ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቸርኒ፤ ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቸርኒ፤  (@Vatican Media)

“የሰው ልጅ ታላቅነት” የተሰኘው ሐዋርያዊ መልዕክት ጥልቅ የሲኖዶሳዊነት ይዘት አለው ተባለ

በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቸርኒ፥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን በማካሄድ ላይ ለሚገኙት የስዊዘርላንድ ብጹዓን ጳጳሳት ግንቦት 24/2018 ዓ. ም. የቪዲዮ መልዕክት ልከዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ፥ ሰኞ ግንቦት 17/2018 ዓ. ም. ይፋ ባደረጉት “የሰው ልጅ ታላቅነት” (Magnifica humanitas) በሚለው የመጀመሪያ ሐዋርያዊ መልዕክታቸው ላይ በማሰላሰል በላኩት የቪዲዮ መልዕክት፥ “ሠነዱ መዋቅራችንን፣ የአሠራር መንገዳችንን እና የስብከተ ወንጌል አቀራረባችንን በሚገባ እንድናጤን ይጠይቀናል” ሲሉ ገልጸዋል።

በቅድስት መንበር የሰው ልጅ ሁለንተናዊ ዕድገት ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤት አስተባባሪ ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቸርኒ፥ ጠቅላላ ጉባኤያቸውን በኤንሲዴልን ገዳም በማካሄድ ላይ ለሚገኙ የስዊዘርላንድ ብጹዓን ጳጳሳት ግንቦት 24/2018 ዓ. ም. የቪዲዮ መልዕክት ልከዋል።

ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቸርኒ በመልዕክታቸው ላይ እንደገለጹት፥ እነዚያ ጥረቶች ከ“ሰው ሠራሽ አስተውሎት” ጳጳሳዊ ኮሚሽን እና “የሰው ልጅ ታላቅነት” ከተሰኘው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሐዋርያዊ መልዕክት ጋር የተያያዙ ናቸው” ሲሉ አስረድተዋል።

ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቸርኒ ለስዊዘርላንድ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ የላኩት መልዕክት፥ “የሰው ልጅ ታላቅነት” በሚለው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ሐዋርያዊ መልዕክት ላይ ያተኮረ ሲሆን፥ ቅዱስነታቸው በቅርቡ ያቋቋሙትን እና ከሰው ሠራሽ አስተውሎት ጋር የተያያዙ ጉዳዮችን እንዲከታተል አደራ በተሰጠው ጳጳሳዊ ኮሚሽን ላይ አፅንዖት ሰጥተዋል።

“ከጅምሩ እጅግ አስፈላጊ ጥያቄ ቀርቦልናል” ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቸርኒ፥ አዲሱ ጳጳሳዊ ኮሚሽን በየአገራቱ ከሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት ጋር ወደ ውይይት እንዴት መግባት እንደሚችል እና አብሮአቸው በመጓዝ ዛሬ የሰው ሠራሽ አስተውሎት የሚያነሳቸውን ተግዳሮቶች በመፍታት እና ግንዛቤን በማስጨበት እንዴት መደገፍ ይችላል?” የሚሉት እንደሚገኙበት ተናግረዋል።

ዘመናዊ ተግዳሮቶችን ለመለየት የሚረዳ ሐዋርያዊ መልዕክት

“ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ካስተማሩኝ ታላላቅ ትምህርቶች አንዱ፥ እውነታን አትፍሩ የሚል ነው” ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቼርኒ፥ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ የታቀፉ በርካታ ምዕመናንን ጨምሮ ሁላችንም ከእውነታው መዳን ወይም አንዳንድ ጊዜ ከእውነታው መራቅ ምን ያህል ከባድ ፈተና መሆኑን ተረድተዋል?” ሲሉ ጠይቀው፥ የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ መልዕክት ከእውነታው ጋር መሳተፍን በትክክል ይጠይቃል” ሲሉ አስረድተዋል።

“የሰው ልጅ ታላቅነት” የሚለው የቅዱስነታቸው ሐዋርያዊ መልዕክት የቤተ ክርስቲያኒቱ ማኅበራዊ አስተምህሮ ታላላቅ መሠረቶችን እና መርሆዎችን በሚገባ በማረጋገጥ፥ ሰዓዊነታችንን አደጋ ላይ የሚጥሉ ወይም ለሰው ልጅ ዕድገት ከባድ እንቅፋቶች ከሚሆኑ እና ከሰው ሠራሽ አስተውሎት ጋር የተያያዙት ብቻ ሳይሆን፥ ሌሎች በርካታ ተግዳሮቶችን እንድንገነዘብ፣ እንድንረዳ፣ እንድንተረጉም፣ እንድንለይ እና በመጨረሻም እንድንጋፈጥ ያግዘናል” ሲሉ አስረድተዋል።

ሲኖዶሳዊነትን በገሃድ መኖር

ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቼርኒ በመቀጠልም፥ “‘የሰው ልጅ ታላቅነት’ የሚለው ሐዋርያዊ መልዕክት ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶሳዊነት በተጨባጭ እንድትኖር ይጋብዛል” ብለው፥ “ይህ ሲኖዶሳዊነት በቤተ ክርስቲያኒቱ ውስጣዊ ጥያቄዎች ላይ ብቻ ያተኮረ ሳይሆን ነገር ግን አልፎ አልፎ ከሚያስጨንቁን የዛሬዎቹ እና የነገዎቹ እውነታዎች ሳንርቅ በድፍረት እና በተስፋ ከሌሎች ጋር በኅብረት እንድንጓዝ የሚጠይቀን ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

“‘የሰው ልጅ ታላቅነት’ ሐዋርያዊ መልዕክት ሁሉንም የሚያካትት እና የሚቀበል በመሆኑ እጅግ ጥልቅ ነው” ያሉት ብጹዕ ካርዲናል ሚካኤል ቼርኒ፥ “ማንም ሰው የራሱን ድርሻ ለመወጣት ደካማ እንዳልሆነ ሁሉ ዓለምን የሚያጋጥሙ ተግዳሮቶችን መሸከም የሚችለው ከሌሎች ጋር በመተባበር ነው” ብለዋል (ቁ. 13)።

በስዊዘርላንድ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ሞዴል ላይ ያሰላሰለው የተቀናጀ የሰው ልጅ ልማት ማስተባበሪያ ጳጳሳዊ ጽሕፈት ቤቱ፥ የስዊዘርላንድ ብጹዓን ጳጳሳት በሌሎች በርካታ አገሮች ውስጥም መሠረታዊ በሆኑ ጥያቄዎች ውስጥ ዜጎችን የሚያካትት ቀጥተኛ የዲሞክራሲ ሥርዓትን የመጠቀም ጸጋ እንዳላቸው ገልጸው፥ አሁን ባለው ሁኔታ አኳያ ቤተ ክርስቲያን ለአገራችሁ እና ለተለያዩ ተቋሞቿ መልካም አስተዳደር ልዩ አስተዋጽኦ እንድታደርግ ተጠርታለች” ሲል አስገንዝበዋል።

ለትክክለኛ የኅሊና ምርመራ የቀረበ ግብዣ

በሰው ሠራሽ አስተውሎት ዘመን የሰው ልጅ ጥበቃ የሚለውን የሐዋርያዊ መልዕክቱ ንዑስ ርዕሥ ያብራሩት ብጹዕ ካርዲናል ቼርኒ በተጨማሪም፥ “አንድ ሰው እነዚህን ባሕላዊ ቅርጾች ናቸው ቢልም፥ ለወንጌል አገልግሎት፣ ለሐዋርያዊ ድጋፍ፣ ለእርቅ እና በቤተ ክርስቲያኗ ሕይወት በተጨባጭ ለመሳተ እንኳን ጥልቅ ፍላጎቶች መኖራቸውን እንገነዘባለን” ሲሉ ተናግረዋል።

የቅዱስነውታቸው አዲሱ ሐዋርያዊ መልዕክት፥ ብጹዓን ጳጳሳት፣ ካኅናት እና ሐዋርያዊ ሠራተኞችም ጭምር እውነተኛ የኅሊና ምርመራ እንድናደርግ ይጋብዘናል” ሲል ተናግረው፥ “ጥያቄዎቹ ለወንጌል አገልግሎት አስፈላጊ በመሆናቸው፥ ለቅርንጫፎቻችን፣ ለአሠራራችን እና እንደ ቤተ ክርስቲያን ከሌሎች ዓለማዊ እውነታዎች ጎን ለጎን በታሪክ መካከል የምንጓዝባቸው መንገዶች በመሆናቸው በራሳችንም ተግባራዊ መሆን አለባቸው” ሲሉ መልዕክታቸውን ደምድመዋል።

 

 

 

02 Jun 2026, 16:24