በካን ዮኒስ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን በጎርፍ ሳቢያ ከባድ ሁኔታዎች አጋጥሟቸዋል በካን ዮኒስ የተፈናቀሉ ፍልስጤማውያን በጎርፍ ሳቢያ ከባድ ሁኔታዎች አጋጥሟቸዋል  (ANSA)

በጋዛ ያለው ከባድ የአየር ሁኔታ ለቤት አልባ ሰዎች ከባድ መከራን ማስከተሉ ተነገረ

በጋዛ ከባድ ዝናብ እየጣለ መሆኑን የእርዳታ ሰራተኞች የገለጹ ሲሆን፥ ይህም በስራቸው ላይ ተጽዕኖ መፍጠሩን ተናግረዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ከሁለት ዓመታት የእስራኤል የቦምብ ጥቃት በኋላ በጋዛ የተከሰተው የጎርፍ አደጋ በሺዎች የሚቆጠሩ የተፈናቃይ ፍልስጤማዊያን ድንኳኖችን ጠራርጎ በመውሰዱ በርካታ መጠለያዎችን ከጥቅም ውጪ ሆነዋል።

ከዚህም በተጨማሪ አንድ የመኖሪያ ሕንፃ በከፊል በመደርመሱ የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉ ተነግሯል።

ይሄንን ተከትሎ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም አስተማማኝ እና የዘላቂ መጠለያዎች አስፈላጊነትን አጉልቶ ያሳየ ሲሆን፥ ኤጀንሲው ከደቡብ ኮሪያ በተገኘ ድጋፍ ለተፈናቀሉ ነዋሪዎች የሚያገለግሉ ከ800 በላይ ያረጁ ድንኳኖችን በአዲስ መተካቱ ቢታወቅም፥ ነገር ግን አሁንም ጥረቱ ከሚፈለገው በታች እንደሆነ ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ተፈናቃዮች ያረፉባቸው ቦታዎችን የሚያስተዳድሩ ቡድኖች የውሃ መውረጃዎችን በማጽዳት የጎርፉን ውሃ በማማስወገድ ላይ እንደሚገኙ ተነግሯል ናቸው።

የተባበሩት መንግስታት ድንኳኖችን፣ ብርድ ልብሶችን እና ሌሎች ቁሳቁሶችን በማከፋፈል ላይ የሚገኝ ሲሆም፥ የክረምት ፕሮግራሞችም በመካሄድ ላይ ቢሆኑም በአሁኑ ወቅት ሁኔታዎች በጣም አሳሳቢ ናቸው ተብሏል።

የጤና ሰራተኞች በዚህ ሳምንት የመጀመሪያውን ከብርድ በሽታ ጋር የተያያዘ በካን ዮኒስ የሁለት ሳምንት ጨቅላ ህፃን ሞት አረጋግጠዋል።

የምግብ አቅርቦቶች በእርዳታ እና በንግድ ወደ ሀገር ውስጥ በሚገቡ ምርቶች የተሻሻሉ ቢሆንም፣ የፕሮቲን እጥረት አሁንም መኖሩ ተገልጿል።

የእርዳታ ቁሳቁሶችን የያዙ ከባድ ተሽከርካሪዎች የሎጂስቲክስ እና የደህንነት እንቅፋት እየገጠማቸው በመሆኑ የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቶች የተገደቡ ሲሆን፥ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ባለስልጣናት ሁሉም ወገኖች የተሟላ እና ያልተደናቀፈ እርዳታ እንዲገቡ መፍቀድ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

19 Dec 2025, 13:47