ቅድስት መንበር፣ ውጫዊ ህዋ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በጦር መሳሪያ ሊታጠቁ አይገባም አለች! ቅድስት መንበር፣ ውጫዊ ህዋ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በጦር መሳሪያ ሊታጠቁ አይገባም አለች!  (AFP or licensors)

ቅድስት መንበር፣ ውጫዊ ህዋ እና ሰው ሰራሽ አስተውሎት በጦር መሳሪያ ሊታጠቁ አይገባም አለች!

ቅድስት መንበር የጦር መሳሪያ በጀት በከፍተኛ ሁኔታ በተስፋፋበት በአሁን ወቅት የጦር መሳሪያ ትጥቅ የማስፈታት የሞራል ግዴታን እንደገና ደግማ ትናገራለች፣ እናም “የሰው ልጅ ሁሉ ግዛት” ሆኖ መቆየት ያለበትን የውጪ ህዋ ወታደራዊ እንቅስቃሴ ከፍተኛ ጉዳት የምያስከትል መሆኑን በመግለጽ አስጠንቅቃለች።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

በቫቲካን የቅድስት መንበር የባለብዙ ወገን ዘርፍ ጽ/ቤት ምክትል ፀሐፊ የእኔታ አባ ዳንኤል ፓኮ የቤተክርስቲያኒቱን የጦር መሳሪያ ትጥቅ የማስፈታት ጥሪ አድሰዋል።

ረቡዕ ዕለት የካቲት 17/2018 ዓ.ም በጄኔቫ በተካሄደው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሚመራው የ2026 ዓ.ም የጦር መሳሪያ ትጥቅ ኮንፈረንስ ላይ ንግግር ሲያደርጉ፣ የሰው ልጅ “ወሳኝ በሆነ ወቅት ላይ ነው” ብለዋል፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ በጥር ወር ጦርነት “ወደ ፋሽንነት ተመልሷል፣ እና ለጦርነት ያለው ቅንዓት እየተስፋፋ ነው” በማለት ያስጠነቀቁትን አስታውሰዋል።

የእኔታ አባ ዳንኤል ፓኮ በኃይል ላይ የተመሰረተ ዲፕሎማሲ ውይይትን እና የጋራ መግባባትን መፈለግን እየተካ መሆኑን በምሬት ተናግረዋል፣ ይህ ለውጥ የጦር መሳሪያ ትጥቅ ኮንፈረንስን ጨምሮ ስለ ጦር መሳሪያ ትጥቅ ማስፈታት የሚደረጉ የብዙ ወገን ውይይቶችን እንዳዳከመ ተናግረዋል።

የጦር መሳሪያ ትጥቅ ማስፈታት “የሞራል ግዴታ” እንደሆነ በመግለጽ የጦር መሳሪያ ትጥቅ ማስፈታትን ሌሎችን ለመጉዳት ዳግመኛ ጥቅም ላይ እንዳይውል የሚያረጋግጥ ነው ብለዋል።

“ትጥቅ መፍታት በራሱ ግብ አይደለም።” ብለዋል። “መተማመንን ለመገንባት እና ፍትሃዊ እና ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ቁልፍ መሳሪያ ነው፣ ስለዚህም ለሰው ልጅ እድገትን ለማበረታታት ወሳኝ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

የእኔታ አባ ዳንኤል ፓኮ የቅድስት መንበር የኑክሌር የጦር መሣርያ መስፋፋትን ተቃውሞ በድጋሚ ገልጸው፣ ለሰው ልጅ ለሚፈጥሩት “የህልውና ስጋት” ያላቸውን ስጋት ገልጸዋል።

የኑክሌር የጦር መሣርያ መከላከያ፣ ዓለም አቀፍ ግንኙነቶች በፍትህ፣ በሕግ እና በመተማመን ላይ ሳይሆን በኃይል ስጋት ላይ የተመሰረቱ መሆን አለባቸው በሚለው ምክንያታዊ ያልሆነ እምነት ላይ የተመሠረተ ነው ብለዋል።

“አደገኛው የጥንቃቄ መንገድ” ሁሉንም የዲፕሎማሲ ጥረቶች ሲተካ፣ “ሰብአዊነት እና ፕላኔታችን በአጠቃላይ ወደ ውድመት እና ጥፋት ጫፍ የመገስገስ አደጋ አለው” ብለዋል።

በዚህ አውድ፣ የእኔታ አባ ዳንኤል ፓኮ የኑክሌር ጦር መሣሪያ ያላቸው አገሮች የጦር መሣሪያዎቻቸውን ለመቀነስ እና በመጨረሻም ለማስወገድ በቅን ልቦና ድርድር እንዲሳተፉ የቅድስት መንበርን ግብዣ ደግመው ገልጸዋል።

የቅድስት መንበር ተወካይ ውጫዊው ቦታ ማለትም ህዋ በፍጥነት ለታላቅ የኃይል ግጭት መድረክ እየሆነ መሆኑን አሳስበው ነበር።

“የውጭ ህዋ ወታደራዊ ኃይል መጠቀም ቀድሞውኑ እውን ሆኗል፣ እናም እምነትን ለመገንባት እና የጋራ ደህንነትን እና ኃላፊነትን ለማሳደግ ተጨባጭ እርምጃዎች ካልተወሰዱ በስተቀር ወደ ጦር መሳሪያ ማዘዋወር ይመራል” ብለዋል።

በውጫዊ ህዋ ውስጥ የሚፈጠር ማንኛውም ዋና ግጭት ለትውልዳችን እና ለወደፊቱ አስከፊ ውጤቶች ይኖረዋል ሲሉ አክለው የገለጹ ሲሆን “ስለዚህ የውጪ ህዋ ፍለጋ እና አጠቃቀም ለሰላማዊ ዓላማዎች ብቻ ጥቅም ላይ እንዲውል፣ እ.አ.አ በ1967 የውጫዊው ህዋ ስምምነት መሠረት እንደ “የሁሉም የሰው ልጅ ግዛት” ሆኖ እንዲቆይ ማድረግ አስፈላጊ ነው” ብለዋል።

ከዚያም የእኔታ አባ ዳንኤል ፓኮ ወደ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) የጦር መሳሪያ ሐሳባቸውን ሲያዞሩ AI ጦርነቶች የሚካሄዱበትን መንገድ እያበላሸ መሆኑን የጠቀሱ ሲሆን “ራስ ገዝ የሆኑ መሳሪያዎች ተዋጊዎች ሲሆኑ፣ የሞራል ፍርድ እና የስነ-ምግባር ውሳኔ አሰጣጥ ልዩ የሰው ልጅ አቅም ይጠፋል፣ የኃላፊነት ሸክምም ይጠፋል፣ የግጭት ገደቡን በአደገኛ ሁኔታ ያሰፋል" ሲሉ ተናግረዋል።

ስለዚህ ሰዎች የሁሉም የኃይል አጠቃቀም ቁጥጥር ዋና አካል መሆን አለባቸው ሲሉ የተናገሩ ሲሆን ገዳይ የራስ ገዝ የጦር መሳሪያዎች ስርዓቶችን ማምረት እና አጠቃቀም ላይ እገዳ እንዲጣል ጥሪ አቅርበዋል።

በማጠቃለያው የእኔታ አባ ዳንኤል ፓኮ የጦር መሳሪያ ማስፈታት ኮንፈረንስ ሀገራት አዳዲስ የጦር መሳሪያ መድረኮችን እንዴት እንደሚጠቀሙ ለማረጋገጥ መንገዶችን እንዲፈልግ አሳስቧል፣ የጦር መሳሪያን ለመገደብ በሚደረጉ ስምምነቶች ደግሞ ወታደራዊ ወጪን ማስፋፋትን እንዲያስወግዱ አሳስቧል።

“የሰው ልጅ ወደ እውነተኛ እና ዘላቂ ሰላም እንዲሸጋገር፣ ይህ የጦር መሳሪያ ኮንፈረንስ ለሁሉም ህዝቦች የጋራ ጥቅም ሲባል ተጨባጭ እና ዘላቂ የጦር መሳሪያ ስምምነቶችን ማሳካት ወሳኝ ነው” ካሉ በኋላ ንግግራቸውን አጠናቀዋል።

27 Feb 2026, 15:35