የዓለም የተቀናጀ ሕክምና ኮንግረስ የተካሄደበት የስብሰባ ማዕከል - ሮም የዓለም የተቀናጀ ሕክምና ኮንግረስ የተካሄደበት የስብሰባ ማዕከል - ሮም 

የተቀናጀ የህክምና አሰጣጥ ሥርዓት የአኗኗር ጥራትን ያሻሽላል ተባለ

በሮም እየተካሄደ ባለው 2ኛው የዓለም የተቀናጀ ሕክምና እና ጤና ስብሰባ (ኮንግረስ) ዋና ዋና የውይይት ነጥቦች ሆነው እየተመከሩበት የሚገኙት ከፍተኛ የሕክምና ውጤቶች ፣ ታሪካዊ ምርምር እና ለጤና የተቀናጀ አቀራረብ የሚሉት ናቸው።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ዋና ዋና የሕክምና ምርምሮች እና የተገኙት የስኬት ድሎች እንዲሁም የክፍለዘመኑ ያልተለመዱ ልማዶች ተሞክሮ የሚሉ ርዕሶችም እስከ መስከረም 12 2016 ዓ.ም. ድረስ በሮም አንጀሊኩም የስብሰባ ማዕከል ውስጥ በሚካሄደው 2ኛው የዓለም የተቀናጀ ህክምና እና ጤና ኮንግረስ ላይ አብረው የሚነሱ ጭብጦች ናቸው።
ኦንኮሎጂ ወይም የዕጢ ህክምና በኮንግረሱ ላይ ትኩረት ተሰጥቷቸው ከሚነሱት ስምንት ዋና ዋና ጭብጦች አንዱ ነው። እንደ ሁለቱ የህክምና ዘዴዎች ማለትም ባህላዊ የህክምና ዘዴ (Allophatic) እና አዕምሮዋዊ እና ማህበራዊ የህክምና ዘዴ (Holistic) ባለሙያዎች ገለጻ ከሆነ ፥ የካንሰር ታማሚዎችን ለመፈወስ እና ጤናቸውን ለመመለስ የተቀናጀ የህክምና አቀራረብ እንደሚያስፈልግ እንዲሁም በባህላዊ እና በልማዳዊ የህክምና ዘዴዎች ማለትም የአኩፓንቸር፣ የአመጋገብ እና ኬሞቴራፒ ህክምናዎች የሚጫወቱት ሚና በተለይ ለካንሰር ህክምና ውጤታማ ናቸው ተብሏል።
በዚህም ዐውድ በስብሰባው ላይ ጠቃሚ ሳይንሳዊ ጥናቶች የቀረቡ ሲሆን ፥ ከነዚህም ዉስጥ በ ‘የተቀናጁ ኦንኮሎጂካል ሕክምናዎች ምርምር ተቋም’ (ARTOI) ሀኪሞች እና በልዩ ባለሙያዎች በካንሰር በሚሠቃዩ 60 ታካሚዎች ላይ ያደረጉትን የምርምር ውጤትን ያጠቃልላል። የተፈጥሮ እና የእጽዋት ምርቶችን እና ሌሎች የተቀናጁ ዘዴዎችን እንዲሁም ባህላዊ የራዲዮቴራፒ ሕክምናን በማስተዳደር ረገድ ያለውን አወንታዊ ተፅእኖ በማያሻማ ሁኔታ ይገልጻሉ። የዚህም ህክምና የመጨረሻው ዓላማ የታካሚውን ሕልውና ማራዘም እና የአኗኗር ዘይቤውን ማሻሻል እንደሆነ ተገልጿል።
ጥናቶች እንደሚያሳዩት እንደ ተፈጥሯዊ የሕክምና አማራጮች የሕክምና ዘዴዎቹ እነ ሃይፐርሰርሚያ ፣ ካናቢስ ፣ ለጡት ካንሰር በሽተኞች የሚደረጉ የአኩፓንቸር ህክምና ፣ ኖርዲክ ዎኪንግ ፣ የጎንዮሽ ጉዳቶችን ለመቀነስ ተብለው የሚደረጉ የአዕምሮ እና የሰውነት ህክምና ፣ ከባድ መድሃኒቶችን በመስጠት የሚደርግ ህክምና (homoeopathy) ፣ የእፅዋት ሕክምና ፣ የቻይናውያን ባህላዊ ሕክምና ፣ ምክር እና ቅድመ ጥንቃቄን ያካትታል።

በሕክምና እና ባልተለመዱ ልምዶች መካከል ያለውን ታሪካዊ ልዩነት ማሸነፍ

በሉካ ሆስፒታል የተመላላሽ ታካሚ ክሊኒክ ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር ኤሊዮ ሮሲ በህክምና እና ባልተለመዱ የህክምና ተግባራት መካከል የነበረው ታሪካዊ ክፍተት ተቀርፎ እንደሆን ተጠይቀው እንደተናገሩት ‘አብሮ መኖር ቀላል የሆኑባቸው አከባቢዎች እንዳሉ ሁሉ በአንዳንድ ቦታዎች ደግሞ ከባድ ይሆናሉ ፥ ምክንያቱም በህክምናው ባለሙያዎች መካከል ትብብር ስለሌለ ነው’ ብለዋል። ከዚህም በላይ ችግር በቀላሉ ወደ ተቃውሞ ሊለወጥ እንደሚችል ገልፀዋል። እንደ እድል ሆኖ ግን እስካሁን ድረስ ከታካሚዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው አብዛኛዎቹ በተለይም የሕፃናት ሐኪሞች እና አጠቃላይ ሐኪሞች ለታካሚው ጤና አጠቃላይ አቀራረብን እንደሚደግፉ አክለዋል ።

የዓለም ጤና ድርጅት መገኘት

‘ስለዚህ የዓለም ጤና ድርጅት በሮም ከተማ በሚደረገው ኮንግረስ ላይ ጣልቃ መግባቱ እና መገኘቱ አስፈላጊ ነው’ ብለዋል ዶክተር ሮስሲ።
የዓለም ጤና ድርጅት "በተለይ ለአንዳንድ ህክምናዎች ዘላቂነት ያለው የገንዘብ ምንጭ በሌሉባቸው እንደ ደቡቡ ክፍለ ዓለማት ባሉ አከባቢዎች ያልተለመዱ የህክምና ዘዴዎች እንዲተገበሩ የዓለም ጤና ድርጅት ሁልጊዜ ፍላጎት እንዳለው ተናግረዋል። ባለፈው ነሀሴ ወር 2015 ዓ.ም. የዓለም ጤና ድርጅት የባህል ህክምና ዙሪያ “ጤና እና ደህንነት ለሁሉም” በሚል መሪ ቃል በህንድ ሃገር ጋንዲናጋር ፡ ጉጃራት ከተማ በተካሄደው ስብሰባ ባወጣው የመጨረሻ መግለጫ ላይ “ባህላዊ ፣ ተጨማሪ ወይም ማሟያ እንዲሁም የተዋሃደ” ተብለው የሚታወቁትን የህክምና ዓይነቶች ለማስተዋወቅ ግልፅ የሆነ የአሰራር ቀመርን አካቷል። የእነዚህ የህክምና ስኬቶች ዛሬ ላይ ከጥቂት ዓመታት በፊት ከነበርው መቶ እጥፍ እንደሚበልጥም ተመላክቷል።
 

22 September 2023, 16:18