ፈልግ

በሜክሲኮ ድንበር በኩል ወደ አሜሪካ ለምሻገር ጥረት የሚያደርጉ ስደተኞች በሜክሲኮ ድንበር በኩል ወደ አሜሪካ ለምሻገር ጥረት የሚያደርጉ ስደተኞች  (AFP or licensors)

የአሜሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ስደተኞችን ለሚመለከት ጉዳይ ቅድሚያን እንደሚሰጡ ተገለጸ

አዲስ የተመረጡት የአሜሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ (USCCB) ፕሬዝዳንት እና የኦክላሆማ ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ ካቫቲካን የዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፥ የአሜሪካ ካቶሊክ ጳጳሳት ለስደተኞች ያላቸውን እንክብካቤን፣ ሲኖዶሳዊነትን እና ልዩነትን በኅብረት ለማሸነፍ የሚያደርጉትን ጥረት በማስመልከት ገለጻ አድርገዋል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ ዮሐንስ መኰንን - ቫቲካን

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ የአሜሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ በኋላ ከቫቲካን የዜና አገልግሎት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፥ “የስደተኞች ጉዳይ የአሜሪካ ብጹዓን ጳጳሳት ቀዳሚ ርዕሥ ነው” ሲሉ ተናግረዋል።

አሜሪካ የስደተኞች አገር እና በስደት ልምድ የተገነባች አገር እንደመሆኗ፥ የአሜሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት በመላው አገሪቱ የሚገኙ ስደተኞችን በመደገፍ ችግሮቻቸውን ለመቀነስ ፍላጎት እንዳላቸው ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ ተናግረዋል።

ነገር ግን ከድጋፍ በተጨማሪ ጳጳሳቱ በተጽእኖ ፈጣሪነታቸው ስደተኞችን በመቀበል ረገድ ለአገሪቱ ጥቅም ሲባል የአገሪቱ ሕግ ለስደተኞች ምቹ ሂደትን ለማመቻቸት የሚያግዝ፥ ወደ አሜሪካ የሚሰደዱ ሃይማኖታዊ አገልጋዮችን ጨምሮ ለስደተኞች በሙሉ ትክክለኛ ጥብቅናን የሚቆም መሆን እንዳለበት ተናግረዋል።

በተለይም የአሜሪካ ጳጳሳት ለስደተኞች ወንድሞቻችን እና እህቶቻችን ፍላጎቶች ትኩረት በመስጠት፥ ስደትን በማስመልከት የሚነሱ አላስፈላጊ ንግግሮችን ለማስቀረት እና በስጋት የሚኖሩ የበርካታ ሰዎች ፍርሃትን ለማረጋጋት እየሠሩ መሆናቸውን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ ተናግረው፥ የአገሪቱን ድንበር መጠበቅ እና የስደት ችግር በሥርዓት መታየቱ መረጋገጥ እንዳለበት አጉልተው ገልጸዋል።

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ እነዚህን ስጋቶች በአእምሯቸው በመያዝ የአሜሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ስደተኞች እና ዜጎች በፍርሃት እና ባለመረጋጋት ውስጥ በሚገኙበት ወቅት ማረጋጋት እንደሚፈልጉ ተናግረዋል። ግባቸው ስደተኛ ወንድሞችን እና እህቶችን መደገፍ እና ስደትን የሚመለከቱ ፍትሃዊ ሕጎችን ለማውጣት እና በአገሪቱ ውስጥ መኖር ያለባቸው ሰዎች ከቤተሰቦቻቸው ጋር መቆየት እንዲችሉ ማድረግ እንደሆነ አስረድተዋል።

የኅብረት ወኪሎች እና መሣሪያዎች

በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ክፍፍል እንዴት መፈወስ እንደሚቻል የተጠየቁት አዲሱ የአሜሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት ጉባኤ (USCCB) ፕሬዝዳንት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ፥ በኅብረተሰባቸው እና በአገራችን ውስጥ እየጨመረ የመጣውን የክፍፍል አዝማሚያ ለመቋቋም የሚረዳ ምሳሌ የሚሆን የኅብረት ወኪሎች እና መሣሪያዎች ለመሆን የሚያግዝ የርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ አመራር ለመከተል እየሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል።

እርስ በርስ በመደማመጥ፣ በመከባበር እና በበጎ አድራጎት ላይ የተመሠረተ መግባባትን የመማር አስፈላጊነትን ጠቁመው፥ አለመግባባት ዘወትር በቤተ ክርስቲያን እና በጳጳሳት ጉባኤ ውስጥ የሰዎች ግንኙነት አካል እንደሆነ ተናግረው፥ አለመስማማት በመከባበር እና በመደማመጥ ሊሆን እንደሚገባ አሳስበው፥ ይህም በርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ አሥራ አራተኛ ጊዜ ብቻ ሳይሆን ከእርሳቸው ቀደም ብለው የነበሩት ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በአዲስ መንገድ እንድንጓዝ ያሳሰቡት የሲኖዶሳዊነት አካል መሆኑን ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ አስረድተዋል።

በሲኖዶሳዊነት ላይ የተካሄደ የሲኖዶስ ጉባኤ
በሲኖዶሳዊነት ላይ የተካሄደ የሲኖዶስ ጉባኤ   (foto Agência Ecclesia)

በሲኖዳላዊነት መንገድ ማደግ

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ ሲኖዳላዊነትን በማስመልከት እንደተናገሩት፥ የአሜሪካ ካቶሊክ ብጹዓን ጳጳሳት የሲኖዶሳዊነት ጉዞን ለመጓዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን ተናግረው፥ በአሜሪካ ውስጥ ያለች ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በተለያዩ ደረጃዎች ምክክር ለማድረግ የሚያስችሉ በርካታ መዋቅሮች እንዳሏት አስረድተዋል።

ቤተ ክርስቲያኗ ጥልቅ በሆነው የማዳመጥ እና የመወያየት ሂደት ውስጥ እንድትገባ የተጋበዘች መሆኗን ተናግረው፥ “እርስ በርሳችን የምንደማመጥበት፣ የምንወያይበት እና የምንተሳሰርበት ዘይቤ ያስፈልገናል” የሚለውን የነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ ተወዳጅ ቃልን በመጥቀስ፣ “በሲኖዳላዊነት መንገድ ማደጋችንን መቀጠል የምንችል ይመስለኛል” ብለዋል።

የሲኖዳዊነት ትርጉም

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ፥ በአሜሪካ ውስጥ ያለች ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን በሲኖዶሳዊነት መንገድ እያደገች እንደሆነች እና በዚህ አዲስ መንገድ ለማደግ ቁርጠኛ መሆኗን ገልጸው፥ ሲኖዳዊት ቤተ ክርስቲያን መሆን በሚለው ላይ መግባባት እና ግልጽነት የሚጎድለው መሆኑን ተናግረዋል።

በሲኖዶሳዊነት ላይ አጭር ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ፥“የሲኖዶሳዊነት አጭር ትርጉም፥ ነፍስሔር ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ በኅብረት መጓዝ” ብለው ያቀረቡት እንደ ሆነ ተናግረው፥ ይህንን ሃሳብ በማስፋት መደማመጥን፣ ለውይይት ፈቃደኛ መሆንን እና መተባበርን መማር፣ ይህን ማድረግ ቀላል ቢመስልም ነገር ግን የሲኖዶሳዊነት ትርጉም ይህ ነው” ሲሉ አስረድተዋል።

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ በቤተ ክርስቲያን መታቀፍን በማስመልከትን እንደተናገሩት፥ ቤተ ክርስቲያን የጳጳስ ወይም የሐዋርያዊ አባት ብቻ ሳትሆን ነገር ግን በኅብረት የሚኖሩ የተጠመቁ ሰዎች እና በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሃላፊነት ከተሰጣቸው ጋር ለመተባበር የሚፈልጉ ሰዎች ኅብረት ናት” ብለዋል።

“ጳጳሳት እና ካኅናት ምዕመናንን መምራት እና መንገዱን ማሳየት አለባቸው” ያሉት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ፖል ኮክሌይ፥ “ነገር ግን ሲኖዳዊት ቤተ ክርስቲያን መሆን የሁሉንም ተሳትፎ እንደሚጠይቅ እና ቤተ ክርስቲያኗን ለመገንባት እና አንድነቷን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆንን ይጠይቃል” ብለዋል።

 

17 Nov 2025, 16:30