ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከጣሊያን የዋና ፌዴሬሽን ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከጣሊያን የዋና ፌዴሬሽን ጋር በቫቲካን በተገናኙበት ወቅት   (@Vatican Media)

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ፡ ስፖርት ለአካልና ለመንፈስ መድኃኒት ነው ማለታቸው ተገለጸ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ከጣሊያን የዋና ፌዴሬሽን ጋር በተገናኙበት ወቅት ስፖርት የአካልና የመንፈስ እድገትን በማሳደግ ረገድ ያለውን ጠቀሜታ አወድሰዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐሙስ ዕለት ሰኔ 18/2018 ዓ.ም ከጣሊያን የዋና ፌዴሬሽን አባላት እና የዓለም አቀፍ የዋና ሻምፒዮና ተሳታፊዎች ጋር ተገናኝተዋል።

62ኛው የሴቴ ኮሊ ዋንጫ ከሰኔ 19 እስከ ሰኔ 21/2018 ዓ.ም በሮም በሚገኘው ታሪካዊው የፎሮ ኢታሊኮ የመዋኛ ስታዲየም ይካሄዳል፣ እና ከሚመጣው የአውሮፓ ሻምፒዮና እና የሜዲትራኒያን ጨዋታዎች በፊት የመጨረሻ የማጣሪያ ዝግጅት ሆኖ ያገለግላል።

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በንግግራቸው ስፖርት በትክክል ከቀረበ ለሰውነትና ለመንፈስ መድኃኒት ሆኖ ሊያገለግል እንደሚችል ተናግረዋል።

“የሰውን የተለያዩ ገጽታዎች ያዋህዳል እንዲሁም እንደ ቁርጠኝነት፣ አንድነት እና ታማኝነት ላሉ በጣም አስፈላጊ እሴቶች ይመራቸዋል” ብለዋል።

ከአካላዊ ጤና በተጨማሪ ስፖርት ለመንፈሳዊ ምግብ በተለይም ዋና እድል ይሰጣል ሲሉ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ ተናግረዋል።

"ዋና የሚለማመደው ሰውን በሚከበው አካል ማለትም በውሃ ውስጥ ሲገባ ቢቻ ነው፣ ይህ በምሳሌያዊ አነጋገር ከእናታችን ማህፀን ጀምሮ የቀረጸን አንድ ገጽታ ያስታውሳል፡ መኖር ማለት ከሌሎች ጋር እና በዙሪያችን ካለው አካባቢ ጋር ተስማምተን መንቀሳቀስን መማር ማለት ነው" ብለዋል።

ለክርስቲያኖች፣ ውሃ ጥምቀትን እና በክርስቶስ ያለንን አዲስ ሕይወት ያመለክታል ያሉት ቅዱስነታቸው ርዕሰ ሊቃነ ጳጳስ ሊዮ "በሴቴ ኮሊ" ዋንጫ ውድድር ውስጥ የሚሳተፉ ተሳታፊዎች ከዓለም ዙሪያ የመጡ መሆናቸውን አስታውሰዋል፣ ከቋንቋ ወይም ከባህል በላይ በሆነ ተመሳሳይ ፍላጎት እና እሴቶች የተሞሉ ናቸው ብለዋል።

"ይህ ገጽታ፣ በዓለም አቀፍ የስፖርት ዝግጅቶች የተለመደ፣ የምንፈልገውን የዓለም ምልክት፣ የተስፋ ምልክት ይሰጣል" ብለዋል። "በሕዝቦች መካከል ሰላማዊ ግንኙነት እንዲኖር እና ለወንድማማችነት አስተዋጽኦ ያደርጋል ካሉ በኋላ ቅዱስነታቸው መልእክታቸውን አጠናቀዋል።

 

26 Jun 2026, 14:25