ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በቫቲካን በሚገኘው በቅዱስ ጴጥሮስ አደባባይ   (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጤና አጠባበቅ ለሚሰቃዩ ሰዎች የእግዚአብሔርን ርኅራኄ መግለጽ አለበት አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በካሪታስ ኢንተርናሽናልኒስ በተዘጋጀው የጤና ኮንፈረንስ ላይ ለተሳታፊዎች ንግግር ባደረጉበት ወቅት፣ በወንጌል እሴቶች ላይ የተመሠረተ የጤና አጠባበቅ ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከሰኔ 16 እስከ ሰኔ 18/2018 ዓ.ም በካስቴል ጋንዶልፎ በተካሄደው “በካሪታስ ኮንፌዴሬሽን ውስጥ ለጤና ሁሉን አቀፍ አቀራረብ” በሚል ርዕስ በተካሄደው የጤና ኮንፈረንስ ላይ ለሚሳተፉ ሁሉ ሞቅ ያለ ሰላምታ እና የመንፈሳዊ ቅርበት ማረጋገጫ ልከዋል።

ረቡዕ ዕለት ሰኔ 17/2018 ዓ.ም የተላከው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ መልእክት በቫቲካን ዋና ጸኃፊ በካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን ተፈርሞ መላኩ ተገልጿል።

የቡድኑ ሥራ “ለትብብር እና ለመተጋገዝ አዲስ መነሳሳት አስተዋጽኦ እንዲያደርግ” ጸልየዋል፣ እና ተሳታፊዎች “በወንጌል እሴቶች ላይ በመመስረት ለታመሙ ሰዎች የሚደርገውን የጤና አጠባበቅ ለማሻሻል” በሚያደርጉት ጥረት ላይ አበረታተዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስን ብዙውን ጊዜ እንደ መለኮታዊ ሐኪም አድርጎ እንደሚያቀርበው በማስታወስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ክርስቶስ ለድሆች ጤናን የሚያመጣው ስቃይን፣ ውርደትን እና መገለልን የሚያስከትሉ የአእምሮ፣ የአካል እና መንፈሳዊ ችግሮችን በመፈወስ እንደሆነ አስታውሰዋል።

ይህ ክብር “የእያንዳንዱን ሰው የግል ሁኔታ ያልፋል” ብለዋል። ጤናን በመመለስ፣ ኢየሱስ የእያንዳንዱን ሰው ውስጣዊ ክብር ይገልጣል እና የሰው ልጅን በእግዚአብሔር ዘላለማዊ መዳን ይመራል ያሉት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሕመምተኞች መካከል በመገኘት የእግዚአብሔርን መንግሥት ስታውጅ ተሳታፊዎች የቤተክርስቲያኒቱን ተልዕኮ እንዲቀጥሉ አበረታተዋል።

“መዳን ረቂቅ ሀሳብ አይደለም” ብለዋል፣ “ነገር ግን የሚጀምሩት የሚሰቃዩትን ቁስሎች በመፈወስ ተጨባጭ እርምጃ ነው” በማለት በመልእክታቸው የገለጹት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የካሪታስ እና ተባባሪዎቹ ሥራ “ለተቸገሩ ሰዎች የእግዚአብሔርን ርህራሄ እና ቸርነት” ለማምጣት ያነጣጠረ እንደሚሆን ያላቸውን ተስፋ በመግለጽ መልእክታቸውን ደምድመዋል።

25 Jun 2026, 15:25