሲሆን ይህም ርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሰላም በሚያምኑ ወጣቶች እና ከእምነት ልዩነቶች ባሻገር በሚመለከቱ እና እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሰዎች በሚቀበሉ ቤተሰቦች እንደሚታይ ይናገራሉ።

በአቶ አንድሪያ ቶርኒዬሊ

የተለያዩ እምነቶችን በሚከተሉ ሰዎች መካከል አብሮ የመኖር እድል እና ከጎሳ ድንበሮች እና ወንድማማችነት በላይ ይህ ርዕዮተ ዓለማዊ ክፍፍሎች ሊባኖስን ያቆሰለው ነገር ነው፣ “መልእክት የሆነች ሀገር”፣ ዓለምን እንደ ተጨባጭ ዕድል እና ወደ ሰላም የሚያደርስ መንገድ ማሳየቷን ቀጥላለች።

ለዚህች ሊባኖስ፣ ለጦርነት እና ለጥላቻ እጅ ለመስጠት ፈቃደኛ ባልሆኑ ወጣቶች ውስጥ የተተከለውን ተስፋ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የወደፊቱን ለመገንባት መንገድ አድርገው ጠቁመዋል።

የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ በአንጾኪያ ማሮናይት ፓትርያርክ ዋና መሥሪያ ቤት ለተሰበሰቡት በሺዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ንግግር ሲያደርጉ፣ አድካሚ በነበረው የስብሰባ ቀን መጨረሻ ላይ፣ “ተስፋ አላችሁ! ጊዜ አላችሁ! ለማለም፣ ለማቀድ እና መልካም ለማድረግ የበለጠ ጊዜ አላችሁ። እናተ የሁኑ ጊዜ ናችሁ፣ የወደፊቱም በእጆቻችሁ ውስጥ እየተቀረጸ ነው! የታሪክን አቅጣጫ የመቀየር ጉጉት አላችሁ! ለክፋት እውነተኛ ተቃውሞ ክፉን በክፉ መመለስ አይደለም፣ ነገር ግን ፍቅር - የራስን ቁስሎች ለመፈወስ እና የሌሎችን ቁስሎች ለመንከባከብ የሚችል ፍቅር ዓይነተኛ ምላሽ ነው” በማለት መናገራቸው ይታሳል።

ከተሰብሳቢዎቹ መካከል አንዳንዶቹ ስለዚህ በነፃነት ስለተሰጠው ፍቅር ተናግረው ነበር - የሌሎችን ቁስሎች ለመፈወስ የሚችል ፍቅር፣ ምክንያቱም በቁስላቸው ውስጥ የራሳችንን ቁስሎች እናውቃለን፣ እናም ከሁሉም በላይ ደግሞ በሚሰቃዩት ሰዎች ውስጥ የእግዚአብሔርን ፊት ስለምናውቅ። ኤሊ የተባለች ወጣት ስለዚህ ጉዳይ ተናግሯል፡- እየሠራ እያለ ገንዘብ ለመቆጠብ ለዓመታት ከከፈለ በኋላ፣ በአገሪቱ የኢኮኖሚ ውድቀት ምክንያት ዕቅዶቹ ሲወድቁ አየ፣ ይህም ሁሉንም ነገር እንዲያጣ አድርጎታል። ሆኖም ላለመሰደድ ወሰነ፡- “አገሬ እየተሰቃየች እያለ እንዴት ወደ ስደት ልሄድ እችላለሁ?” ብሎ ለእራሱ እራሱ ጥያቄ አቀረበ።

ከዚያም በታይዜ በተካሄደው የጸሎት ስብሰባ ላይ፣ በእሷ ዕድሜ ክልል ውስጥ የምትገኝ አሲልን የምትባል ወጣት ሊባኖሳዊት ግን የሙስሊም እምነት ተከታይ የነበረችው ልጅ በደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ አገኘቻት። የአሲል መንደር በእስራኤል ወረራ ወቅት በቦምብ ሲደበደብ፣ ቤተሰቧ የሚሄዱበት ቦታ ስላልነበረው ወደ ጆኤል ቤት ሄዱ። ጆኤል እና እናቷ በደስታ ተቀብለዋቸዋል፡- “በሃይማኖት መካከል ያለው ልዩነት እንቅፋት አልፈጠረም… በጥልቅ ስምምነት ኖረናል… አንድ መሠረታዊ እውነት ተረድቻለሁ፣ እግዚአብሔር በቤተክርስቲያን ወይም በመስጊድ ግድግዳዎች ውስጥ ብቻ አይኖርም። የተለያዩ ልቦች ሲገናኙ እና እንደ ወንድም እና እህት ሲዋደዱ እግዚአብሔር ይገለጣል”።

ከእሷ በኋላ የአሲል እናት ሩካያ እንዲህ ሲሉ ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል “የጆኤል እናት የቤቷን በር ከፍተውልኝ ‘ይህ የአንቺ ቤት ነው አሉኝ። ማን እንደሆንኩ፣ ከየት እንደመጣሁ ወይም ምን እንደማምን አልጠየቁም… ሃይማኖት የምትናገሩት ነገር እንዳልሆነ ተረድቻለሁ፤ እያንዳንዱን ድንበር የሚያቋርጥ በፍቅር የምትኖሩበት ነገር ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ይህን ሁሉ እውን ያደረገው ምንድን ነው? ሊባኖስ እንደነበረች እና ምን እንደሚፈለገው እንድትቆይ ያስቻላት ምን መሠረት ነው? ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ “ሀሳብ፣ ውል ወይም የሞራል መርህ ብቻ ሊሆን የማይችል” መሠረት ለይተዋል። የአዲሱና የታረቀው ሕይወት እውነተኛ መርህ “ከላይ የሚመጣው ተስፋ ነው፡ ክርስቶስ ራሱ ነው! ኢየሱስ ለሁሉም መዳን ሞቶ እንደገና ተነሳ። እርሱ ሕያው የሆነው፣ የእኛ እምነት መሠረት ነው፤ ዓለምን ከክፉ ሁሉ የሚያድነው የምሕረት ምስክር ነው”።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ የመጀመሪያውን ሐዋርያዊ ጉዞ ማክሰኞ ሕዳር 23/2018  አጠናቀው ወደ ሮም በሚመለሱበት ወቅት የሚጠናቀቀው፣ ቅዱስነታቸው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን 267ኛ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሆነው ከተመረጡ በኋላ በማግስቱ የተናገራቸውን ቃላት ትርጉም ለማብራራት ይረዳል፣ አዲሱ የሮም ጳጳስ በቤተክርስቲያን ውስጥ የሥልጣን አገልግሎት የሚሰጥ ማንኛውም ሰው “ክርስቶስ እንዲነግሥ እርሱ መክሰም አለበት” ሲሉ ተናግረዋል። ወንጌልን ለሚያውጅ ማንኛውም ሰው የሚተገበሩ ቃላት ናቸው። ለሌሎች የክርስቲያን አብያተ ክርስቲያናት መሪዎች እና የሊባኖስን ሃይማኖታዊ ሞዛይክ (ሕብረ ሃይማኖታዊነትን) ከሚመሰረቱ የተለያዩ ወጎች ለተውጣጡ የሙስሊም መሪዎች፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በዚህች ምድር የኢየሱስን የሕዝብ አገልግሎት የተመለከቱ ክስተቶችን እንዳዩ አስታውሰዋል። በተለይ ለሴት ልጇ ፈውስ ስትፈልግ የነበረችው ከነዓናዊቷ ሴት ጋር የነበረው ግንኙነት እና እምነቷን ጠቅሰዋል፡- “እዚህ፣ ምድሪቱ እራሷ በኢየሱስ እና በተማጸነች እናት መካከል ከሚደረግ የመግባቢያ ቦታ በላይ ትሆናለች፤ ትህትና፣ እምነት እና ጽናት ሁሉንም እንቅፋቶች የሚያሸንፍበት እና እያንዳንዱን የሰው ልጅ ልብ የሚያቅፈውን የእግዚአብሔርን ወሰን የሌለው ፍቅር የሚያሟላበት ቦታ ይሆናል”።

“ክርስቶስ እንዲኖር ወይም እንዲነግሥ እኛ መክሰም” ማለት ወደ ውስጣዊነት መገለል፣ “ፍጹም” የሆኑ የተዘጉ ማህበረሰቦችን መገንባት ወይም በቁጥር ላይ ተመስርተው የኃይል እና የታላቅነት ህልሞችን ማሳደድ ማለት አይደለም፣ ይህም በትንሽነት የሚታየውን የእግዚአብሔርን አመክንዮ መርሳት ነው። “ክርስቶስ እንዲኖር የእኛ መክሰም” ማለት ውስንነታችን ቢኖርም እያንዳንዱን የሰው ልጅ ልብ ያለ ልዩነት የሚያቅፍ፣ ለትንንሽ፣ ለተጨቆኑ እና ለሚሰቃዩት የሚያጎነብስ ወሰን የሌለው የእግዚአብሔር ፍቅር መሳሪያ መሆን ማለት ነው። የሊባኖስ ወጣቶችን ሊያበረታቷቸው የመጠቱት የቅዱስ ጴጥሮስ ተተኪ ፊት የመሰከሩት ይህን ነው።

 

03 Dec 2025, 19:00