ፈልግ

ተቃዋሚዎች በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ሲጸልዩ ተቃዋሚዎች በአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፊት ለፊት ሲጸልዩ   (2020 Getty Images)

የአሜሪካ ብጹአን ጳጳሳት የሃይማኖት ነፃነትን በጸሎት፣ በማሰላሰል እና በተግባር ማበረታታት ይገባል አሉ

የዩናይትድ ስቴትስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹአን ጳጳሳት ጉባኤ ከሰኔ 15 እስከ 22 ቀን 2017 ዓ.ም. ድረስ በተከበረው ‘የሃይማኖት ነፃነት ሳምንት’ ፥ ምእመናንን በጸሎት፣ በትምህርት እና በሕዝባዊ ተግባር የሃይማኖት ነፃነትን ለሁሉም አማኞች እንዲያበረታቱ በመጋበዝ አክብረዋል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

ሰኔ 15 በሚከበረው የቅዱስ ጆን ፊሸር እና የቅዱስ ቶማስ ሞር በዓል የተጀመረው በዩናይትድ ስቴትስ የምትገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ዘንድ የሚከበረው የሃይማኖታዊ ነፃነት ሳምንት፥ ሰኔ 22 በሚከበረው የቅዱስ ጴጥሮስ ወጳውሎስ ክብረ በዓል መጠናቀቁ ተገልጿል።

የዩናይትድ ስቴትስ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ብጹአን ጳጳሳት ጉባኤ (USCCB) ተነሳሽነት የሆነው የሃይማኖት ነፃነት ሳምንት ክብረ በዓል ምዕመናን “ለካቶሊኮች እና ለሁሉም እምነት ተከታዮች አስፈላጊ የሆነውን የሃይማኖት ነፃነት መብት” እንዲያበረታቱ በመጋበዝ መልዕክቱን አስተላልፏል።

'የተስፋ ምስክሮች'
“የፖለቲካ ጽንፈኝነት በሃይማኖት ነፃነት ላይ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ” እንዲሁም ከማህጸን ውጭ የሚከናወን ጽንስ ህጋዊነት፣ ስደተኞችን የሚያገለግሉ የካቶሊክ ቤተክርስቲያን አገልጋዮችን ማስፈራራት እና የወላጆችን የትምህርት ምርጫ የመሳሰሉ ጉዳዮችን በሚያነሳው በዩናይትድ ስቴትስ ስላለው የሃይማኖት ነፃነት ሁኔታ ላይ የሚያተኩረው የጉባኤው የ 2025 ዓ.ም. ዓመታዊ ሪፖርት ላይ የተመሰረተው የዘንድሮው በዓል “የተስፋ ምስክሮች” በሚል መሪ ቃል እንደተከበረ ተገልጿል።

ከዚህም በተጨማሪ የዘንድሮው ጭብጥ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ ካወጁት የኢዮቤልዩ ዓመት ጋር የተያያዘ ነው ሲሉ ወደ ‘ሃይማኖታዊ ነፃነት ሳምንት’ የተቀየረውን የመጀመሪያውን ‘የነፃነት ሳምንታት’ ክብረ በዓል ሀሳብ ያቀረቡት እና በኢሊኖይ የስፕሪንግፊልድ ሀገረ ስብከት ጳጳስ ብጹእ አቡነ ቶማስ ፓፕሮኪ ተናግረዋል።

ብጹእ አቡነ ፓፕሮኪ ለቫቲካን ዜና እንደተናገሩት በቅዱስ ጳውሎስ አባባል በመነሳሳት ተስፋ ማድረግ እንደማያሳፍር ጠቅሰው፥ ክብረ በዓሉ ‘ስለ መጪው ጊዜ እና እግዚአብሔር ከዘላለም ሕይወት ጋር በተያያዘ በሚሰጠን ተስፋ ላይ እርግጠኞች እንድንሆን ያደርገናል’ ብለዋል።

የሃይማኖት ነፃነት ሳምንት የካቶሊክ እምነት ተከታዮች በዩናይትድ ስቴትስ እና በዓለም ዙሪያ የሃይማኖት ነፃነት እንዲጠበቅ ተግተው እንዲጸልዩ ለመጋበዝ፣ በሃይማኖታዊ ነፃነት ትርጉም ላይ እንዲያሰላስሉ እና የሃይማኖት ነፃነትን ለመጠበቅ አስፈላጊው እርምጃ እንዲወሰድ የሚያበረታታ እንደሆነም ጭምር ያስረዱት ብጹእነታቸው፥ ስለዚህም እነዚህ ሦስት ደረጃዎች መጸለይ፣ ማሰላሰል እና ከሃይማኖት ነፃነት አንፃር ለተስፋ ምስክሮች እንድንሆን በሚያደርጉ መንገዶች ላይ እርምጃ እንዲወሰድ ማድረግ ነው ብለዋል።

ነፃነት እና እውነት
ብጹእ አቡነ ፓፕሮኪ ከቫቲካን ዜና ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ የሃይማኖት ነፃነት ጥያቄ ቤተክርስቲያን ነጻነትን አስመልክታ ከምታስተምረው አስተምህሮ አንፃር መረዳት አለበት ያሉ ሲሆን፥ ብጹእነታቸው የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ዮሐንስ ጳውሎስ ዳግማዊን ትምህርት በመጥቀስ፣ እውነተኛ ነፃነት ከእውነት ጋር የተዛመደ መሆኑን እና አንድ ሰው የሚፈልገውን ሁሉ የማድረግ ችሎታ ካለው የማድረግ “ፈቃድ” ሊጠየቅ እንደማይገባ አስረድተዋል።

ብጹእ አቡነ ፓፕሮኪ አክለውም “እምነታችንን በነፃነት ለመተግበር፣ ትክክል የሆነውን ለመከተል እና እውነትን ለመናገር እንድንችል ቤተክርስትያን ነፃነት መኖሩን ታስተምራለች ያሉ ሲሆን፥ በመቀጠልም ከመብት ጋር በተያያዘ ግዴታዎችን መፈጸም እንደሚገባ ጠቁመው፥ በቤተክርስቲያን ውስጥ ብቻ ሳይሆን “በሲቪሉ ማህበረሰብ አውድ” ውስጥም ጭምር ተግባራዊ ሊደረግ ይገባል ብለዋል።

ብጹእነታቸው በመጨረሻም የጋራ ጥቅምን እና ሀገሪቷን ለማገዝ ብሎም ነፃነቷን ለማስጠበቅ፥ “የነፃነታችን እና የመብታችን ጥያቄ ብቻ ሳይሆን ጥሩ ዜጋ የመሆን ግዴታዎች አለብን” በማለት አጠቃለዋል።

23 Jun 2025, 14:34