ለኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት የተላከ የኅዘን መግለጫ
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን የጳጳሳት ጉባኤ ጥቅምት 9 ቀን 2018 ዓ.ም. የተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈተ ሕይወት የሰማነው በታላቅ ሀዘን ነው፡፡
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን በታላቁ አባት በተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ ሕልፈተ ሕይወት የተሰማትን ጥልቅ ኀዘን ትገልጻለች። ሀገራችን ታላቅ አባትን አጥታለች!
ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ዑመር ኢድሪስ የብዙዎች አባት፣ የሰላም እና የአንድነት ተምሳሌት ነበሩ። ከኢትዮጵያ ካቶሊክ ቤተክርስቲያን ጋር በተለይም በሀገራችን ሰላም እና እርቅን ለማውረድ በርካታ ስራዎችን በጋራ ሰርተዋል።
ቤተክርስቲያናችን በእኚህ ታላቅ አባት ህልፈተ ህይወት የተስማንን ሀዘን እየገለጽን ለቤተቦቻቸው፣ ለወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ ለእስልምና እምነት ተከታዮች እና ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እውነተኛ መጽናናትን እንመኛለን።
ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ
ሊቀጳጳሳት ዘካቶሊካውያን
የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝደንት
20 Oct 2025, 14:22