ፈልግ

ቅዱሳት መጻሕፍት ቅዱሳት መጻሕፍት  (©khanchit - stock.adobe.com)

ቅዱሳት መጻሕፍት

ለነፍሳችን ከሁሉ የሚጠቅመን ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ ነው፡፡ ቅዱስ ዮሐንስ «የዚህን ቃል ትንቢት የሚያነብና የሚሰማ ብፁዕ ነው፣ የታደለ ነው” (ራእ. 1፣2፤ 2ኛ. ዮሐ. 5፣39) ይላል፡፡ ኢየሱስም አንድ ቀን ለአይሁዳውያን «እናንተ በቅዱሳት መጻሕፍት የዘለዓለምን ሕይወት እንድታገኙ ምዕራፎችን መርጣችሁ መርምሩ፤ በእርግጥ በእነርሱ ሕይወት የምታገኙ ስለሚመስላችሁ እነርሱን አጥብቃችሁ ትመረምራላችሁ፣ እነርሱ ስለ እኔ የሚመሰክሩ ናቸው” (ዮሐ. 5፣39) ይላቸው ነበር፤ እነርሱ ግን አልተረዱትም፡፡

የእዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ ቫቲካን

አይሁዳውያን በበኩላቸው በቅዱሳት መጻሕፍት ንባብ ብዙ ያስቡና ይቆረቆሩ ነበር፡፡ ኢየሱስ በምኩራባቸው እየተገኘ ቅዱሳት መጻሕፈት ያነብላቸውና ይተረጉምላቸው ነበር፡፡ የቀድሞ ክርስቲያኖች በቅዱሳት መጻሕፍት ንባብ ትጉሆች ነበሩ፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ለተማሪው ለጢሞቴዎስ «እኔ ወደ አንተ እስክመጣ ድረስ በንባብ ተጠመድ” (2ኛ. ጴጥ. 1) እያለ ይመክረው ነበር፡፡ ጻድቃን ሁሉ ከማናቸውም ነገር አብልጠው መንሳዊ ቅዱሳት መጻሕፍትን ይወዱ ነበር፤ እኛንም ቅዱሳት መጻሕፈትን እንድናነብ ይመክሩናል፡፡ በተለይ ደግሞ ቤተክርስቲያን ቅድሳት መጻሕፍት እንድናነብ ከእኛ የማይለዩ ሕይወታችን አድርገን እንድናስባቸው በጥብቅ ትማጠነናለች፡፡

ኢየሱስና ቤተክርስቲያን ቅዱሳት መጻሕፍን የሚያበረታቱት ከሆነ የቅዱሳት መጻሕፈት ትልቅነትና አስፈላጊነት ልንረዳ ይገባናል፡፡ የቅዱሳት መጻሕፈት የእግዚአብሔር ቃል እንጂ የሰው መጽሐፍት አይደሉም፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ «ትነቢት በሰው ፈቃድ ሚመጣ አይደለም፣ በመንፈስ ቅዱስ የተናገሩ ሁሉ በእግዚአብሔር ተልከው ነው´ (ኛ. ጴጥ. 1፣21) ይላል፡፡ እነዚያ ቅዱሳት መጻሕፍትን የጻፉ ሰዎች በእግዚአብሔር ፈቀድና ኃይል ተነሣሥተው ነው የጻፉዋቸዋል፡፡ እርሱ እያገዛቸውና በመንፈሱ እየመራቸው ነው፡፡ ቅዱሳት መጻሕፍት አንዲጻፉ የፈለገው ለሰው ለጆች የእግዚአብሔረን መንግሥት ማሳወቂያ መንፈሳዊ ትምህርትና መመሪያ እንዲሆኑ ብሎ ነው፡፡ የሰጠን መጻሕፍት እግዚአብሔር ፈጣሪያችንና አምላካችን መሆኑን እኛ ደግሞ ፍጥረቶችና አገልጋዮቹ እንደሆንን እርሱ ሰማያዊ አባታችን እኛም ደግሞ ልጆቹ እንደሆንን ያሳውቁናል ያስተምሩናል፡፡ ስለ እግዚአብሔር ምሕረትና ፍቅር ይናገሩናል፡፡ኢየሱስ ስለ ደኀንነታችን እንተሰዋ ይገልጡልናል፡፡ እግዚአብሔር እኛ በሰማይ ከእርሱ ጋር ዘወትር እንድንነግሥ እንደ ፈጠረን በምድርም ላይ ለነፍሳችንና ለሥጋችን እንደሚያስብልን የሚያፈልገንን ዕርዳታ እንደሚሰጠን ያስገነዝቡናል፡፡ ቅዱሳት መጻሕፈት እግዚአብሔር አምላከችንን እንድንወደው ስግደትና ምስጋና ለኃጢአታችን ካሣ እንድናቀርብለት ያስታውሱናል፡፡ ኃጢአትን እንድንጠላ ጽድቅን እንድንከተል የሚያበረታቱ የነፍሳችን ብርሃን ናቸው፡፡

የእግዚአብሔር ትዕዛዝ አስታውቀው እንደንፈጽም ያግዙናል፤ በእነርሱ ለነፍሳችን የሚያሰፈልገንን መንፈሳዊ ምግብና ኃይል እናገኛለን፡፡ «ቅዱሳት መጻሕፈት መንፈሳዊ የአእምሮ ብቃታችንን የምንመለከተባቸው መስተዋት ናቸው፣ በእነርሱም ውስጥ ውስጣዊ መልካተንን እናያለን፡፡ በመንፈስ ወደ ፊት ወይም ወደ ኋላ እንደምንሄድ እናውቃለን ይላል ቅዱስ ጐርጐርዮስ፡፡ የቅዱሳት መጻሕፍት ቁም ነገር ተረድተን አብልጠን እንድንወድ ያስፈልገናል፡፡ በትጋትና በንፈሳዊ ስሜትና በጥንቃቄ እንድናነባቸው ይገባናል፡፡ «እኔ እስከምመጣ ድረስ በንባብ ተጠመድ" የሚለውን የቅዱስ ጳውሎስን መንፈሳዊ ትምህርት አንርሳ፡፡

 

24 March 2023, 11:03