ቅድስት መንበር፡- አረጋውያን እኩል ጥበቃ እና የሥራ መብቶቻቸው ሊረጋገጥ ይገባል ማለቷ ተገለጸ።
የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን
በጄኔቫ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የቅድስት መንበር ቋሚ ታዛቢ ሊቀ ጳጳስ ኤቶሬ ባሌስትሬሮ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የአረጋውያንን ሰብአዊ መብቶች እንዲጠብቁ ያቀረበችውን ጥሪ በድጋሚ ማስተጋባታቸው የተገለጸ ሲሆን በ60ኛ የሰብዓዊ መብቶች መደበኛ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር በዓለም ዙሪያ ያሉ ማኅበረሰቦች መጪውን የስነ ሕዝብ አወቃቀር ለውጥ ለመፍታት ዝግጁ አይደሉም ብለዋል።
እ.ኤ.አ. በ 2030 ፣ ከ6 ሰዎች ውስጥ አንዱ የ60 ወይም ከዚያ በላይ የእድሜ ባለጸጋ ይሆናሉ ፣ በአጠቃላይ 1.4 ቢሊዮን ሰዎች ከ60 አመት እድሜ በላይ እንደሚሆኑ የተገለጸ ሲሆን ይህም አሃዝ እ.አ.አ በ 2050 በእጥፍ ይጨምራል ተብሎ ይጠበቃል ።
በዚህ ለውጥ መካከል ሊቀ ጳጳስ ባለስትሬሮ እንደተናገሩት የአረጋውያን በአካል መድከም እና ክብር በተገቢው አክብሮት እና ተግባራዊ ግምት ውስጥ በማስገባት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ደህንነታቸውን ጨምሮ ማረጋገጥ እንደሚገባ ገልጸዋል።
"ይህ የስነ-ሕዝብ ለውጥ ማህበረሰቦች ለታላላቆቻቸው ምን ያህል ዋጋ እንደሚሰጡ እና እንደሚንከባከቡ የሚያሳይ የሞራል ፈተና ነው" ብሏል።
የህዝቡ እድሜ እየገፋ ሲሄድ ንቁ ዜጎችን በመደገፍ እና የተቸገሩትን በመርዳት መካከል ያሉ ሀብቶችን ወደ ሌላ ቦታ መፈለግ አለባቸው ብለዋል ሊቀ ጳጳሱ፣ ይህ ለውጥ በአረጋውያን ኪሳራ ሊመጣ አይችልም ብለዋል ።
ክብራቸው በእድሜም ሆነ በአካልና በአእምሮ በመድከማቸው ሰብዓዊ መብታቸውን መጠበቅ እንደሚገባ ገልጸዋል።
"የአንድ ሰው ዋጋ በወጣትነት፣ በጉልምስና፣ በአካላዊ ጥንካሬ ወይም ፍጹም ጤንነት ሊገለጽ አይችልም፣ ምክንያቱም በማይለወጥ እውነት ላይ ስለሚገኝ፣ እያንዳንዱ ሰው በእግዚአብሔር መልክና አምሳል መፈጠሩ፣ ይህ እውነታ በጊዜ በራሱ ሊጠፋ የማይችል ነው" ሲል ተናግሯል።
በጄኔቫ የሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት የጳጳሱ ተወካይ አረጋውያንን በኅብረተሰቡ ላይ እንደ ሸክም የሚመለከቱ ፖሊሲዎችን “መወርወር” ተግቢ አይደለም ሲሉ በቁጭት ተናግሯል፤ ከእነዚህም መካከል ራስን ማጥፋት ሕጋዊ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ወይም ራስን ማጥፋት መርዳትን ጨምሮ፣ እነዚህን እና እነዚህን የመሳሰሉ ፖሊሲዎች የአረጋዊያንን ደህንነት ይጋፋሉ ያሉ ሲሆን እነዚህ ፖሊሲዎች አዛውንቶቻችንን ከማክበር ይልቅ "የሞትን ባህል" ያሳድጋሉ ብለዋል።
ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ ሀገራት በጡረታ፣ በጥሬ ገንዘብ ጥቅማ ጥቅሞች እና በጤና እና በማህበራዊ እንክብካቤ አገልግሎቶች የአረጋውያንን ክብር እንዲያስከብሩ ያሳሰቡ ሲሆን አረጋውያን ኑሯቸውን ለማስቀጠል በሰው ኃይል ውስጥ መቆየት ሲገባቸው መድሎውን ለመከላከል በሥራ ገበያ ጥበቃ ሊደረግላቸው ይገባል ብለዋል ።
"የሚገባቸውን እረፍት፣ ጥበባቸውን እና ምክራቸውን ለወጣቱ ትውልድ ለማስተላለፍ እድሉን ተነፍገዋል፣ ይህም ለወጣቱ ትውልድ የወደፊቱን ጊዜ በተስፋ እና በኃላፊነት እንዲገጥሙ ያስችላቸዋል" ብለዋል።
በተለይም ሴቶች በእርጅና ጊዜ የሚከላከሉበትን ማህበራዊ ጥበቃ እና የጡረታ አበል ፍትሃዊ ተጠቃሚ መሆን አለባቸው ይሉ ሲሆን በማጠቃለያው፣ ሊቀ ጳጳስ ባሌስትሬሮ ጠንካራ የማህበራዊ ዋስትና ሥርዓቶችን ለማስጠበቅ፣ በተለይም ብዙ አረጋውያን ብቸኛ የእርዳታ ምንጭ የሚያገኙበትን ቤተሰብ ለመደገፍ፣ ትውልዶች መካከል ትብብር እንዲደረግ አሳስበዋል።
ቅድስት መንበር በማጠቃለያም “ቤተሰብን በሚደግፉ የማህበራዊ ጥበቃ ፖሊሲዎች ላይ የበለጠ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ፣ ቤተሰብን ለማጠንከር እና ለመጠበቅ የሰው ልጅ ማህበረሰብ ዘላቂ መሰረት ነው ብለ በከፍተኛ ሁኔታ እንደ ምታምን" ገለጸዋል።