የሲኖዶሳዊነት ሂደት አስተባባሪ አባላት የኢዮቤልዩ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት የሲኖዶሳዊነት ሂደት አስተባባሪ አባላት የኢዮቤልዩ ጸሎት ሥነ-ሥርዓት 

የሲኖዶሳዊነት ጉዞ አስተባባሪዎች ግንኙነቶች በክርስቶስ አንድ ሊሆን እንደሚገባ አሳሰቡ

የኢዮቤልዩ በዓላቸውን ለማክበር ወደ ሮም የመጡ ሁለት ሺህ የሚጠጉ የሲኖዶሳዊነት ሂደት አስተባባሪ አባላት በቫቲካን ባደረጉት የጋራ ውይይት የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ማድረግ እንደሚገባ ገለጹ።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የኢዮቤልዩ በዓላቸውን ከጥቅምት 14-16/2018 ዓ. ም. ድረስ በሮም በማክበር ላይ የሚገኙ የካቶሊካዊ ሀገረ ስብከቶች የሐዋርያዊ እና ፋይናንስ አገልግሎት ጽሕፈት ቤቶች ተወካዮች በሮም ባካሄዱት የጋራ ውይይት የእርስ በርስ ግንኙነታቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ አንድ ማድረግ እንደሚገባ ገለጹ።

ከዓለም ዙሪያ ወደ ሮም ንግደት የሲኖዶሳዊነት ሂደት አስተባባሪ አባላት ዓርብ ጥቅምት 14/2018 ዓ. ም. ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ጋር ከመገናኘታቸው በፊት ባደረጉት ውይይት ስለወደፊት ተስፋ፣ ቀጣይነት ባላቸው ችግሮች፣ ሲኖዶስነት በቤተ ክርስቲያን እና በዓለም ውስጥ በሚሉት ርዕሦች ላይ ተወያይተዋል።

ውይይቱ በሲኖዶሳዊነት መንፈስ በመታገዝ በተስፋ የተሞላው የወደፊታ እይታ ላይ ምን ማድረግ እንደሚገባ ያመልካተ ሲሆን፥ ከአንዳንድ እንቅፋቶች ባሻገር የአባላቱ ውይይት “እኔ እና እኛ” ፣ “አንድነት እና ወጥነት” ፣ “እንክብካቤ እና የወንጌል ተልዕኮ” በሚሉት ር ዕሦች ላይ ያተኮረ እነደነበር ተመልክቷል። ውይይቱ በተጨማሪም በማኅበራዊ ግንኙነት ውስጥ ባለው እውነተኛ የግንኙነቶች ተሃድሶ ጥሪ፣ በማኅበራዊ ቡድኖች መካከል ያሉ ጥልቅ ችግሮችን የሚያወግዝ እና “አንድ መሆን” የሚለውን የኢየሱስ ክርስቶስን ጥሪ የሚያሳድግ እንደ ሆነ ታውቋል።

እነዚህ ርዕሦች የሲኖዶሳዊነት ሂደት አስተባባሪ አባላት ጥቅምት 14/2018 ዓ. ም. በጳውሎስ ስድስተኛ አዳራሽ ውስጥ በስብሰባቸው መክፈቻ ላይ ከዳሰሷቸው ዋና ጭብጦች መካከል ጥቂቶቹ እንደ ነበሩ ታውቋል። በስብሰባው መክፈቻ ላይ ንግግር ካደረጉት መካከል የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ግሬች፣ ካርዲናል ግሬጎርዝ ራይሽ በፖላንድ የሎዶ ከተማ ሊቀ ጳጳስ፣ ሚጌል ደ ሳሊስ አማራል፥ በፖርቹጋል የነገረ መልኮት ሊቅ እና የቅዱስ መስቀል ዩኒቨርሲቲ የቤተ ክርስቲያን ጥናት ተባባሪ ፕሮፌሰር እና ማርያና አፓሬሲዳ ቬናቾ፥ በብራዚል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚሽን እና የሲኖዶሱ ዋና ጽሕፈት ቤት የአፈጻጸም ምዕራፍ አባል የተገኙ ሲሆን፥ የስብሰባ ክፍለ ጊዜን የመሩት አቡነ ሉዊስ ማሪን ደ ሳን ማርቲን፣ የሲኖዶሱ ዋና ጽሕፈት ቤት ምክትል ጸሐፊ እንደ ነበሩ ታውቋል።

በክርስቶስ ላይ የተመሠረተ ተስፋ

የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ጸሐፊ ብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ግሬች ለስብሰባው ተሳታፊዎች ሰላምታቸውን ሲያቀርቡ ባደረጉት ንግግር፥ ቻርለስ ፔጉይ በጻፈው “የተስፋ ምስጢር” በሚለው መጽሐፋቸው ውስጥ “እምነት ሁሉን ያያል፣ ተስፋ የሚሆነውን ይመለከታል፣ ፍቅርም ሁሉንም ይወዳል” የሚለውን የሦስት የነገረ መለኮት ሊቆች የበጎነት ራዕይዎችን አስታውሰዋል።

ብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ግሬች ለስብሰባው ተሳታፊዎች እንደተናገሩት፥ ፍቅር “ስሜት” ብቻ ሳይሆን ክርስትናን በተጨባጭ የምንኖርበት መንገድ እንደሆነ አስረድተው፥ ቤተ ክርስቲያን ፍጹምነትን ሳትጠብቅ እውነታን መቀበልን እንደምትመርጥ ገልጸው፥ ይህም “በአሁን ጊዜ በሕይወት የመቆየት ውሳኔ እና አንድነት ማለት ወጥነት ማለት እንዳልሆነ የሚያስገነዝብ የመንፈሳዊነት ብስለት ምልክት ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

“ፍቅር ከእምነት ጋር የተገናኘ ነው” ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ማርዮ ግሬች፥ “ፍቅር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ከሰው በላይ መለኮታዊ የሆነውን ነገር የምናይበት መንገድ ነው” ሲሉ ተናግረው፥ ይህም “የጨለመ ተስፋ ሳይሆን የእውነታው ግልጽ እይታ ነው” ሲሉ በማስረዳት፥ “የሲኖዶሳዊነት ጉዞ የሚጀምረው በኅብረተሰቡ የተገለሉ ሰዎች ጩኸት በማዳመጥ ነው” ብለው፥ ለቻርለስ ፔጉይ ተስፋ ማለት ወደፊት የሚመጣው ነገር ማረጋገጫ እና በጋራ እይታ ላይ የተመሠረተ በመሆኑ እራሳችን የምንገነባው ሳይሆን በራሱ እንዲፈጸም የመተው ዝንባሌን የሚጠይቅ መሆኑን አስረድተዋል።

የሲኖዶሳዊነት ሂደት አስተባባሪ አባላት ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት
የሲኖዶሳዊነት ሂደት አስተባባሪ አባላት ጉባኤ የመክፈቻ ሥነ-ሥርዓት

“ለድሆች የቆመች ድሃ ቤተ ክርስቲያን”

በፖላንድ የሎዶ ከተማ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ ካርዲናል ግሬጎርዝ ራይሽ በሲኖዶሳዊነት ላይ በተገለጡ ሦስት ዋና ዋና ርዕሦች ላይ በማትኮር፥ የመጀመሪያው በ “እኔ” እና “እኛ” በሚለው ላይ ያለውን ልዩነት በማስመልከተ ገለጻ አድርገዋል። ሲኖዶሳዊነት የእርስ በርስ ግንኙነት መታደስን እንደሚጠይቅ የገለጹት ካርዲናል ግሬጎርዝ ራይሽ፥ ዘመናዊው ዓለምን እውነተኛ እና ዘላቂ ግንኙነት የሚያሰጋው መሆኑን ተናግረዋል። ይህን ለመረዳት የሚቻልበት ብቸኛው ትስስር ተወዳዳሪነት እንደሆነ አስረድተዋል።

ሁለተኛው በአንድነት እና በመመሳሰል መካከል ያለው ችግር መሆኑን ተናግረው፥ ቤተ ክርስቲያን በአንድ በኩል አንድነትን ስትገልጽ በሌላ በኩል ልዩነትን ካለመቀበል የሚመጣ የመከፋፈል ፈተና ውጤት እንደሚሆን አስረድተዋል። በንግግራቸው ቅዱስ አጎስጢኖስን እና ቅዱስ ፍራንሲስ ደ ሴልስን ያስታወሱት ብጹዕ ካርዲናል ራይሽ፥ ቤተ ክርስቲያንን በብዙ የተለያዩ አበቦች የተሞላ ለምለም የአትክልት ሥፍራ ጋር አነጻጽረው፥ ልዩነት በራሱ የማይከፋፈል፥ ትእቢት እና ኃይልን ያለ አላግባብ መጠቀም የሚከፋፈል መሆኑን አስረድተዋል።

የወንጌል አገልግሎት እና የጋራ ካህናት እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው

ብጹዕ ካርዲናል ራይሽ ስለ እርስ በርስ ግንኙነት መታደስ በማስመልከት የተናገሩትን መሠረት በማድረግ  ንግግር ያደረጉት ፕሮፌሰር ደ ሳሊስ አማርል፥ የእርስ በርስ ግንኙነት ደጎች እንድንሆን የሚጋብዝ ብቻ ሳይሆን የሞራላዊነትን መልዕክት የሚቀንስ መሆኑ በመግለጽ፥ የእርስ በርስ ግንኙነት የሲኖዶሳዊነትን ጥልቅ ትርጉም እንደገና ለማግኘት የቀረበ ጥሪ ነው” ሲሉ አስገንዝበዋል።

ፖርቹጋላዊው የነገረ-መለኮት ሊቅ ፕሮፌሰር ደ ሳሊስ አማርል፥ ከቅዱሳት ምስጢራት በሚገኙ ግንኙነቶች ላይ የተመሠረቱ በርካታ እርምጃዎችን ዘርዝረው፥ “እግዚአብሔር ራሱ በእኛ እና በእርሱ መካከል ያቋቋመው ትስስር” ነው ሲሉ አስረድተዋል። በቅድሚያ የጥምቀት ምስጢር እያንዳንዱን ሰው ወደ አንድነት የሚጠራ፣ ኃይልን የሚሰጥ እና ኃላፊነት በሚሰማው የቤተሰብ እና የወንድማማችነት ግንኙነት በቤተ ክርስቲያን ሕይወት ውስጥ እጅግ አስፈላጊ የሆነ ትስስር የሚፈጥር እንደሆነ አስረድተዋል።

ከዚያም ቀጥሎ የክኅነት ምስጢር ሌሎች እንደ ሚስዮናዊ ደቀ መዛሙርት ሆነው እንዲያድጉ በመርዳት ላይ ያተኮረ ልዩ አገልግሎት እንደሆነ በማስረዳት፥ “ድነት ከውስጣዊ እውቀት የሚመነጭ ሳይሆን ነገር ግን ከውጭ የመጣ እና በእምነት በኩል በምንሰማው ቅዱስ ቃል የሚሰጠን ስጦታ ነው” ሲሉ አስገንዝበዋል።

“የአገልግሎት እና የጋራ ክኅነት እርስ በርስ የሚደጋገፉ ናቸው ያሉት” ፕሮፌሰር ደ ሳሊስ አማርል፥ ይህም ማለት በቤተ ክርስቲያን ማኅበረሰብ ውስጥ ማንም ሰው ራሱን ችሎ የቆመ አለመሆኑን ገልጸው፥ ይህ ጽንሰ-ሃሳብ የቤተ ክርስቲያንን መዋቅር ሕያው ግንኙነት ማግኘት እንዳለበት እና ወደ ተራ ድርጅትነት መውረድ እንደሌለበት ተናግረዋል።

በስብሰባው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዓባላት
በስብሰባው መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የሲኖዶሱ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዓባላት

ሲኖዶሳዊነት የክፍፍል ችግሮችን ለመቅረፍ ያግዛል

በብራዚል የብሔራዊ አስተባባሪ ኮሚሽን እና የሲኖዶሱ ዋና ጽሕፈት ቤት የአፈጻጸም ምዕራፍ አባል ማርያና አፓሬሲዳ ቬናሲዮ በበኩላቸው፥“ሲኖዶሳዊት ቤተ ክርስቲያን በሕዝቦች መካከል እንደ ብርሃን ታበራለች” በማለት የተናገሩትን የነፍስሔር የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ የቅርብ ጊዜውን የጳጳሳት ጉባኤ የመጨረሻ ሠነድ መግለጫ በመጥቀስ ባደረጉት ገለጻ፥  “ሲኖዶሳዊነት ማኅበራዊ ትንቢት ነው” ብለዋል። ይህም የቤተ ክርስቲያን መዋቅራዊ ሞዴል ብቻ ሳይሆን፥ የኑሮ እና የድርጊት መንገድ እንደሆነ ገልጸው፥ “እኔ” ከሚል አስተሳሰብ “እኛ” የሚለውን የቤተ ክርስቲያን ማንነት የሚገልጽ መሆኑን አስረድተዋል።

ማርያና አፓሬሲዳ ቬናሲዮ የአገራቸውን የብራዚል ምሳሌ በመጥቀስ እንደተናገሩት፥ በሲኖዶሱ የመጀመሪያ ምዕራፍ ወቅት ብዙ ሰዎች ለመጀመሪያ ጊዜ በቤተ ክርስቲያን ተሰሚነት እንዳላቸው መሰማታቸውን ተናግረው፥ ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 13ኛ “እኔ ወደድኳችሁ” በሚለው ሐዋርያዊ ማሳሰቢያቸው፥ “ጎጂ የሆነ ኢኮኖሚያዊ አምባገነንነትን የሚቃወም መንገድ እንደሆነ መናገራቸውን አስታውሰዋል።

የሲኖዶሳዊነት ውይይት በቤተ ክርስቲያንም ሆነ በኅብረተሰብ ውስጥ ለሚታየው የመከፋፈል ፈተና  መድኃኒት ሆኖ እንደሚያገለግል፥ “አንድነት ግጭትን ያስወግዳል በሚለው መሠረታዊ መርህ መሠረት የተለያዩ ሃሳቦችን እና አቋሞች በሚያጣምሩ ፍሬያማ ውይይቶችን ላይ መሳተፍ ይቻላል” ሲሉ ተናግረዋል።

ማርያና አፓሬሲዳ ቬናሲዮ በንግግራቸው ማጠቃለያ፥ ቤተ ክርስቲያን ከወንጌል አዋጅ ማዕከላዊነት የሲኖዶሳዊነት መንገድን ብቻ ሳይሆን የማንነት መግለጫ የሆነውን ሕያው ምላሽ እንድትቀበት መጠራቷን እና ይህም “አንድ መሆን” ለሚለው የኢየሱስ ክርስቶስ ጥሪ ሕያው ምላሽ እንደሆነ አስረድተዋል።

 

27 Oct 2025, 16:18