ፈልግ

ከአፍሪካ ወደ ብራዚል ሳን ፓውሎ የተደረገ የሮማን እና የጆን አድካሚ የስደት ጉዞ

የትውልድ አገራቸው ናይጄሪያን እና ከአይቮሪ ኮስትን ትተው የተሰደዱት ሁለት ሰዎች፥ ሮማን እና ጆን ሕይወታቸውን ለአደጋ አጋልጠዋል። መድረሻቸውን በማያውቋቸው መርከቦች ውስጥ ተደብቀው እስከ ብራዚል ሳን ፓውሎ የደረሱት እነዚህ ሰዎች፥ ለስደተኞች ዕርዳታን በሚያቀርብ የስካላብሪኒ ካቶሊካዊ ገዳማውያን ማኅበር አዲስ ተስፋ የሚያገኙበትን ዕርዳታ እያደረገላቸው ይገኛል።
ከሁለት ሳምንታት ጭንቀት እና አለመረጋጋት በኋላ ሮማን ኢቢሜኔ ከናይጄሪያ ርቆ በብራዚል አዲስ ሕይወት ጀምሯል።
ከሁለት ሳምንታት ጭንቀት እና አለመረጋጋት በኋላ ሮማን ኢቢሜኔ ከናይጄሪያ ርቆ በብራዚል አዲስ ሕይወት ጀምሯል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የ35 ዓመት ዕድሜ ሰው ሮማን ኤቢሜኔ ከናይጄሪያ ወጥቶ የስደት ጉዞን ከሌጎስ ከተማ የጀመረው ለሁለተኛ ጊዜ ነበር። ሮማን አገሩን ለቅቆ ለመሰደድ የወሰነበትን ምክንያት ሲገልጽ፥ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታዎች፣ በምግብ፣ በገንዘብ እና በጤና እንክብካቤ ጉድለት ምክንያታ መሆኑን ጠቁሞ፥ አክሎም አገሩን ለቅቆ የወጣበት ምክንያትም በየቀኑ በሚመለከተው የግድያ እና የዝርፊያ ወንጀም ምክንያት መሆኑን አስረድቷል።

በውድቅት ሌሊት አንድ ዓሣ አጥማጅ በጀልባው አሳፍሮት ወደ ትልቅ መርከብ ካደረሰው ከኋላ መርከቡ ላይ ለመውጣት መቻሉን የሚገልው ሮማን፥ በድብቅ ወደ መርከብ ከገቡት አራት ናይጄሪያውያን መካከል የመጀመሪያው ነበር። ከሁለት ሳምንታት በኋላ ጆን ኢኮም እንዲሁ በተመሳሳይ መንገድ በጭነት መርከብ ተሳፍሮ ከአይቦሪ ኮስት የተሰደደው ሚስቱን እና ሁለት ልጆቹን እዚያው ትቶአቸው ነበር። የ24 ዓመቱ ጋናዊ ወጣትም ለስደት የበቃው በሥራ ማጣት ምክንያት እንደነበር ገልጿል። ከአንድ ጓደኛው ጋር የስደት ጉዞን የጀመረው ጋናዊው ወጣት ጓደኛውን መስማት በማይችልበት ርቀት ከመርከቡ ተሽከርካሪ አጠገብ ሆኖ በጩኸት ድምጽ በመግባባት ከአቢጃን ወደብ ጉዞ ጀምረዋል።

የስልኩ ባትሪው ሳያልቅ ገና ጆን ኤኮው እና ጓደኛው ከጭነት መርከብ ሞተር አጠገብ ተደብቀው የተረፉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ምስል ቀጾ አስቀምጧል
የስልኩ ባትሪው ሳያልቅ ገና ጆን ኤኮው እና ጓደኛው ከጭነት መርከብ ሞተር አጠገብ ተደብቀው የተረፉበትን ሁኔታ የሚያሳይ ምስል ቀጾ አስቀምጧል

የውሃ ጥማት እና እርግጠኛ አለመሆን

ሮማን ብዙ የሚበላ እና የሚጠጣ ነገር ነበረው ነገር ግን ብዙም አልቆዩም። አራቱ ናይጄሪያውያን ለአሥር ቀናት ያህል የሚበቃ ስንቅ ማጠራቀም ችለዋል። አዲስ ሕይወት ለመጀመር ተስፋ ያደረጉባቸው ሁለት መዳረሻዎች ማለትም አውሮፓ ወይም አሜሪካ ለመድረስ በጀልባ ምን ያህል ጊዜ እንደሚወስድ ለመረዳት ሲሞክሩ ይህን ያህል ያለ ረጅም ጉዞ ይሆናል ብለው ፈጽሞ አስበው አያውቁም።

መርከቧ ጉዞዋን ከጀመረች አንድ ቀን አለፈ፤ ሁለተኛ እና ሦስተኛ ቀንም ተቆጠረ፤ መቆሚያ የሌለው ጉዞ ሆነ። መርከቡ ወዴት እያመራ እንደሆነ የሚያውቅ በመካከልቻው አልነበረም። “ይህ ዓይነት ረጅም ጉዞ አጋጥሞኝ አያውቅም!" ይል ጀመር ሮማን። ከፍተኛ የውሃ ጥም በተጨማሪ ምን ያህል በሕይወት እንደሚቆዩ እርግጠኞች መሆን አልቻሉም። አንዳንድ ጊዜ መርከቧ ላይ ገብተው መርከበኞቹን ዕርዳታ ለመጠየቅ ያስቡ ነበር። ነገር ግን ለቅጣት ሲባል ወደ ውቅያኖሱ ሊወረወሩ እንደሚችሉ በማሰባቸው መጠየቅ ፈሩ።ጆን እና ጓደኞቹ የያዙት ውሃ እና ምግብ ካሰቡት ጊዜ አስቀድሞ አለቀባቸው። በአምስተኛው ቀን ዕርዳታን ለመጠየቅ ተነሱ። የመርከቡ አለቃ ራሱ ሊቀበላቸው ሄደ። ጋናዊው ወጣት ጥሩ አቀባበል እንደተደረገላቸው በማየቱ ለድፍረታቸው ምስጋናውን አቀረበ።

ከዚህ በኋላ ነው መርከቧ ወደ ብራዚል እያመራች እንደምትገኝ የተረዱት። ይሁን እንጂ መርከብ ላይ ቆይተው ወደ አይቦሪ ኮስት እንዲመለሱ ወይም ለብራዚል መንግሥት ባለሥልጣን እንደሚሰጧቸው ተነግራቸዋል። ጆን ወደ አቢጃን እንዲመለስ የቀረበለትን የሁለት ሺህ ዶላር እገዛ ያልተቀበለው፥ ተመልሶ ላለመምጣት የወሰነ መሆኑ እንደሆነ ገልጿል።

 ውሃ፣ ዳቦ እና ስኳር የብራዚል ፌደራል ፖሊስ ለአራቱ ህገወጥ የናይጄሪያ ስደተኞች የሰጣቸው የመጀመሪያ የነፍስ አድን ዕርዳታዎች ነበሩ
ውሃ፣ ዳቦ እና ስኳር የብራዚል ፌደራል ፖሊስ ለአራቱ ህገወጥ የናይጄሪያ ስደተኞች የሰጣቸው የመጀመሪያ የነፍስ አድን ዕርዳታዎች ነበሩ

የነፍስ አድን ዕርዳታ ልመና

5,500 ኪሎ ሜትርን ለአሥራ አራት ቀናት በድብቅ ከተጓዙ በኋላ አራቱም ናይጄሪያውያን ወደ መዳረሻቸው ደረሱ። በእጃቸው የቀረው ትንሽ የባሕር ውሃ ብቻ ነበር። የአካባቢውን ቅዝቃዜው መቋቋም አልቻሉም። ከነበራቸው ትንሽ ጥንካሬ ጋር በእርግጠኝነት ትንሽ ተስፋ ነበራቸው። በዚያን ጊዜ ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ የባሕር ዳርቻ ጠባቂዎች ሞተሮቻቸውን ወደ ጭነት መርከብ ሲያስጠጉ ሰሙ። ጎህ ሲቀድ ነበርና ሮማን ሕይወቱን ለማዳን ስለወሰነ በመሪው ላይ ተቀመጦ፥ “እባክህ እርዳን” እያለ መጮህ ጀመረ።

በእዚህ አስከፊ ሁኔታዎች ውስጥ የሚገኙ ሰዎች ምስሎች በዓለም ዙሪያ በመሰራጨት፥ በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች በየቀኑ ከአገራቸው ለማምለጥ እና በሕይወት ለመትረፍ የሚያደርጉትን ተስፋ አስቆራጭ ድርጊት አጉልቶ ያሳያል። ጥገኝነትን ያገኙት በደቡብ ምሥራቅ ብራዚል በምትገኘው ቪቶሪያ ወደብ ነበር። ከመካከላቸው ሁለቱ ወደ ናይጄሪያ ለመመለስ የወሰኑት ወደፈለጉት ቦታ መድረስ ስላልቻሉ ነው።

በሳን ፓውሎ በሚገኝ የስካላብሪኒ የስደተኞች ማዕከል ውስጥ፣ ሮማን ኢቢሜኔ ንጹህ አልጋ፣ መታጠቢያ ቤት፣ ምግብ፣ የቋንቋ ትምህርት እና የሕግ እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ተሰጠው
በሳን ፓውሎ በሚገኝ የስካላብሪኒ የስደተኞች ማዕከል ውስጥ፣ ሮማን ኢቢሜኔ ንጹህ አልጋ፣ መታጠቢያ ቤት፣ ምግብ፣ የቋንቋ ትምህርት እና የሕግ እና የስነ-ልቦና ድጋፍ ተሰጠው

በጭንቀት ወቅት የተዘረጋ እጅ

ሮማን እና አብረውት ከነበሩት መካከል አንዱ ወደ ሳን ፓውሎ ደረሱ። ወደ ብራዚል ሲደርሱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ስደተኞችን ተቀብሎ ከ80 ለሚበልጡ ዓመታት ሲረዳ የቆየ የስካላብሪኒ ገዳማውያን ማኅበር የስደተኞች መርጃ ድርጅት ተቀበላቸው። ጆንም ከረጅም የመርከብ ጉዞ በኋላ በብራዚል ሰሜናዊ ክፍል ወደምትገኝ ማካፓ ደረሰ። እርሱ ወደ ሳን ፓውሎ ለመሄድ ሲወስን ጓደኛው የፈረንሣይ ደሴት ወደሆነች ጉያና ጉዞውን ቀጠለ።

እነዚህ ሁለት አፍሪካውያን ስደተኞች አሁን የሚኖሩበት ሥፍራ አላቸው፤ ቀጣዩ ተግዳሮታቸው ሥራን መጀመር የሚያስችል ቋንቋ መማር ነው። ጆን መካኒክ ነው። በተቻለ ፍጥነት ተሽከርካሪዎችን ለመጠገን ተስማሚ ልብስ ማግኘት ይፈልጋል። ሮማን የብየዳ ሥራን እና ሌሎች ብዙ የሥራ ዕድሎችን አግኝቷል። አዲሱ ማኅበረሰብ ጋር ለመቀላቀል ሁለቱም በስደት ታሪካቸው ውስጥ አዲስ ምዕራፍ እየጀመሩ ይገኛሉ።

እንደ ባለሙያዎች ገለጻ፣ ይህ ምዕራፍ በጀልባው ላይ ከሚደርስ ጉዳት የበለጠ ጭንቀት ሊፈጥር ይችላል። ምክንያቱም ባብዛኛው የባሕል ግጭት፣ ማኅበራዊ ተቃውሞ እና ለሰው ልጅ ስቃይ የሚሰጥ ግድየለሽነት ከፍተኛ የብስጭት ምንጮች ናቸው።

ስደተኞቹ ከዚህ በፊት ባላቸው ተሞክሮ መከራን በሚገባ ያውቃሉ። መከራን የበለጠ ለመቋቋም መጠለያን፣ ምግብን፣ የቋንቋ ትምህርቶችን እና የሕግ ድጋፍን ከመስጠት በተጨማሪ ከረዥም እና አሰቃቂ ጉዞ በኋላ በምድር ላይ የተሻለ ሕይወት እንዲኖራቸው የስነ-ልቦና ድጋፍ ይሰጣቸዋል።

እንደ ሌሎች ስደተኞች ሁሉ፣ ጆን ኢኮው የፖርቹጋል ቋንቋ ትምህርት ጀመረ
እንደ ሌሎች ስደተኞች ሁሉ፣ ጆን ኢኮው የፖርቹጋል ቋንቋ ትምህርት ጀመረ
ጆን ኤኮው ከመላው ዓለም ከመጡ ስደተኞች ጋር ምሳ ከበላ በኋላ፣ በሳኦ ፓውሎ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የምግብ ማቅረቢያ ሳህኖችን በማጠብ ያግዛል
ጆን ኤኮው ከመላው ዓለም ከመጡ ስደተኞች ጋር ምሳ ከበላ በኋላ፣ በሳኦ ፓውሎ በሚገኘው የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የምግብ ማቅረቢያ ሳህኖችን በማጠብ ያግዛል
በአይቮሪ ኮስት ጆን ኢኮው የመኪና መካኒክ ሆኖ ይሠራ ነበር
በአይቮሪ ኮስት ጆን ኢኮው የመኪና መካኒክ ሆኖ ይሠራ ነበር
ሮማን ኢቢሜኔ እና ሌሎች ሦስት ናይጄሪያውያን ከሞት በተረፉበት ወቅት በተንቀሳቃሽ ስልክ የቀረጸውን የቪዲዮ ምስል ሲመለት
ሮማን ኢቢሜኔ እና ሌሎች ሦስት ናይጄሪያውያን ከሞት በተረፉበት ወቅት በተንቀሳቃሽ ስልክ የቀረጸውን የቪዲዮ ምስል ሲመለት

 

23 September 2023, 17:01