ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር 

ቅድስት መንበር፡- የቫቲካን ዲፕሎማሲ ለጋራ ጥቅም እንጂ የግል ጥቅምን የምያመልክት አይደለም!

ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር የቅድስት መንበር ዲፕሎማሲ ተስፋን ወደ "ዲፕሎማሲያዊ ተግባር" በመተርጎም ላይ እና የጋራ ጥቅምን ለማገልገል "ባልንጀራ የመሆን" አስፈላጊነት ላይ ያተኮረ ንግግር አድርገዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

"ባልንጀራ መሆን" ለጋራ ጥቅም አገልግሎት የሚሰጠው የዲፕሎማሲ ጥልቅ ትርጉም እንጂ የተለየ ጥቅም አይደለም ሲሉ የተናገሩት ቫቲካን ከመንግሥታት እና ከዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነቶች በበላይነት የሚመሩት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር የቅድስት መንበር ተግባር ከግዛቶች ጋር ያለውን ግንኙነት የሚመራበት አመለካከት እንዴት እንደሆነ ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም በጉባኤው ላይ ባደረጉት ንግግር “በተስፋ ባልንጀራ መሆን፣ የሀይማኖቶች ምስክርነት እና የፖለቲካ በጎ አድራጎት ዲፕሎማሲ” በሚል መሪ ቃል በቀረበ ስብሰባ ላይ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።

በጳጳሳዊው ድርጅት  “ካሪታ ፖለቲካ” (“የፖለቲካ በጎ አድራጎት ድርጅት”) አዘጋጅነት ዝግጅቱ የተካሄደው በቫቲካን አቅራቢያ በሚገኘው በቅዱስ ካሊስቶ ሕንጻ ውስጥ እንደ ነበረ የተገለጸ ሲሆን “ሃይማኖቶች እና ዲፕሎማሲዎች” የተሰኘው ድርጅት ከሰላሳ ዓመታት በፊት የተመሰረተ ተቋም ሲሆን በተለይም ቅድስት መንበር ከተለያዩ አምባሳደሮች ጋር በመተባበር በሀይማኖት ተቋማት መካከል ውይይቶችን ለማበረታታት፣ ለማስተባበር እና ለማጠናከር ያለመ ድርጅት ነው።

እጅግ በጣም "ጠቃሚ" በሚባሉት ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን የጳጳሱ ዲፕሎማሲ ሥራ ወደ ኋላ ማፈግፈግን አይቀበልም እና ድርብ አቀራረብን ይከተላል - አፋጣኝ ቀውሶችን መፍታት እና በተመሳሳይ ጊዜ "የምርጫ ዑደቶችን" የሚያልፍ የረዥም ጊዜ ራዕይ መገንባት ነው ሲሉ ካርዲናል ፖል ጋላገር ተናግረዋል፣ አስረድተዋል።

ይህ ቅንጦት ሳይሆን ስልታዊ አስፈላጊነት ነው፣ ይህም ደግሞ አደጋዎችን ያስከትላል። ከአብዛኞቹ የአለም ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት ማቆየት ቅድስት መንበር "ከአምባገነን መንግስታት ጋር ከመጠን በላይ መስማማት" ወደሚል ግንዛቤ ሊያመራ ይችላል፣ ነገር ግን የዲፕሎማቲክ መገኘት "በሌላ መንገድ ለመድረስ አስቸጋሪ በሆኑ ስርዓቶች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር ብቸኛው መንገድ" ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል።

ተስፋን ወደ “ዲፕሎማሲያዊ ተግባር” መተርጎም

ሊቀ ጳጳስ ጋልገር እንዳሉት መቀራረብ የዲፕሎማሲው እምብርት ነው። "ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ የተለያዩ አገራት አምባሳደሮችን የሹመት ደብዳቤ ሲቀበሉ፣ ከፕሮቶኮል ባሻገር የዘለለ መርህ እያቀረብን ነው" ብለዋል።

የቅድስት መንበር ዲፕሎማሲ “ንቁ ገለልተኝነት” ላይ የተመሠረተ ነው ሲሉ ቫቲካን ከመንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ጋር የምታደርገውን ግንኙነት በበላይነት የሚመሩት ሊቀ ጳጳስ ፖል ጋላገር የተናገሩ ሲሆን ይህ ማለት ግዴለሽነት ሳይሆን ለሰው ልጅ መረጋጋት እና “የጋራ ጥቅም” ከ“ልዩ ጥቅም”፣ ከጂኦፖለቲካዊ ቡድኖች እና ከርዕዮተ ዓለማዊ ማዕቀፎች - “ዛሬን ለመለየት በጣም አስቸጋሪ የሆኑትን” ማለት ነው ሲሉ አብራርተዋል።

ስለ ደጉ ሳምራዊ የወንጌል ምሳሌ በመጥቀስ “ለቆሰለው ሰው ተጨባጭ እና ዘላቂ ኃላፊነት መውሰድ” ማለት በመሆኑ በተግባር አርአያ ይሆናል ሲሉ ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ጠቁመዋል። ይህ በጳጳሳዊ ዲፕሎማሲ ውስጥ ሲንፀባረቅ አንዳንድ ምሳሌዎችን ጠቅሰዋል፣ ለምሳሌ ቅድስት መንበር በዩናይትድ ስቴትስ እና በኩባ መካከል የተፈጠረውን መቀራረብ፣ በኮሎምቢያ የሰላም ሂደት ወይም በትዕግስት ከቬትናምና ከቻይና ጋር ያለውን ግንኙነት በመመሥረት ረገድ የተጫወተችውን ሚና ጠቅሰዋል።

እያንዳንዱ የቅድስት መንበር ጣልቃገብነት የጋራ ጥቅምን ለማስተዋወቅ እና ተስፋን ወደ “የተጨባጭ ዲፕሎማሲያዊ ተግባር” ለመተርጎም ያለመ ነው ብለዋል ሊቀ ጳጳስ ሪቻርድ ፖል ጋላገር። ዝም ብሎ “የገራገር ብሩህ ተስፋ” ሳይሆን “በአደጋ ግምገማ” ላይ የተመሰረተ ተግባር “ትዕግስትን” ውድቅ የሚያደርግ እና ለውይይት ምንም ቦታ የለም ብሎ ማሰብ እና በጣም “አንገባጋቢ” በሆኑ ሁኔታዎች ውስጥ እንኳን ለውጥ ማምጣት አይቻልም ብሎ ማሰብ እንደ ማይገባ ገልጸዋል።

አጣዳፊ እና የረጅም ጊዜ እይታ

የቫቲካን ዲፕሎማሲ በሁለት ጊዜያዊ ደረጃዎች ይሠራል፣ በአንድ በኩል ለአስቸኳይ ድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ይሰጣል፣ ይህ ማለት ለቀውሶች፣ ግጭቶች፣ ሰብአዊ ሁኔታዎች - በሌላ በኩል ደግሞ የረጅም ጊዜ ራዕይን ይመለከታል፥ በምርጫ ዑደቶች ያልተገደበ ነው። "ይህ ቅንጦት አይደለም፣ ነገር ግን ስልታዊ አስፈላጊነት" ያለው ነው፣ ምክንያቱም ያለ ሰፊ ተስፋ፣ መፍትሄዎች ደካማ እንደሆኑ ይቆያሉ ሲሉ ሊቀ ጳጳስ ሪቻርድ ፖል ጋላገር አጽንዖት ሰጥው ተናግረዋል። በጂኦፖለቲካዊ መልክዓ ምድር ውስጥ እየተከሰቱ ያሉ ግጭቶችን እና ውጥረቶችን በመጥቀስ፣ የሽምግልና ችግሮችን እና የ“ዓለም አቀፋዊ መረጋጋት” ውስብስብነትን አምነዋል።

ሊቀ ጳጳስ ጋልገር በተጨማሪም ፈጣን የቴክኖሎጂ እድገቶች እና የስነ-ምህዳር ቀውስ ተግዳሮቶች ላይ አጽንኦት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን፣ ይህም "አዲስ የትብብር ማዕቀፎች" በአንድ ሀገር ሊፈጠሩ የማይችሉ፣ ነገር ግን ብዙውን ጊዜ ለመተግበር አስቸጋሪ ናቸው። እነዚህ ጉዳዮች ለባለብዙ ወገንነት “አበረታች” ሊሆኑ እንደሚችሉ ጠቁመዋል፣ ነገር ግን ሁልጊዜ እንደዛ አይደለም ብለዋል።

የንግግር ፣ የማዳመጥ እና የሞራል ሁኔታዎች የምያስከፍሉት ዋጋ

ከአብዛኞቹ የአለም ሀገራት ጋር ያለውን ግንኙነት ማቆየት አንዳንድ ጊዜ “ለአምባገነን መንግስታት በጣም ተስማሚ ነው” ተብሎ ሊወሰድ ይችላል ሲሉ የተናገሩት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ሆኖም፣ ዲፕሎማሲያዊ መገኘት “ለመድረስ አዳጋች በሆኑ” ሥርዓቶች ላይ ተጽዕኖ ለማሳደር “ብቸኛው መንገድ” ነው ብለዋል።

የቅድስት መንበር ሥነ ምግባራዊ ሥልጣን—ከቁሳዊ ፍላጎቶች እጦት የመነጨ—የሥነ ምግባር መርሆችን አስፈላጊነት ለማስታወስ ያስችለዋል “በማይመች ጊዜም እንኳን” ሲሉ ሊቀ ጳጳስ ጋላገር ጠቁመዋል። ነገር ግን ማዳመጥ “ሁልጊዜ ዋስትና የለውም”፣ ምክንያቱም የይግባኝ ጥሪዎች የማይሰሙ ሊሆኑ ስለሚችሉ፣ በተለይም “ወዲያውኑ ጂኦፖለቲካዊ ፍላጎቶች” ጋር ሲጋጩ ሲሉ ገለጸዋል።

ዲፕሎማሲያዊ ውሳኔዎችም “ከፍተኛ የሞራል ዋጋን” ሊያስከትሉ ይችላሉ፣ “ፍፁም ጥሩ እና ፍፁም ክፉ” መካከል የመምረጥ ጉዳይ እምብዛም አይደለም ሲሉ የተናገሩት ሊቀ ጳጳሱ ከዚህ አንፃር፣ ሁኔታዎች “ጠንካራ አቋም” የሚጠይቁ ከሆነ ገለልተኝነት እንደ እንቅፋት ሊታይ ይችላል፣ ነገር ግን መንገዶችን ክፍት ማድረግ በመጨረሻ “ከህዝባዊ ውግዘቶች የበለጠ ውጤታማ ጣልቃገብነቶች” ሊያስከትል ይችላል የሚለው እምነት ማዕከላዊ ነው ብለዋል ሊቀ ጳጳስ ጋላገር።

ፍልሰት፡ ሰላም፡ የባለ ብዙ ጎን ፍላጎቶች

ለውይይቱ ከቀረቡ ርእሶች መካከል ቫቲካን ከተለያዩ አገራት መንግሥታት እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች  የምታደርገውን ግንኙነት የሚመለከተው የቅድስት መንበር ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ የሆኑት ሊቀ ጳጳስ ፖል ሪቻርድ ጋላገር ይህ ጉዳይ መሰረታዊ መንስኤዎችን በመተንተን እና ድንገተኛ ሁኔታዎችን ወደ እድሎች ለመቀየር በሚያስችል “በአጠቃላይ እይታ” መቅረብ አለበት ብለዋል።

ብዙውን ጊዜ በቀድሞ ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ይጠቀሱ የነበሩትን የትጥቅ ግጭቶች እና “የሦስተኛው ዓለም ጦርነት ብልጭታዎች መታየት መጀመራቸውን” በተመለከተ ሊቀ ጳጳስ ሪቻርድ ሲናገሩ ከጦርነት አለመኖር የዘለለ እና በሕዝቦች መካከል ፍትሃዊ ግንኙነቶችን ለመፍጠር የሚያተኩር “የሰላም ሥነ-መለኮት” እንዲዳብር ጠይቀዋል።

አክለውም በሃይማኖት ተቋማት መካከል የሚደርጉ ውይይቶች ለርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዲፕሎማሲ ቁልፍ ቦታ ሆኖ እንደሚቀጥል፣ የብዝሃ ወገንተኝነትን ማስተዋወቅ - እንደ ርዕዮተ ዓለም ሳይሆን እንደ እምነት፣ “ዓለም አቀፍ ፈተናዎች፣ ከወረርሽኙ እስከ የአየር ንብረት ቀውስ፣ ብቻውን ሊጋፈጡ አይችሉም" ብለዋል ።

 

15 Oct 2025, 15:13