ፈልግ

ሕጋዊ ደንብ

ሕጋዊ ማሳሰቢያዎች

የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደር ጽሕፈት ቤት ሲሆን ይህም የተቋቋመው እ.አ.አ. በሰኔ 27/ 2015 ዓ.ም ላይ በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቼስኮስ “የአሁኑ የግንኙነት ሁኔታ” (L'attuale contesto comunicativo") በሚል የግል ተነሳሽነት "አዲስ በቅድስት መንበር ሥር የሚተዳደር ጳጳሳዊ የመገናኛ ብዙዐን ጽሕፈት ቤት እንዲመሰረት ባወጁት አዋጅ መሰረት የተቋቋመ ነው። የእዚህ ጽሕፈት ቤት የበላይ አስተዳዳሪ ቅድስት መንበር ናት።

የእዚህ ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) ዋና ተግባር የሚሆነው በቤተ ክርስቲያኑዋ የወንጌል ተልዕኮ አገልግሎት እና በአዲሱ የቅድስት መንበር ሐዋርያዊ የመገናኛ ዘዴ መዋቅር ውስጥ የሚገኙትን ጠቃሚ መረጃዎች  ለማጎልበት የሚረዳ አዲስ፣ አሳታፊ፣ የተቀናጀ እና የመልቲሚዲያ መገናኛ ሥርዓት ማቋቋም ነው።

 

የአጠቃቀም መመሪያዎች እና ደንቦች

በዚህ ድረ ገጽ ውስጥ (ከዚህ በኋላ "ድረ ገጽ" እየተባለ ይጠራል) እንዲሁም በእነዚህ ድረ ገጽ ውስጥ የሚሰጡ አገልግሎቶች መጠቀም እና ማመሳከር፣ እንዲሁም የቀጥታ ስርጭቶችን መጠቀምን በተመለከተ ተጠቃሚው (ከዚህ በኋላ “ተጠቃሚ” በመባል ይጠራል) “የአጠቃቀም መመሪያዎችን እና ደንቦችን” መከተል ይኖርበታል።

ኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) በድረ-ገፁ ላይ የተለጠፉ ህትመቶችን ለተጠቃሚው በቅድሚያ ሳያሳውቅ በማንኛውም ጊዜ፣ በአጠቃቀም ሁኔታ ላይ ለውጦችን እና / ወይም በድኽረ ገጹ ላይ የተደርጉ ማሻሻያዎች እና ለውጦችን የአጠቃቀም መመሪያዎችን እና ደንቦችን” በመከተል እነዚህን ለውጦች እና ማሻሻያዎችን በራሱ ድረ ገጽ አማካይነት  ለተጠቃሚዎቹ በማሳወቅ በማንኛው ጊዜ ለውጥ የማድረግ መብት አለው።

 

የአእምሯዊ ንብረት መብቶች

የድረ ገጹ ይዘቶች ለምሳሌ እንደ ምስል፣ ድምፆች፣ ቪዲዮዎች፣ ሙዚቃ፣ ጽሑፎች፣ ፎቶግራፎች፣ ስዕሎች፣ ፋይሎች፣ የንግድ ምልክቶች፣ አርማዎች፣ ዜናዎች፣ ሶፍትዌሮች ማንኛውንም ይዘት እና / ወይም መረጃ፣ በማንኛውም ዓይነት ቅርፀት (ከ 'ይዘት' በኋላ)፣ የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) ንብረቶች በመሆናቸው የተነሳ በማንኛውም ሁኔታ እንደ በፊቱ፣ በቅጂ መብት የተጠበቁ በመሆናቸው የተነሳ በማንኛውም ሁኔታ በሙሉ ወይም በከፊል ሊሆኑ ይችላል፣ በማንኛውም ዓይነት መልኩ ወይም በማንኛውም መንገድ ከኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) አስቀድሞ በጽሑፍ የተሰጠ ፍቃድ ሳያገኝ ማሻሻያ ማድረግ፣ መቅዳት፣ ማከፋፈል፣ ማሰራጨት፣ ማተም፣ ማስተላለፍ፣ ማባዛት ወይም በሌላ መልኩ እንዲገኝ ማድረግ በፍጹም አይቻልም፣ ይህም ንዑስ ፍቃድ ሳይኖረው ሽያጭን ማከናወን፣ የሽያጭ ሥራዎችን በነጻ ማከናወን ወይም ብዝበዛን በማንኛውም መንገድ ያለፈቃድ መፈጸምን ያካትታል።

በድረ ገጹ ላይ የሚታተሙ ምስሎችን፣ ሰነዶችን፣ ምርቶችን፣ ዓርማዎችን እና የንግድ ምልክቶችን በኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) በኩል በቅጂ መብት ስልጣን መሰረት በግልጽ ለመጠቀም ያሳወቁ ሶስተኛ ወገኖች ሳይቀሩ በእዚህ በቅጅ መብት የተጠበቁ ናቸው።

የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት  SPC አርማ እና / ወይም መፈክር በድጋሚ ማዋቀር በጥብቅ  የተከለከለ ነው።

“የቅድስት መንበር የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት” የሚለው ስም የሌላ ጣብያ የበይነመረብ (ኢሜል) አድራሻ ወይም የሌላ ተመሳሳይ አይነት አድራሻዎች አካል አድርጎ መጠቀም አይቻልም።

 

የኃላፊነት ገደብ

የዚህ መረጃ መስጫ ድረ ገጽ ማመሳከሪያ ይዘቶች በቅን ልቦና የተሰጡ ናቸውና “የቅድስት መንበር የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት” (SPC) እንደዚህ ያለውን ይዘት እርግጠኛ፣ ትክክለኛ እና የተሟላ መሆኑን ይከታተላል። ይሁን እንጂ ስህተቶች፣ ግድፈቶች እና እርግጠኛ ያልሆኑ ጉድለቶች ሊኖሩ የሚችሉ ሲሆን ስለዚህ በአግባቡ ያለውን መረጃ በጊዜ ሂደት ለማረም እና በማንኛውም ሁኔታ እነዚህን ሁኔታዎች ለማስተካከል የሚረዱ እርምጃዎች በኃላፊነት መንፈስ ያከናውናል።

የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት” (SPC) ሶስተኛ ወገኖች ከዋናው ይዘቶች ጋር በተያያዘ መልኩ  ስለሚጠቀሙበት አጠቃቀም ምንም ዓይነት ኃላፊነት አይወስድም።

ድረ ገጹን በመጠቀም ሂደት ውስጥ ለሚፈጥሩ ለማንኛውም ዓይነት  ቫይረሶች ወይም ደግሞ መረጃን በማሰስ ሂደት ውስጥ ሊፈጥሩ ለሚችሉ የኮፒውተር ብክለቶች የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት” (SPC) ኃላፊነት በፍጹም አይወስድም።

(Link) ወይም “አገናኝ” በሚለው የአጠቃቀም ዘዴ አማካይነት ከሶስተኛ ወገን ድረ ገጽ ጋር በተያያዘ መልኩ በእዚሁ በሶስተኛ ወገን ድረ ገጽ ተጠቃሚዎች አማካይነት ለሚከሰቱ ስህተቶች የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) ኃላፊነት አይወስድም። በ “Links” አማካይነት የተገናኙ መስመሮች የተገናኙትን ዋና ድረ ገጽ ጣቢያ ማረጋገጫ ባለማግኘታቸው የተነሳ በእዚህም መስረት ለሚፈጥረው የጥራት ጉድለት፣ የይዘት ለውጥ እና ስዕላዊ መግለጫዎች ጋር የተያያዘ ስህተት የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) ኃላፊነት አይወስድም። ከላይ የተጠቀሱትን ድር ገጾች ለመመልከት የወሰኑ ተጠቃሚዎች ለሚከሰተው ማንኛውም አደጋ ራሳቸውን ተጠያቂ ማድረግ ይኖርባቸዋል፣ በእዚህም ምክንያት በድረ ገጹ ውስጥ የሚገኙትን ቫይረሶች ወይም የመነጩን የብክለት ስጋቶች ሙሉ በሙሉ ኃላፊነት መውሰድ ይኖርባቸዋል።

በማንኛውም ሁኔታ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ወይም/ እና ከመረጃ ወይም ከማዕቀፉ አጠቃቀም እና ወይም በመረጃዎች ወይም በምስል በማንኛውም የመገናኛ መንገድ ጋር ተያይዞ በሶስተኛ ወገን አማካይነት ለደረሰው ጉዳት እና/ወይም ኪሳራ የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) ተጠያቂ አይሆንም።

 

የግል መረጃዎች ጥበቃ

የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) በድረ-ገፁ ላይ የሚቀርቡት አገልግሎቶች ደንበኞች ከተጠቀሙ በኃላ (አገልግሎቱን ተከትሎ) በድረ ገጹ ላይ የሚታየውን  የገለሰቦችን የግል መረጃ በከፍተኛ ደረጃ የሚጠበቁ ምስጢሮች እና በ "ግልጋሎት ድረ ገጹን የተጠቃሚዎችን የግል መረጃዎች በጥንቃቄ የሚቀመጡ መሆናቸውን ያስታውቃል። የሶስተኛ ወገን የድረ ገፁ አገልግሎት አቅራቢ በሂደቱ የኮሚኒኬሽን ጽሕፈት ቤት (SPC) የተረጋገጠ የመረጃ አያያዝ ዋስትና ያለው ከሆነ የተጠቃሚውን የግል መረጃ ይገነዘባል ይጠብቃልም።

ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን አገልግሎቶች በመጠቀም ተጠቃሚው በራሱ የግል መረጃዎ ሂደት ውስጥ በራሱ ፈቃድ መስማማቱን ያሳውቃል፣ ነገር ግን እስካልፈቀደ ድረስ በድረ-ገጹ ላይ ያሉትን አገልግሎቶች መጠቀም የለበትም።

 

ተፈፃሚነት ያለው ህግ እና ፍትሀዊ ፍ / ቤት

አሁን ያሉትን «የአጠቃቀም ደንቦች እና የአጠቃቀም ሁኔታዎች» የሚቆጣጠረው በቫቲካን ከተማ ውስጥ በተተገበሩት ህጎች ላይ በተመሰረተ መልኩ ነው፣ ከትርጓሜ ስህተት ለሚነሳ ማንኛውም ዓይነት አለመግባባት እና ክርክር የቫቲካን ከተማ ግዛት ፍርድ ቤት ተመሳሳይ የፍርድ ስልጣን ይኖረዋል።