የኢዮቤልዩ ዓመትን እንደ ዓለም 'ሰንበት' በማየት አሁንም ለማረፍ ጊዜ እንዳለ ተነገረ
አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ
ቆም ብለው ያስቡ
ይተንፍሱ
እረፍት ያድርጉ
ምድር በጭንቀት ውስጥ እንዳለች ሊገነዘቡ ይችላሉ?
የይቅርታ ምልክትን በመጠባበቅ ላይ ያሉ ሰዎች የሚሸከሙት የነፃነት ስሜት ሊሰማዎት ይችላል ወይስ አይሰማዎትም?
ማንበብ ከመቀጠልዎ በፊት አንድ ጊዜ ይተንፍሱ።
ይህ የህዳር ወር ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ “ስፔስ ነን ኮንፈንዲት” (Spes non confundit) ወይም “ተስፋ አያሳፍርም” (ሮሜ 5፡5) በሚል መሪ ቃል ያስጀመሩት የኢዮቤልዩ ዓመት አሥራ አንደኛው ወር ሲሆን፥ ብጹዕነታቸው የተስፋ ነጋዲያን እንድንሆን ያቀረቡት ጥሪ በተለይ በአሁኑ ወቅት ተስፋ የቆረጡ ሰዎች ስለ መጪው ጊዜ የሚናገሩት ትርክቶች በሕዝብ አስተሳሰቦች ላይ የበላይ ሆነው በሚታዩበት በዚህ ዘመን ከመቼውም ጊዜ በላይ ጠንካራ እና አስፈላጊ መልዕክት ነው።
ቅዱስ በር ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም. ከተከፈተ ጀምሮ አስራ አንድ ወራት ያለፉ ሲሆን፥ እነዚህ ወራቶች አጭር ቢሆኑም ዓለም በርካታ አሉታዊ እና አዎንታዊ ለውጦችን የተመለከተበት፣ የፖለቲካ ተዋናዮች የተለዋወጡበት፣ የመገናኛ ዘዴዎች ባህሪያቸው የተለወጠበት፣ ችግሮቹ ተጠናክረው ቢቀጥሉም የጂኦፖለቲካዊ ሁኔታዎች እንደገና የተዋቀሩበት፣ እንዲሁም አድልዎ፣ ብዝበዛ እና ማግለል ፈውስ የተነፈጋቸው ቁስሎች የሆኑበት ጊዜያት ነበሩ።
ከዚህ አንፃር፣ አንድ ሰው በዚህ የኢዮቤልዩ ዓመት ለራሴም ሆነ ለዓለም ያበረከትኩት አስተዋጽኦ ምንድን ነው? ምን ተጨባጭ ምልክቶችን አካትቻለሁ? ብሎ መጠየቅ ይገባል።
ርዕሠ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ የኢዮቤልዩ ዓመትን ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሳሰቡት በችግር ውስጥ ለሚገኙ እስረኞች፣ በሽተኞች፣ ወጣቶች፣ ስደተኞች፣ አዛውንቶች እና ድሆች ሰላምን፣ ማበረታቻን እና እንክብካቤን ሰጥቻለው ወይ ብሎ መጠየቅ አለበት።
በማንኛውም ሁኔታ የራስዎን አስተዋፅዖ ለማቅረብ አሁንም ጊዜ አለ።
ተስፋ ለማድረግ፣ በሌላ እርምጃ እንደገና ለመጀመር እና ለማረፍ አሁንም አልረፈደም።
ኢዮቤልዩ በዋናነት ከንቃተ ህሊና በጣም የራቀ የነቃ የእረፍት ጊዜ ነው። የኢዩቤልዩ ዋና መሰረት የተመሰረተው በዕብራይስጥ ኢዮቤልዩ ላይ ሲሆን፥ ይህም የዕብራይስጥ ኢዮቤልዩ በዘሌዋውያን ምዕራፍ 25፡10 ላይ “አምሳኛውንም ዓመት ትቀድሳላችው፥ በምድሪቱም ለሚኖሩባት ሁሉ ነፃነትን ታውጃላችሁ፤ እርሱ ለእናንተ ኢዩቤልዩ ነው፥ ሰው ሁሉ ወደ ርስቱ እና ወደ ወገኑ ይመለስ” ተብሎ እንደተፃፈው፥ በየሃምሳ ዓመቱ መሬትን ማሳረፍ፣ ንብረትን መመለስ እና ባሪያዎች ነፃ ማውጣትን ይጠይቃል።
የኢዮቤልዩ ሶስት ምልክቶችን የሚያሳዩ ሶስት ተጨባጭ ድርጊቶች መሬት፣ ነፃነት፣ እና ይቅርታ ሲሆኑ፥ እነዚህም በእንክብካቤ ሥነ-ምግባር ውስጥ መሠረታቸውን አድርገዋል። ለዘመናት በጸጥታ ያለፈ የጥበብ ዓይነት፥ ለከፍተኛ ዜናዎች በቀላሉ የሚቀመጥ በጣም አስፈላጊ የሆነ ማህደረ ትውስታ ነው። ነገር ግን ስንረሳው ወደ እኛ የሚመልሰው ቃሉን ብቻ ነው።
ነቢዩ ኢሳይያስ በትንቢቱ ላይ (ኢሳ 61፡1-2) “የጌታ መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች ወንጌልን እሰብክ ዘንድ ቀብቶኛልና፥ ለታሰሩትም መፈታትን፣ ለእውሮችም ማየትን እሰብክ ዘንድ፥ የተጠቁትንም ነፃ አወጣ ዘንድ የተወደደችውን የእግዚያብሔርን ዓመት እሰብክ ዘንድ ልኮኛል” በማለት እነዚህን ጭብጦች የሚያነሳ ሲሆን፥ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ በሉቃስ ወንጌል 4፡18–19 ላይ ይሄንኑ ኢሳይያስ ትንቢት በመፈጸም “የእግዚአብሔር ሞገስ ዓመት” ፍጻሜ መሆኑን በመናገር ከዓለም ጋር እንደታደሰ ቃል ኪዳን አዲስ ኪዳን የመኖር ጥሪን ያሳየናል።
ስለዚህ የኢዮቤልዩ ዓመት የማያቋርጥ የመደጋገም ዝንባሌን እና ግትርነትን እንዲሁም የብቸኝነት ባህሪን በመቃወም የመታደስ ጊዜን ይወክላል።
ምድራችንም መበዝበዟን ቀጥላለች፥ ማግለል ቀጥሏል፥ የውድመት ሁኔታዎች የመቀነስ ምልክት ሳያሳዩ አዳዲስ የብዝበዛ ዓይነቶች ብቅ ይላሉ።
ለዚህ ነው ‘ሻባት’ ወይም ሰንበት የተሰኘው የእረፍት ጊዜ አስተሳሰብ የመጣው፥ ለዚህ ነው ለተወሰነ ጊዜ “የማቆም” ተግባር ከላይ የተጠቀሱትን ዝንባሌዎች ለማቋረጥ አስፈላጊ የሆነው። በኦሪት ሰንበት የፍጥረት ሰባተኛውን ቀን ያስታውሳል፥ እግዚአብሔር ሥራውን ጨርሶ፣ አቁሞ፣ ቀኑን ባረከ፣ ቀደሰው። ቆም ማለት ብቻ ሳይሆን የእግዚአብሔርን ህልውና የምናከብርበት ልዩ የመታደስ ጊዜ ነው። ከዚህም በተጨማሪ ምድሪቱ ሳይታረስ የምትቆይበት እና ድንገተኛ ምርቷ ለድሆች፣ ለእንግዶች እና ለእንስሳት ተጠብቆ የሚቆይበት ‘ሴሚታ’ የተባለውን የሰንበትን ዓመት አገኘ። ከዚህም በዘለለ ለተወሰነ ጊዜ ማቆም ለሌላ አዲስ ነገር የመከፈቻ እና የማስጀመሪያ ዕድልን ይሰጣል።
ለራሳችን ለውጥ ጊዜ ሳንሰጥ እንዴት እራሳችንን እና ዓለምን እንደምንለውጥ ማሰብ እንችላለን? ለመተንፈስ ምንም ቦታ ካልተሰጠ የአስተሳሰብ እና የህይወት ልምዶች እንዴት ሊለወጡ ይችላሉ?
ከዚህ አንፃር ኢዮቤልዩ የዓለምን ሰንበት አስፈላጊነት የሚያነሳሳ ሲሆን፥ ታላቅ የእረፍት እና የእንክብካቤ ጊዜ የሰው ልጅ ከፍጥረት ጋር የታደሰ ቃል ኪዳን ሊኖር እንደሚችል የሚያስታውስ ነው። የአውሮፓዊያኑ የ2025 ዓመት ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንቺስኮስ እ.አ.አ ግንቦት 1 ቀን 2019 ዓ.ም. “የዛሬን ኢኮኖሚ ለመለወጥ እና ለነገው ኢኮኖሚ ህይወትን ለመስጠት ወደ ‘ቃል ኪዳን’ መግባት” አስፈላጊነትን በመናገር በተለይም ለወጣቶች ደጋግመው ያሳሰቡትን የታደሰ ቃል ኪዳን እንዲያደርጉ ያስተጋባል።
መደበኛው ኢዮቤልዩ ታህሳስ 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የቅዱስ በርን በመዝጋት የሚጠናቀቅ ሲሆን፥ ይህም ለቀረው ጊዜ ሀላፊነት እንድንወስድ ጥሪ የሚያደርግልን ተምሳሌታዊ የጊዜ ገደብ ነው።
ቀነ ገደብ ቢኖርም ግን ደግሞ ለዚህ ሁሉ ጊዜ እንዳለ ለመገንዘብ የሚረዳን ግብዣ ነው።
ለምድር የሚሆን ጊዜ
የነፃነት ጊዜ
የይቅርታ ጊዜ
እናም እስካሁን እነዚህን ካላደረጉ፡-
ለአፍታ ቆም ይበሉ
ይተንፍሱ
እረፍት ያድርጉ