የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ከየጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር በሮም የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፔትሮ ፓሮሊን ከየጣሊያን ጠቅላይ ሚንስትር ጆርጂያ ሜሎኒ ጋር በሮም   (@VATICAN MEDIA )

ካርዲናል ፓሮሊን፣ ቅድስት መንበር በሰላም ቦርድ ውስጥ እንደ ማትሳተፍ ገለጹ!

ቅድስት መንበር “በልዩ ባህሪዋ ምክንያት የሰላም ቦርድ ውስጥ አትሳተፍም፣ ይህም በግልጽ የሌሎች መንግስታት ባህሪይ ግን አይደለም" ሲሉ የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የተናገሩ ሲሆን የላተራን ስምምነት የተፈረመበትን አመታዊ በዓል ምክንያት በማድረግ በሮም ከጣሊያን መንግሥት ጋር በተደረገው የሁለትዮሽ ስብሰባ ጎን ለጎን፣ በቅድስት መንበር የጣሊያን ኤምባሲ መቀመጫ በሆነችው ፓላዞ ቦሮሜኦ፣ ይህንን አቋም ተናግረዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

ምላሽ መስጠት አስፈላጊ ነው

በሰላም ቦርድ ውስጥ እንደ ታዛቢ ብቻ ተሳትፎ ማድረግን በተመለከተ ጋዜጠኞች ላቀረቡላቸው ጥያቄ ምላሽ ሲሰጡ፣ ካርዲናል ፓሮሊን “በተወሰነ ደረጃ ግራ የሚያጋቡን ነጥቦች አሉ። ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው አንዳንድ ወሳኝ ነጥቦች አሉ ሲሉ ተናግረዋል፣ በስብሰባው ላይም የጣሊያን ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሰርጂዮ ማታሬላ ተገኝተዋል።

ካርዲናል አክለውም “አስፈላጊው ነገር ምላሽ ለመስጠት ሙከራ እየተደረገ ነው። ሆኖም ግን፣ ለእኛ መፍትሄ ሊሰጣቸው የሚገቡ አንዳንድ ወሳኝ ጉዳዮች አሉ” ሲሉ የቫቲካን ዋና ጸኃፊ ካርዲናል ፒዬትሮ ፓሮሊን የተናገሩ ሲሆን “አንድ ስጋት” አለ፣ ይህም “በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሁሉም በላይ እነዚህን የችግር ሁኔታዎች የሚያስተዳድረው የተባበሩት መንግስታት መሆን አለበት። ይህ አጥብቀን ከጠየቅናቸው ነጥቦች አንዱ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

ስለ ዩክሬን አሉታዊ አመለካከት

የቫቲካን ዋና ጸኃፊ የሆኑት ካርዲናል ፓሮሊን ግጭቱ ከተከሰተ  ከአራት ዓመታት በፊት በዩክሬን ስላለው ጦርነት ስጋታቸውን ገልጸዋል። ይህ በኪየቭ እና በሌሎች ከተሞች በኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ በሚሰነዘሩ ከባድ የቦምብ ጥቃቶች የታጀበ ጥቃት የተጀመረበት አራተኛውን አመት እየዘከርን እንገኛለን ብለዋል።

"ዩክሬንን በተመለከተ" እንደ ካርዲናል ገለጻ፣ "ከፍተኛ የሆነ ተስፋ አስቆራጭ ነገር አለ። በሁለቱም በኩል ስለ ሰላም እውነተኛ እድገት እንዳለ አይመስለንም፣ እና ከአራት ዓመታት በኋላ አሁንም በዚህ ወቅት ማለትም በጦርነት ሁኔታ ውስጥ ሆነን መገኘታችን አሳዛኝ ነው… እነዚህ ውይይቶች የተወሰነ እድገት ሊፈጥሩ እንደሚችሉ ተስፋ እናደርጋለን፣ ነገር ግን ለእኔ ብዙ ተስፋ እና ብዙ አዎንታዊ ነገር አለ ብዬ አላስብም" ብለዋል።

ካርዲናል ፓሮሊን በቤተክርስቲያኗ ልብ ውስጥ ላሉ ጉዳዮች ጣሊያን ለሰጠችው ትኩረት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በሁለትዮሽ ስብሰባው ወቅት መንግስት ለቤተክርስቲያኗ ልብ ቅርብ ለሆኑ ብዙ ጉዳዮች ላደረጋቸው ትኩረት በቅድስት መንበር በኩል "ከሁሉም በላይ የምስጋና መግለጫ ተሰጥቶ" እንደነበር አፅንዖት ሰጥተው ገልጸዋል።

ካርዲናሉ ከጠቀሳቸው ጉዳዮች መካከል "ማህበራዊ ተፈጥሮ ያላቸው፣ ለቤተሰብ እርምጃዎች እና ድንጋጌዎች፣ የትምህርት ጉዳይ፣ የአካል ጉዳት ጉዳይ እና የእስር ቤቶች ጉዳይ። የCEI [የጣሊያን ጳጳሳት ጉባኤ]ን በቀጥታ የሚመለከቱ እና የትኞቹ እድገት እንደተደረገባቸው የስራ ቡድኖች ያሉባቸው ጉዳዮች" ይገኙበታል።

 

18 Feb 2026, 16:41