ፈልግ

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በማልታ ለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተዘጋጀ መፈክር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በማልታ ለሚያደርጉት ሐዋርያዊ ጉብኝት የተዘጋጀ መፈክር 

‘ብሩህ ምድር’ የሆነቺው ማልታ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስን መምጣት በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች

የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ 36ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት ሊጀመር ጥቂት ሰአታት ብቻ ቀርተውታል፣ ቅዳሜ እና እሁድ የሚካሄደው የሁለት ቀናት ጉዞ ነገ መጋቢት 24/2014 ዓ.ም ይጀመራል። ለሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ የተደረገለትን አቀባበል ፈለግ በመከተል “በደስታ መቀበል እና እምነት” የተሰኘው ሐረግ የዚህ ሐዋርያዊ ጉዞ ጭብጥ ሐሳብ ነው፣ በተመሳሳይ ጊዜ ይህ ሐዋርያዊ ጉብኝት የዩክሬን ጦርነት አስከፊነት ማንጸባረቁ እንደማይቀር ይገመታል።

የዚህ ዜና አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

በአውሮፓ ደቡባዊ ጫፍ ላይ የምትገኘው ይቺ ሀገር በታሪኳ ለሶስተኛ ጊዜ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳትን ለመቀበል በዝግጅት ላይ ነች። በታሪክ ውስጥ እ.አ.አ በ1990 እና 2001ዓ.ም ወደ ማልታ ሪፐብሊክ ለመጀማሪያ ጊዜ ሐዋርያዊ ጉብኝት ለማደረግ ወደ እዚያው ያቀኑት በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እንደ ነበሩ የሚታወስ ሲሆን ከእዚያ በኋላ ደግሞ እ.አ.አ በ2010 ዓ.ም ላይ በወቅቱ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት የነበሩት ቤኔዲክት 16ኛ ካደረጉት ጉብኝት በመለጠቅ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በዚህ ሳምንት ማብቂያ ላይ በመጋቢት 24-25/2014 ዓ.ም ማለትም በመጪዎቹ ቀናት ቅዳሜ እና እሁድ በማልታ ደሴት የሚያደርጉትን ሐዋርያዊ ጉብኝት እንደ ሚጀምሩ ይታወቃል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው ጉዞ ነው። ከዚህ ቀደም እ.አ.አ ለግንቦት 2020 ዓ.ም ታቅዶ የነበረው ጉዞ በወረርሽኙ ምክንያት ለሌላ ጊዜ መተላለፉ ይታወሳል። አሁን በዩክሬን ጦርነት እና የቦምብ ፍንዳታውን የሚሸሹ ስደተኞች የማያቋርጥ ፍሰት መታየቱ የማይቀር ነው።

በወንጌል አዋጅ ምንጭ

ዛሬ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁኔታ ማልታ - “ብሩህ ምድር”፣ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ባለፈው ረቡዕ በጋቢት 21/2014 ዓ.ም በቫቲካን በሚገኘው በጳውሎስ 6ኛ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ባደረጉት የጠቅላላ የትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ላይ እንደገለፁት - “ብዙ መጠጊያ የሚፈልጉ ወንድሞችን እና እህቶችን ለመቀበል ቆርጣለች። የእንግዳ ተቀባይነት መሪ ቃልም የጉዞው አርማ ተምሳሌት ሲሆን ወደ ሮም ሲሄዱ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት በደሴቲቱ ላይ ተሰባብራ የሰጠመችው ጀልባ ላይ ወደ ሌሎች ብቅ ሲሉ እጆቻቸውን ሲዘረጉ የሚያሳይ ነው” ማለታቸው ይታወሳል። “ወደ ወንጌል መስበክ ምንጮች የመሄድ እድል” እና ለጳጳሱ “በመጀመሪያ በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታትን ያስቆጠረ ሕያው ታሪክ ያለው የክርስቲያን ማህበረሰብን ለመተዋወቅ” እንደሚሄዱ ቅዱስነታቸው አክለው ገልጸዋል። የማልታ ደሴት ሕዝብ 408,000 የተጠመቁ የካቶሊክ ምዕመናን የሚገኙባት አገር ስትሆን ከጠቅላላው 478,000 ህዝብ ብዛቷ ውስጥ 85% የካቶሊክ እመነት ተከታይ ነው፣  ማልታ ጎዞ እና ሌሎች ትናንሽ ደሴቶች ሰንሰለት ውስጥ የምትገኝ ደሴት ናት ።

መጋቢት 24-25/2014 ዓ.ም

ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ ቅዳሜ ጠዋት በማልታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 10 ሰዓት ላይ እንደ ሚደርሱ የሚጠበቅ ሲሆን ከአቀባበል ሥነ ሥርዓቱ በኋላ ወደ በቫሌታ ወደሚገኘው ግራንድ ማስተር ቤተ መንግሥት ያቀናሉ። ሕንጻው የተገነባው እ.አ.አ በ1571 ዓ.ም ሲሆን በወቅቱ በመካከለኛው ዘመን ከፍ ያለ ጀብዱ ለፈጸመ የሚሰጥ የወታደር ክብር ማዕረግ የነበራቸው የመስቀል ተዋጊዎች በታላቁ ሊቅ እና መምህር በቅዱስ ዮሐንስ መቀመጫ በሆነው ቦታ ላይ የተገነባ ሕንጻ ሲሆን ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ የማልታ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ጆርጅ ዊልያም ቬላን እና ከዚያም ጠቅላይ ሚኒስትር ሮበርት አቤላን ጋር እንደ ሚገናኙ ይጠበቃል። የሀገሪቱን መንግስት ለመምራት በድጋሚ ተመርጧል። በታላቁ ምክር ቤት  አዳራሽ ውስጥ ከማልታ ባለስልጣናት እና የዲፕሎማቲክ አባላት ጋር እንደ ሚገናኙ የሚጠበቅ ሲሆን በእዚያም ስፍራ ቅዱስነታቸው የቀኑን የመጀመሪያ ክፍል የሆነውን ንግግር እንደ ሚያደርጉ ከወጣው የጉዞ መርዓ ግብር ለመረዳት ተችሏል። ከእዚያም በኋላ "እህት" ደሴት በመባል ወደ ምትታወቀው ጎዞ ደሴት በመጓዝ በእዚያ የሚገኘውን የማርያም ቤተመቅደስ ይጎበኛሉ፣ በመቅደሱ ፊት ለፊት ባለው ትልቅ አደባባይ፣ የማልታ መንፈሳዊ ነጋዲያን የአምልኮ ስፍራ፣ ሊቃነ ጳጳሳት፣የጳጳሳት ሲኖዶስ ዋና ጸሃፊ የማልታ ካርዲናል ማሪዮ ግሬች፣ከምእመናን ጋር የጸሎት ስነ ስረዓት ይመራሉ።

የቅዱስ ጳውሎስ የተቦረቦረ ዋሻ (ፍርኩታ) እና መስዋዕተ ቅዳሴ በፍሎሪያና

እሁድ መጋቢት 25/2014 ዓ.ም ጠዋት ላይ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ  ከኢየሱሳዊያን ማኅበር አባላት ጋር በግል ይገናኛሉ፣ ከዚያም በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከቀኑ 8፡30 ላይ ራባት ወደሚገኘው የቅዱስ ጳውሎስ የተቦረቦረ ዋሻ ውስጥ ወደ ሚገኘው ቤተመቅደስ ያቀናሉ። እ.አ.አ በ60 ዓ.ም ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ ታስሮ ወደ ሮም በሚመጣበት ወቅት የነበረበት መርከብ በገጠማት አደጋ ምክንያት ከተሰበረች እና ከሰመጠች በኋላ “የአሕዛብ ሐዋርያ” በመባል የሚጠራው ሐዋርያው ጳውሎስ በእዚያች ደሴት በማረፍ ስብከተ ወንጌልን የጀመርበት እና ለደሴቱ ክርስትና ወሳኝ ክስተት በነበረበት ቦታ ተገኝተው ጸሎት ያደርጋሉ። እ.ኤ.አ. በ1990 በቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊ እና በ2010 በነዲክቶስ 16ኛ የተጎበኘው ይህ የቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ የተቦረቦረ ዋሻ ውስጥ የሚገኘው ቤተመቅደስ 1950ኛውን የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ተጎብኝቶ እንደ ነበረ ይታወሳል። ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቸስኮስ በስፍራው ተገኝተው ሻማ ካበሩ በኋላ  ለቅዱስ ሐዋርያው ጳውሎስ ጸሎት በማቅረብ በቦታው የሚገኙትን 14 የሀይማኖት አባቶች እንዲሁም በአካባቢው በሚገኘው የካሪታስ ድርጅት የሚታገዙትን በርካታ በሽተኞች ጋር ተገንኝተው ሰላምታ እንደ ሚለዋወጡ ይጠበቃል። ከማልታ ትላልቅ ክፍት ቦታዎች አንዱ የሆነው ፒያሳሌ ዴ ግራናይ በፍሎሪያና - ከቫሌትታ ግንብ በላይ ባለችው ከተማ  በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከረፋዱ 10.15 ላይ መስዋዕተ ቅዳሴ እንደ ሚያደርጉ ይጠበቃል።

 “ያልተለመደ ደግነት አሳይተውናል” በሚል መሪ ቃል የሚደርገው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳቱ ይህ 36ኛው ሐዋርያዊ ጉብኝት በሮም የሰዓት አቆጣጠር አመሻሹ ላይ 6፡15 አካባቢ ከሁለት መቶ በላይ ስደተኞች የሚገኙበትን የዮሐንስ 23ኛ የሰላም ማዕከል በመጎብኘት ይጠናቀቃል። ከዚያም በሮም የሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 7፡40 ላይ ወደ ሮም እንደ ሚመለሱ ከወጣው የጉዞ መረዓ ግብር ለመረዳት ተችሏል።

01 Apr 2022, 16:00