ፈልግ

የትምህርት ዓለም የኢዮቤልዩ በዓል የትምህርት ዓለም የኢዮቤልዩ በዓል 

የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች የምርምር ጥምረት በትምህርት ዓለም የኢዮቤልዩ በዓል እንደሚሳተፍ ተገለጸ

የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፍ ስትራቴጂያዊ የምርምር ጥምረት (SACRU) ከጥቅምት 17-21/2018 ዓ. ም. ድረስ “የሳይንሳዊ ምርምር ነፃነት” በሚል ርዕሥ የተዘጋጀ የትምህርት ዓለም የኢዮቤልዩ በዓልን በማክበር ላይ እንደሚገኝ እና ለቅድስት መንበር ዲፕሎማሲያዊ ተወካዮች ከቀረበ በኋላ የጥምረቱ ልዑካን ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ ባቀረቡት ሳምንታዊ የጠቅላላ ትምህርተ ክርስቶስ አስተምህሮ ላይ መሳተፉ ታውቋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

የያዝነው ሳምንት ቅዱስ ልበ ኢየሱስ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ መሥራች አባል የሆነበት እና የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፍ ስትራቴጂያዊ የምርምር ጥምረት የሚስተናገዱበት እንደሆነ ታውቋል።

የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፍ ስትራቴጂያዊ ምርምር (SACRU) በካቶሊክ ማኅበራዊ አስተምህሮ በመመራት በምርምር እና በማስተማር፣ በዓለም አቀፍ ተሳትፎ እና በትብብር የላቀ ሥራ የሚሠሩ ዩኒቨርሲቲዎች ጥምረት ነው። የምርምር ጥምረቱ ስትራቴጂያዊ ዓላማ በአጋር አገራት መካከል ዓለም አቀፍ ትብብርን ማዳበር ሲሆን፥ ለጋራ ጥቅም ሲባል በዓለም ደረጃ እውቀትን እና ከፍተኛ ትምህርትንም ያሳድጋል።

“የሳይንሳዊ ምርምር ነፃነት” በሚል ርዕሥ ከጥቅምት 17 እስከ 21/2018 ዓ. ም. በሚከበረው የትምህርት ዓለም የኢዮቤልዩ በዓል ቀናት ውስጥ ከአውስትራሊያ ካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ እና ከሮም ካምፓስ ከጥምረቱ ስምንት አባል ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ 14 የዶክትሬት ማ ዕረግ ተማሪዎች ይሳተፋሉ።

“በቀጣዮቹ ትውልድ ተመራማሪዎች እና ምሁራን በሚሰጥ ምርጥ ስልጠና አማካኝነት በዓለም ላይ ላለው የጋራ ጥቅም ብልጽግና በእውነት አስተዋጽኦ ማድረግ ስለምንችል ተነሳሽነቱ ለእኛ እጅግ አስፈላጊ እንደሆነ እናምናለን” ሲሉ የ2025-2028 የጥምረቱ ፕሬዝዳንት እና ፖርቱጋል የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ ሃላፊ ኢዛቤል ካፔሎአ ጊል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። “በእየጨመረ በሚሄድ ዓለም ውስጥ እንደ ታማኝነት እና የምርምር ነፃነት ያሉ ጉዳዮች ለሳይንሳዊ ዕድገት ወሳኝ ስለሆኑ ሳይንሳዊ ምርምሩ ማኅበረሰቡን እንዲጠራጠሩት ሳይሆን እንዲታመንበት ያስችለዋል” ብለዋል።

“የሳይንሳዊ ምርምር ነፃነት” በሚል ርዕሥ የተዘጋጀ የትምህርት ዓለም ኢዮቤልዩ
“የሳይንሳዊ ምርምር ነፃነት” በሚል ርዕሥ የተዘጋጀ የትምህርት ዓለም ኢዮቤልዩ

የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፍ ስትራቴጂያዊ የምርምር ጥምረት (SACRU) ዋና ጸሐፊ እና በካቶሊክ ዩኒቨርሲቲ የግብርና፣ የምግብ እና የአካባቢ ሳይንስ ፋኩልቲ ዲን የሆኑት ፒየር ሳንድሮ ኮኮንሴሊ እንደተናገሩት፤፤ “በምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ውጤታማ የሆነ ጥምረት ለመፍጠር ወጣቶችን ማሳተፍ አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸው፥ “አዳዲስ ተመራማሪዎች ከምርምር በስተጀርባ ያለ እውነተኛ አንቀሳቃሽ ኃይል እንደሆነ እና በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች የላቀ ምርምርን የሚያበረታታ ጠንካራ ፈጠራ ያለበት ጥምረት ማዳበር የምንችለው በተለያዩ የእውቀት ዘርፎች ላይ የላቀ ምርምርን የሚያበረታታ ጠንካራ ጥምረት መፍጠር ስንችል ነው” ብለዋል። “ዘመናዊ ተግዳሮቶችን መፍታት የራሳቸውን የጥናት ዘርፎች ከማጠናከር ባለፈ ከሌሎች ዘርፎች ጋር በመነጋገር ፈጠራን እና ትብብርን የሚያበረታታ ተሻጋሪ አመለካከትን የሚያዳብሩ ተመራማሪዎችን እንደሚጠይቅ ገልጸው፥ “በሮም የሚገኘው የመኸር ወቅት ትምህርት ቤት የተከፈተረው ይህንን ዓላማ ከግምት ውስጥ በማስገባት ነው” ብለዋል።

የካቶሊክ ዩኒቨርሲቲዎች ዓለም አቀፍ ስትራቴጂያዊ የምርምር ጥምረቱ ሐሙስ ጥቅምት 20/2018 ዓ. ም.  በግሎባል ትምህርታዊ መንደር የመረጃ መድረክ ላይ መሳተፉ ታውቋል። ጥምረቱ በመጨረሻም ዓርብ ጥቅምት 21/2018 ዓ. ም. ከጥምረቱ ዘጠኝ አባል ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ የአስተዳዳሪዎች ረዳት አስተዳዳሪዎች እና ሌሎች ፕሮፌሰሮች ልዑካን ቡድን ከመኸር ወቅት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጋር በመሆን ከርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ጋር እንደሚገናኙ እና ከሰዓት በኋላ ወደፊት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን እና ውጥኖችን በማስመልከት በዓለም አቀፍ ትምህርታዊ መንደር የተዘጋጀ ስብሰባን ይካፈላሉ።

 

30 Oct 2025, 14:43