ፈልግ

የመስከረም 25 ቀን 2018 ዓ. ም  የ25ኛ መደመኛ ሰንበት ንባባት እና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ የመስከረም 25 ቀን 2018 ዓ. ም የ25ኛ መደመኛ ሰንበት ንባባት እና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ 

የመስከረም 25 ቀን 2018 ዓ. ም የ25ኛ መደመኛ ሰንበት ንባባት እና የቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የዕለቱ ንባባት

1.             አሞፅ 8፡4-7

2.          መዝሙር 112

3.          ጢሞቲዎስ 2፡1-8

4.          ሉቃስ 16፡1-13

የዕለቱ ቅዱስ ወንጌል

የዐመፀኛው መጋቢ ምሳሌ

ደግሞም ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ አለ፦ “መጋቢ የሚያገለግለው አንድ ባለ ጠጋ ሰው ነበረ፤ ‘ይህ ሰው ያለህን ይበትናል፤’ የሚል ክስ በእርሱ ዘንድ አቀረቡ። ጠርቶም ‘ይህ የምሰማብህ ነገር ምንድነው? ወደ ፊት ለእኔ መጋቢ ልትሆን አትችልምና የመጋቢነትህን ሂሳብ አስረክበኝ፤’ አለው። መጋቢውም በልቡ ‘ጌታዬ መጋቢነቱን ከእኔ ይወስዳልና ምን ላድርግ? ለመቈፈር ኃይል የለኝም፤ መለመንም አፍራለሁ። ከመጋቢነቱ ብሻር በቤታቸው እንዲቀበሉኝ የማደርገውን አውቃለሁ፤’ አለ። የጌታውንም ባለ ዕዳዎች እያንዳንዳቸውን ጠርቶ የመጀመሪያውን ‘ለጌታዬ ምን ያህል ዕዳ አለብህ?’ አለው። እርሱም ‘መቶ ማድጋ ዘይት’ አለ። ‘የጽሑፍ ማስረጃህን እንካ፥ ፈጥነህም ተቀምጠና ኀምሳ ብለህ ጻፍ፤’ አለው። በኋላም ሌላውን ‘አንተስ ስንት ዕዳ አለብህ?’ አለው። እርሱም ‘መቶ ዳውላ ስንዴ’ አለ። ‘የጽሑፍ ማስረጃህን እንካ ሰማንያ ብለህም ጻፍ፤’ አለው። ጌታውም ዐመፀኛውን መጋቢ ስለ ብልኃቱ አመሰገነው፤ የዚህ ዓለም ልጆች ለትውልዳቸው ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና። እኔም እላችኋለሁ፤ የዐመፃ ገንዘብ ሲያልቅ በዘለዓለም ቤቶች እንዲቀበሉአችሁ፥ በእርሱ አማካኝነት ወዳጆችን ለራሳችሁ አብጁ።

“በትንሹ የታመነ በብዙም እንዲሁ የታመነ ነው፤ በትንሹ የሚያታልል በብዙም እንዲሁ ያታልላል። እንግዲያስ በዐመፃ ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ እውነተኛውን ገንዘብ ማን አደራ ይሰጣችኋል? በሌላ ሰው ገንዘብ ካልታመናችሁ፥ የእናንተን ማን ይሰጣችኋል? ለሁለት ጌቶች መገዛት የሚቻለው አንድም አገልጋይ የለም፤ ወይ አንዱን ሲጠላ ሌላውን ይወዳል፤ ወይ አንዱን ሲጠጋ ሌላውን ይንቃል። ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”

የዕለቱ ቅዱስ ወንጌል አስተንትኖ

የተወደዳችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ እንደምን አረፈዳችሁ!

በዛሬው ስርዓተ አምልኮ ላይ የተነበበው ቅዱስ ወንጌል ውስጥ ያለው ምሳሌ (ሉቃ. 16፡1-13) ለእኛ ለመረዳት ትንሽ አስቸጋሪ ይመስላል። ኢየሱስ ስለ ሙስና የሚገልጽ ታሪክ ተናግሯል:- ሐቀኝነት የጎደለው ሥራ አስኪያጅ ሰርቆ ጌታው ሲያገኘው ከሁኔታው ለመውጣት ብልህ ሆኖ የሚያደርገውን ጥረት እናያለን። እራሳችንን እንጠይቃለን፡ ይህ በሙስና የተዘፈቀ ስራ አስኪያጅ ብልህነት ምንድን ነው እና ኢየሱስ ምን ሊነግረን ይፈልጋል?

በዚህ ታሪክ ውስጥ ሙሰኛው ሥራ አስኪያጁ የጌታውን ንብረት በመጠቀሙ ለችግር እንዴት እንደ ተዳረገ እንመለከታለን። አሁን ሂሳቡን ሰርቶ ለጌታው ማስረከብ አለበት፣ ከእዚያን በኋላ ስራውን ያጣል። ግን ተስፋ አልቆረጠም ለራሱ እጣ ፈንታ እራሱን አይተወም እና ከእጣ ፈንታው ጋር አይጫወትም። በተቃራኒው ወዲያውኑ በብልሃት ይሠራል፣ መፍትሄ ይፈልጋል እና መፍትሄ ፈጣሪ ይሆናል። ኢየሱስ “የዚህ ዓለም ልጆች ከመሰሎቻቸው ጋር በሚኖራቸው ግንኙነት ከብርሃን ልጆች ይልቅ ብልኆች ናቸውና” (ሉቃስ 16፡8) ሲል በፊታችን የሚያስቆጣ መንገድ አድርጎ ይህን ታሪክ ተጠቅሞበታል። በጨለማ ውስጥ የሚንቀሳቀሱ፣ በተወሰኑ ዓለማዊ ደረጃዎች፣ በችግር ጊዜም እንኳ እንዴት ማለፍ እንደሚችሉ ሲያውቁ፣ ከሌሎች ይልቅ ብልህ መሆንን ያውቃሉ። ይልቁኑ የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት፣ ማለትም እራሳችን፣ አንዳንድ ጊዜ ተኝተናል ወይም የዋህ ነን፣ ከችግሮች መውጫ መንገዶችን እንዴት መፈለግ እንዳለብን አናውቅምና። ለምሳሌ ስለግል ወይም ማህበራዊ ቀውስ እያሰብኩ ነው፣ ነገር ግን ስለ ቤተክርስትያን ችግር፡ አንዳንድ ጊዜ ተስፋ መቁረጥ እንዲያሸንፈን እንፈቅዳለን ወይም ተጎጂውን ማጉረምረም እና መጫወት እንጀምራለን። ይልቁኑ ኢየሱስ ወንጌልን በመከተል ብልህ መሆን፣ ንቁ እና በትኩረት እውነታውን ለመረዳት እና ለራሳችን እና ለሌሎች ጥሩ መፍትሄዎችን ለማግኘት አዲስ ነገር ፈጣሪ መሆን እንደምንችል ተናግሯል።

ኢየሱስ የሚሰጠን ሌላ ትምህርት ግን አለ። በእርግጥ እኛ የምንጠይቀው የአስተዳዳሪው ብልህነት ምንድን ነው? ዕዳ ውስጥ ለነበሩት ቅናሽ ለማድረግ ወሰነ፣ እናም ጓደኞቹ ሆኑ እና ጌታው ሲያባርረው ሊረዱት እንደሚችሉ ተስፋ አድርጓል። ለራሱ ሀብት ከማካበት በፊት አሁን ግን በተመሳሳይ መንገድ እየሰረቀ ወደፊት ሊረዱት የሚችሉ ጓደኞችን ለማፍራት ይጠቀምበታል። ከዚያም ኢየሱስ ቁሳዊ ነገሮችን ስለምንጠቀምበት መንገድ ያስተምረናል:- “ስለዚህ እላችኋለሁ፤ የዚህ ዓለም ገንዘብ ባለቀ ጊዜ በዘላለም ቤት ተቀባይነት እንዲኖራችሁ፣ በዚሁ ገንዘብ ወዳጆችን ለራሳችሁ አፍሩበት” (ሉቃስ 16፡9) የዘላለም ሕይወትን ለመውረስ በዚህ ዓለም ውስጥ ሸቀጦችን ማከማቸት አያስፈልግም፣ ነገር ግን ዋናው ነገር በወንድማማችነት ግንኙነታችን ውስጥ የምንገልጸው ፍቅር ነው የሚያስፈልገን። ኢየሱስ ከእኛ የሚጠይቀው ይህን ነው፡ የዚህን አለም እቃዎች ለራሳችሁ እና ለራስ ወዳድነት ብቻ አትጠቀሙበት፡ ነገር ግን ጓደኝነትን ለመፍጠር፡ ጥሩ ግንኙነት ለመፍጠር፡ በበጎ አድራጎት ስራ ለመስራት፡ ወንድማማችነትን ለማስፋፋት እና ለደካሞች እንክብካቤ ለማድረግ ትጉ ይለናል።

ወንድሞችና እህቶች፣ በዓለማችን ዛሬም በወንጌል ውስጥ እንዳለ የሙስና ታሪኮች አሉ፡- ሐቀኝነት የጎደለው ምግባር፣ ኢ-ፍትሃዊ ፖሊሲ፣ የግለሰቦችንና የተቋማትን ምርጫ የሚቆጣጠር ራስ ወዳድነት፣ እና ሌሎችም በርካታ አጉል ሁኔታዎች አሉ። እኛ ክርስቲያኖች ግን ተስፋ እንድንቆርጥ ወይም ይባስ ብለን ነገሮችን እንድንተው፣ ግዴለሽ እንድንሆን አይፈቀድልንም። በአንጻሩ እኛ የተጠራነው በወንጌል ጥበብና ብልሃት በጎ ነገርን በመስራት የዚህን ዓለም ሸቀጣ ሸቀጦችን በቁሳቁስ ብቻ ሳይሆን ከጌታ የተቀበልነውን ስጦታ ሁሉ ተጠቅመን እራሳችንን ለማበልጸግ አይደለም። ግን የወንድማማችነት ፍቅር እና ማህበራዊ አብሮነት ለመፍጠር ነው የተጠራነው። ይህ በጣም አስፈላጊ ነው፡ በባህሪያችን ማህበራዊ ጓደኝነት መፍጠር እንችላለን።

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንደ ራሷ የመንፈስ ድሆች እንድንሆን እርስ በርሳችንም በበጎ አድራጎት ሥራ ባለጸጎች እንድንሆን በአማላጅነቷ ትረዳን ዘንድ እንጸልይ።

 

04 Oct 2025, 23:06