ፈልግ

የሚያዝያ 6/2016 ዓ.ም የአራተኛው የዐብይ ጾም ሳምንት ንባባት እና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የሚያዝያ 6/2016 ዓ.ም የአራተኛው የዐብይ ጾም ሳምንት ንባባት እና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ 

የሚያዝያ 6/2016 ዓ.ም የአራተኛው የዐብይ ጾም ሳምንት ንባባት እና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

እግዚአብሔር አቅፎ ከኃጢአታችን ነፃ ያወጣናል!

የእለቱ ንባባት

1.    2ቆሮንጦስ 36፡14-16.ን19-23

2.    መዝሙር 136

3.    ኤፌሶን 2፡4-10

4.    ዮሐንስ 3፡14-21

የእለቱ ቅዱስ ወንጌል

 

ሙሴ በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ፣ የሰው ልጅም እንዲሁ ሊሰቀል ይገባዋል፤ ይኸውም በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው ነው።

“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከ መስጠት ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወድዷልና። እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ለመፍረድ ሳይሆን፣ ዓለምን በእርሱ ለማዳን ነው። በእርሱ የሚያምን ሁሉ አይፈረድበትም፤ በእርሱ የማያምን ግን በአንዱ በእግዚአብሔር ልጅ ስም ስላላመነ፣ አሁኑኑ ተፈርዶበታል። ፍርዱም ይህ ነው፤ ብርሃን ወደ ዓለም መጣ፤ ሰዎች ግን ሥራቸው ክፉ ስለ ነበረ፣ ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ወደዱ፤ ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላል፤

አድራጎቱም እንዳይገለጥበት ወደ ብርሃን አይመጣም። በእውነት የሚመላለስ ግን ሥራው በእግዚአብሔር የተሠራ መሆኑ በግልጽ ይታይ ዘንድ ወደ ብርሃን ይመጣል።”

 

የእለቱ የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዚህ የዐብይ ጾም አራተኛ እሑድ ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል የኒቆዲሞስን ምሳሌ ያቀርብልናል (ዮሐ. 3፡14-21)፣ ፈሪሳዊ፣ “የአይሁድ አለቃ” (ዮሐ 3፡1) የሆነ ሰው ነበር። ኢየሱስ ያደረጋቸውን ምልክቶች አይቶ ከእግዚአብሔር የተላከ መምህር መሆኑን እርሱ አወቆ ሌሎች ሰዎች እንዳያዩት በማሰብ በሌሊት ሊገናኘው ሄደ። ጌታ ተቀበለው፣ ከእርሱ ጋር ተነጋገረ እና አለምን ሊያድን እንጂ ሊፈርድ እንዳልመጣ ገለጠለት (ዮሐንስ 3፡17)። እስቲ በዚህ ላይ ቆም ብለን እናስብ፡ ኢየሱስ የመጣው ለማዳን እንጂ ለመኮነን አይደለም። ይህ ቆንጆ የሆነ ነገር ነው!

ብዙ ጊዜ በወንጌል ውስጥ ክርስቶስ የሚያገኛቸውን ሰዎች ሐሳብ ሲገልጽ፣ አንዳንድ ጊዜ እንደ ፈሪሳውያን ያሉ የሐሰት አመለካከቶቻቸውን ሲገልጥ እናያለን (ማቴ. 23፡27-32)፣ ወይም በሕይወታቸው መዛባት ላይ እንዲያስቡ፣ እንደ ሳምራዊቷ ሴት (ዮሐ. 4፡5-42) ያሉ ሰዎችን ሲገናኝ ሐሳባቸውን አንዲያጠሩ ያደርጋል። በፊቱ ምንም ምስጢር የለም፡ በልቡ ያነባቸዋል። ይህ ችሎታው ሊረብሽ ይችላል ምክንያቱም በመጥፎ ጥቅም ላይ ከዋለ ሰዎችን ይጎዳል፣ ምሕረት ለሌለው ፍርድ ያጋልጣል። በእርግጥም ማንም ሰው ፍጹም አይደለም፡ ሁላችንም ኃጢአተኞች ነን፣ ሁላችንም እንሳሳታለን፣ እና ጌታ ድክመታችንን እውቀቱን ተጠቅሞ እኛን ለመኮነን ቢጠቀም፣ ማንም ሊድን አይችልም ነበር።

ነገር ግን እንደዚህ አይደለም። በእርግጥም ሕይወታችንን ለመቀበል፣ ከኃጢአት ነፃ ለማውጣትና እኛን ለማዳን እንጂ፣ ጣቱን ወደ እኛ ለመቀሰር አይሻም። ኢየሱስ እኛን ለፍርድ ለማቅረብ ወይም እኛ ላይ ለመፍረድ ፍላጎት የለውም፣ ማናችንም እንዳንጠፋ ይፈልጋል። ጌታ በእያንዳንዳችን ላይ ያለው እይታ እኛን የሚያደነቁረን እና አስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ የሚከቱት ዓይነ ስውር ብርሃን ሳይሆን ረጋ ያለ የወዳጅ መብራት ብልጭታ ሲሆን ይህም በራሳችን ውስጥ ያለውን መልካም ነገር እንድናይ እና ክፉውን ዝንባሌዎቻችንን እንድንገነዘብ ይረዳናል፣ ስለዚህ በጸጋው ረዳትነት ተመልሰን እንድንፈወስ እድል ይሰጠናል።

ኢየሱስ ዓለምን ሊያድን እንጂ ሊፈርድ አልመጣም። ብዙውን ጊዜ ሌሎችን የምንኮን እኛን እናስቡ፣ ብዙ ጊዜ፣ መጥፎ መናገር፣ በሌሎች ላይ ሐሜት ለመፈለግ መሄድ እንወዳለን። ጌታ እኛን ሁላችንም ይህን መሐሪ እይታ እንዲሰጠን፣ እርሱ እኛን እንደሚመለከተን እኛም ሌሎችን እንድንመለከት እንጠይቀው።

እርስ በርሳችን መልካም ነገር እንድንመኝ ማርያም በአማልጅነቷ ትርዳን።

 

ምንጭ፡ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ መጋቢት 01/2016 ዓ.ም ካደረጉት የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የተወሰደ!

 

 

 

 

13 April 2024, 09:52