ፈልግ

ዘለዓለማዊ ደኀንነታችን የሚረጋገጠው በመስቀሉ ነው! ዘለዓለማዊ ደኀንነታችን የሚረጋገጠው በመስቀሉ ነው!  (ANSA)

ዘለዓለማዊ ደኀንነታችን

አንድ አዋቂ ሰው (ፈላስፋ) በአንዲት ጀልባ ተቀምጦ ከባህር ዳርቻ በሚገኙ አገሮችና መንደሮች ከአንዱ ከተማ ወደ ሌላ ከተማ ሲሻገር ለጀልባው ባለቤት «አንተ ወጣት ጀግና እነዚህ ከዋክብት እንዴት አድርገው በሚታየን ሰማይ እንደሚሽከረከሩ ታውቃህን;´ በማለት ጠየቀው፡፡ የጀልባውም ባለቤት «አንተ ወጣት ጀግና እነዚህ ከዋክብት እንዴት አድርገው በሚታየን ሰማይ እንደሚሽከረከሩ ታውቃለህን;´ በማለት ጠየቀው፡፡ የጀልባውም ባለቤት «አላውቅም ጌታዬ´ ሲል መለሰለት፡፡ ከዚያም አዋቂው ጥቂተ ጊዜ ቆይቶ «ማንበብ ትችላለህን;´ አለው፡፡ ሰውዬውም ትንሽ ሰልችቶት «ኧረ እኔ ማንበብ አልችልም´ ሲል መለሰ፡፡ አዋቂውም ያን ጊዜ «ታዲያ ምን ትችላለህ; አንተስ በዓለም የጠፋህ ሰው ነህ፤ ምንም አታውቅም አትረባም´ እያለ አዋረደው፡፡

በባሕር በጀልባ ላይ እየተንሰፈፈ ሲሄዱ ማዕበል ተነስቶ ጀልባዋን ሊገለብጣትና ሊያሰጥማት ቀረበ፡፡ ያ ጀግና ጐበዝም ጀልባዋን አጥብቆ መያዝ አቅቶት ከባድ የአእምሮ ጭንቀት ላይወደቀ፡፡ ጠፋን እያለ የሚያደርገውንና የሚለውን አጣ፡፡ አዋቂውም በበኩሉ እጅግ ፈርቶና ተጨንቆ በጣም ተንቀጠቀጠ፣ ባለጀልባውም ወጣት ወደ ባሕር ዘሎ ዋኝቶ ራሱን ማዳን ካልሆነ የሚያደርገው ሌላ ነገር የሌለ መሆኑን አይቶ ይህንን እንተረዳ ወደ አዋቂው መለሰ አለና «ጌታ ሆይ ዋና ያውቃሉን;´ ሲል ጠየቀው፤ እርሱም «አልችልም አላውቅም´ ሲል መለሰለት፡፡

ከዚህ ቀጥሎ ባለጀልባው ጀግናው ጐበዝ ወጣት «እንግዲህ እርስዎ ጠፍተዋል ማለት ነው´ እያለ መለሰለትና እርሱ ከጀልባው ዘሎ ዋኝቶ ሕይወቱን አዳነ፡፡ አዋቂው ግን ያ ሁሉ ዕውቀትና ፍልስፍና እያለው መዋኘት ባለመቻሉ ሕይወቱን አጠፋ፡፡ ጀልባዋ ባሕር ውስጥ ስትሰጥም አዋቂው ሰውዬ ከመላ ዕውቀቱ ጋር በባሕሩ ውኃ ሰምጦ ሞተ፡፡ ትዕቢተኛ አዋቂ ስንት ነገር ሲያውቅና ሰፊ ዕውቀት ሲኖረው ቀላል የሆነችውን ነገር ስላልቻለ ሕይወቱን ሊያድናት አልቻለም፡፡

ይህ ታሪክ ምንን ያሳስበናል; አንዳንዶች በዓለም ልባሞችና ብልሆች የሚባሉ ከሞታቸው በኋላ በወዲኛው ዓለም በጣም አስፈላጊ በሆነው ዕውቀት ነፍሳቸውን ማዳን እንደሚይችሉና እንደሚኰነኑ፣ ሌሎች ደግሞ በዓለም አስተሳሰብ ደንቆሮዎችና ያልተማሩ የሚባሉ ግን በየዋህ መንፈሳዊነታቸው ከሞታቸው በኋላ መነግሥተ ሰማያትን በመውረስ ነፍሳቸውን እንደሚያድኑ ያሳስበናል፡፡ ብዙዎች ደንቆሮዎች ከድንቁርና ጋር ወደ መንግሥተ ሰማያት እንደሚገቡና አንደ እነዚህ አዋቂዎች የሚባሉ ግን ከሁሉ ዕውቀታቸው ጋር ወደ ገሃነ እሳት ሲሄድ ምን ይባላል;

አንዳንዶች በዓለም ጉዳዮች አዋቂዎች ብልጦች ዕውቀትና ችሎታ በሚፈለግበት ተወዳዳሪ የማይገኝላቸው በመንፈስ ጉዳይ ሲሆን ሰነፎች ደንቆሮዎች ሆነው ይገኛሉ፡፡ አንዳንዶች ግን በዓለም ጉዳዮች ሰነፎችና ደንቆሮዎች ሲመስሉ እግዚአብሔርን በሚመለከቱ መንፈሳዊ ጉዳዮች እጅግ ትጉሆችና ብልሆች ሆነው ይገኛሉ፡፡ ይህ ደግሞ ከፍላጐታቸው ስለሆነ ነው፡፡ እነዚያ ፊተኞች በሙያና በብልህነት ረገድ በዓለም ከፍ ብለው ይታያሉና ዓለም ያደነቃቸዋል በእነርሱም ይቀናባቸዋል፡፡ እነዚያ ኋለኞች ግን በመንፈሳዊነታቸው እግዚአብሔር ይደሰትባቸዋል፡፡ በዓለም እነዚህን ይንቃል፤ እግዚአብሔር ደግሞ እነዚያን ይንቃል፡፡ እነዚያ በዓለም አዋቂዎች የሚባሉ የሥጋቸውን ምኞትና ሐሳብ ይፈጸማሉ፡፡ እነዚያ በዓለም አስተያየት ደንቆሮዎች ተብለው የተናቁ ስለ ነፍሳቸው ደኀንነት በጥብቅ ይቆረቆራሉ፡፡ እነዚያ በሁለቱ መንገዶች የሚጓዙት ሰዎች በየመንገዳቸው ሲሄዱ ሞት ሲደርስ ነገሩ ይቀየራል፡፡

ስለዚህ ጉዳይ ጥበበ ሰሎሞን የሚለንን እንመልከት «እነዚያ በዓለም ተከብረው የነበሩ ወደ ዘለዓለም ስቃይ ገሃነመ እሳት ሲጣሉ  እነዚያ ይንቋቸው የነበሩ ደንቆሮዎች ጻድቃን ግን ወደ ዘለዓለማዊ ደኀንነት ሲሄድ ካዩ በኃፍረትና በብስጭት ተሞልተው በሕይወታቸው ተጸጽተው እኛ ሞኞች ሕይወታችንን የማይረባ አድረገን ተመልክተነዋል፣ አሁን ግን እነሆ እነርሱ ጻድቃን የእግዚብሔር ልጆች ሆነዋል፣ እንግዲያውስ እኛ ተሳስተን በጥፋት መንገድ ቧርቀናል፣ እግዚአብሔርን ንቀናል፤ ምን ጠቀመን ትዕቢትና ሀብት ሁሉ እንደ ጥላ አልፈዋል´ እያለ ይጮኻሉ (ጥበ. ሰሎ. 5፣4     )፡፡ በደካነት ወደ ዓለም ስናዘነብል የዘለዓለምን ደኀንነት በመርሳት ሥጋችንን ለማስደሰት ነፍሳችንን እናሳዝናለን በምድር እንዲመቸን ብዙ ጥረት እናደርጋለን፡፡ በሰማይ እንዲመቸን ግን ተግተን አንሠራም፣ ጊዜያዊና ዓለማዊ ኑሮአችንን ለማመቻቸ ጠንቅረን አንሰራም  ለማዘጋጀት ግን ተግተን አንሠራም ቸል እንላለን፡፡ «ሰው ዓለምን በሙሉ ቢይዝ ነፍሱን ግነ ቢያጠፋ ምን ይጠቅመዋል;´ (ማቴ. 16፣26) እያለ ኢየሱስ በጥብቅ ያስጠነቅቀናል፡፡ ስንሞት እንዳይደርስብን በሕይወታችን ለዘለዓለማዊ ደኀንነታችን ባለን ኃይልና ችሎታ ያላሰለሰ ጥረት እናድርግ፡፡

13 June 2022, 12:58