ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የኢየሱሳዊያን ማሕበር ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች ጋር በቫቲካን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የኢየሱሳዊያን ማሕበር ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች ጋር በቫቲካን   (@VATICAN MEDIA)

ር.ሊ.ጳ ሊዮ፣ ዩኒቨርሲቲዎች አንድነትን እና የጋራ ጥቅምን ለማሳደግ ዋና መንገዶች ናቸው አሉ!

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የኢየሱሳዊያን ማሕበር ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች ጋር ባደረጉት ስብሰባ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች የተገለሉ ሰዎችን ፍላጎቶች ለመፍታት እና የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) ተጽእኖን ለማሰላሰል ማህበረሰቡ የሚያጋጥሙትን ችግሮች ለመጋፈጥ ተስማሚ ቦታዎች ሊሆኑ እንደሚችሉ ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የእውነትን ፍለጋ ሂደት በማበረታታት፣ ከተገለሉ እና ከወጣቶች ጋር ቅርብ በመሆን እና አካባቢን ለመጠበቅ በመስራት፣ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ዛሬ የሰው ልጅ የሚያጋጥሙትን ተግዳሮቶች ለመጋፈጥ አስፈላጊ ቦታዎች ይሆናሉ ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐሙስ ሰኔ 18/2018 ዓ.ም ተናግረዋል።

"ተቋማቶቻችሁ የሚፈለጉት በማህበረሰቡ ዳር ዳር ያሉ ወይም የተገለሉ ሰዎች ስለሚያጋጥሟቸው ኢፍትሃዊ ድርጊቶች ተማሪዎቻችሁን ለማስተማር ብቻ ሳይሆን፣ በአንድነት እና በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረቱ አዳዲስ ሞዴሎችን በማቅረብ የስርዓት ለውጥን ለማስተዋወቅ ዋና መንገዶች እንዲሆኑ መርዳት ነው" ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በሰሜን አሜሪካ ከሚገኙ የኢየሱሳዊያን ማሕበር ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች እና ተወካዮች ጋር በቫቲካን ባደረጉት ስብሰባ ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ እነዚህ ተቋማት አባሎቻቸው የማህበረሰቡን በጣም አንገብጋቢ ጉዳዮች እንዴት እንዲጋፈጡ እንደሚረዱ የሚያሳይ ፍኖተ ካርታ አቅርበዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ከኢየሱሳዊያን ማሕበር አራት ሁለንተናዊ የሐዋርያዊ ምርጫዎች መነሳሻ አግኝተዋል፤ እነዚህም እ.አ.አ በ2019 ዓ.ም የተቋቋሙ እና ለቀጣዮቹ 10 ዓመታት የኢየሱሳዊያንን ማኅበር ሥራ ለመምራት የታለሙ ናቸው።

ምርጫዎቹ የሚከተሉት ናቸው፣ ወደ እግዚአብሔር የሚወስደውን መንገድ ማሳየት፣ ከተገለሉት ጋር መራመድ፣ ከወጣቶች ጋር መጓዝ እና የጋራ ቤታችንን መንከባከብ የተሰኙ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የዘመናት ለውጥ ምዕራፍ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ንግግራቸውን የጀመሩት “ዛሬ የሰው ልጅ የሚያጋጥሙትን በርካታ ተግዳሮቶች” በማጉላት “የዘመናት ለውጥ ምዕራፍ ተብሎ በሚጠራው” ወቅት በማጉላት ነው።

ማህበረሰቦች የበለጠ ዓለማዊ እየሆኑ መምጣታቸውን አጉልተው ገልጸዋል፣ “ብዙዎች ስለ እግዚአብሔር መናገር  ከሕዝብ ማዕቀፍ እና ከሕዝብ ባህል ባሻገር ለማስወጣት ይፈልጋሉ” ወይም የፖለቲካ ሥርዓቶች “የድሆችን፣ የስደተኞችን እና ዓለም የተገለሉ ሰዎችን ጩኸት” አያስተናግዱም ሲሉ በቁጭት ተናግረዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ወጣቶች ብዙውን ጊዜ የተሻለ የወደፊት ተስፋ እንደሌላቸው እና የፕላኔቷ ሀብቶች ለግል ጥቅም፣ ጥቅም ላይ እንደሚውሉ አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል።

እንዲሁም አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) በሰው ልጅ ላይ የሚያሳድረውን እየጨመረ የመጣውን ተጽዕኖት አውስተዋል።

ለስደተኞችና ለጥገኝነት ጠያቂዎች እድሎችን መስጠት

በዚህ ረገድ፣ የኢየሱሳዊያን ማሕበር አራት ሁለንተናዊ ሐዋርያዊ ምርጫዎች እነዚህን ጉዳዮች ለመፍታት እንደሚረዱ ጠቅሰዋል።

ከድሆች ጋር በሚደረገው ጉዞ ጭብጥ ረገድ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ በተለይ “በድህነት ውስጥ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወንድሞቻችንና እህቶቻችን በድህነት በሚኖሩበት በዚህ ወቅት” ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አፅንዖት ሰጥው ተናግረዋል።

ብዙ ሰዎች በጦርነት፣ በሃይማኖታዊ ወይም በፖለቲካዊ ስደት፣ በረሃብ ወይም በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ቤታቸውን ለቀው ለመውጣት እንደሚገደዱ ተናግረዋል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኢየሱሳዊያን ማሕበር ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የጋራ ጥቅምንና አንድነትን ለማስተዋወቅ ብቻ ሳይሆን “ለስደተኞች፣ ለጥገኝነት ጠያቂዎችና ዝቅተኛ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ደረጃ ላላቸው ሰዎች የላቀ ትምህርት ተጠቃሚ እንዲሆኑ እድሎችን ለማቅረብ” እንዲረዱ አጥብቀው ተናግረዋል።

“በዚህ መንገድ፣ በሚኖሩባቸው ማህበረሰቦች ውስጥ የበለጠ ሙሉ በሙሉ መዋሃድ እንዲሁም ሰፊውን የተማሪ አካላት በተለያዩ ልምዶቻቸውና አመለካከቶቻቸው ማበልጸግ ይችላሉ” ሲሉ አክለው ተናግረዋል።

የሰው ሰራሽ አስተውሎት አሉታዊ እና አወንታዊ ውጤቶች

ምንም እንኳን በኢየሱሳዊያን ማሕበር ምርጫዎች ውስጥ የተለየ ጭብጥ ባይሆንም፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ስለ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) ተጽእኖም ተናግረዋል፣ ኮሌጆች እና ዩኒቨርሲቲዎች የዚህ የቴክኖሎጂ እድገት አሉታዊ እና አወንታዊ ውጤቶችን በመፍታት ረገድ ልዩ ሚና ሊጫወቱ እንደሚችሉም ጠቁመዋል። እነዚህ ተቋማት በተለይ “ለቤተክርስቲያኒቱ የማኅበራዊ አስተምህሮ መርሆዎች አዲስ ማበረታቻ መስጠት ይችላሉ” ሲሉ አብራርተዋል።

በወጣቶች ላይ ተስፋን መፍጠር

ከወጣቶች ጋር አብሮ የመሄድን ጭብጥ በተመለከተ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ኮሌጆችና ዩኒቨርሲቲዎች የተሻለ የወደፊት ተስፋን ለማመንጨት ተፈጥሯዊ ቦታዎች መሆናቸውን አጥብቀው ተናግረዋል። ተማሪዎች ብዙውን ጊዜ በሐሳባዊነትና በጉልበት የተሞሉ የትምህርት ሥራቸውን ይጀምራሉ፣ እና በትምህርታቸውና በግንኙነታቸው ዓለምን ወደ ተሻለ ሁኔታ በመቀየር አዲስ የተስፋ ስሜት ያገኛሉ ብለዋል።

“በማህበረሰቦቻችሁ ውስጥ ባሉ ሰዎች መካከል ያንን የተስፋ ስሜት በውይይት፣ በአገልግሎትና በጸሎት እድሎች አማካኝነት ማሳደግ እንድትቀጥሉ እጋብዛችኋለሁ፣ የክርስቶስ ትንሣኤ የመጨረሻው የተስፋ ምንጭ መሆኑን እና ከእርሱ ጋር ሁሉም ነገር የሚቻል መሆኑን ሁልጊዜ አስታውሱ” ብለዋል ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ።

የፍጥረት እንክብካቤ፣ በአርአያነት መምራት

ወደ ፍጥረት እንክብካቤ ጭብጥ በመመለስ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ የኢየሱሳዊያን ማሕበር የሚተዳደሩ ተቋማት “በምሳሌነት ብቻ ሳይሆን በንድፈ ሐሳብ ጭምር እንዲያስተምሩ” አበረታተዋል፣ በተለይም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖዎችን እና “ጥቂቶች የጋራ ጥቅምን ችላ በማለት የተፈጥሮ ሐብቶችን መበዝበዝ" እንዲያቆሙ እንዲሰሩ ጋብዘዋል።

“በካምፓሶቻችሁ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ስለእነዚህ ወቅታዊ አደጋዎች ለማስተማር በምታደርጉት ጥረት እንድትጸኑ፣ እንዲሁም ማህበረሰቦቻችሁ ለሥነ-ምህዳር ዘላቂነት፣ እክብካቤ ማድረግ እና ለእግዚአብሔር ስጦታዎች አመስጋኝነት ምሳሌዎች እንዲሆኑ እንድታበረታቱ እመክራችኋለሁ” ብለዋል።

እውነትን የሚፈልጉ እግዚአብሔርን ይፈልጋሉ

ወደ እግዚአብሔር የሚወስደውን መንገድ የሚያሳየውን ጭብጥ በተመለከተ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ “ምርምር የሚያደርጉ፣ ጥናት የሚከታተሉ እና እውነትን የሚፈልጉ ሰዎች በመጨረሻ እግዚአብሔርን ይፈልጋሉ፣ ቢያውቁትም ባይገነዘቡትም” ብለዋል።

አባላት “እውነት የሆነውን” ማወቅ የሚችሉበት እና በወጣቶች መካከል እየጨመረ ላለው የእግዚአብሔር ረሃብ ምላሽ የሚሰጡበት የትምህርት ተቋማት ማህበረሰቦችን መፍጠር አስፈላጊ መሆኑን አጥብቀው ተናግረዋል።

በዚህ ረገድ፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የኢየሱሳዊያን ማሕበር በመንፈሳዊ ልምምዶች ላይ ሰፊ ተሳትፎ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፣ ምክንያቱም አስፈላጊ ውሳኔዎችን በተመለከተ ግንዛቤን ለመስጠት ይረዳሉ ብለዋል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ንግግራቸውን የጨረሱት የኢየሱሳዊያን ማኅበር - በመስራች የቅዱስ ኢግናሽዬስ ዘ ሎዮላን - "የኢየሱሳዊያን ማሕበር ባህል እንዲቀጥሉ" በመጋብዝ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

26 Jun 2026, 14:19