ፈልግ

59ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ- የማህደር ምስል 59ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ- የማህደር ምስል  

59ኛው የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ መደበኛ ጉባኤ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ካቶሊክ ጳጳሳት ጉባኤ 59ኛ መደበኛ ጉባኤያቸውን በእምድብር ሀገረ ስብከት ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ህዳር 29 ቀን 2018 ዓ.ም. ጀምረዋል።

ጉባኤው የ12 ሀገረስብከት ብፁዓን ጳጳሳት በተገኙበት በብፁዕ ሊቀጳጳስ ብሪያን የቅድስት መንበር ተወካይ በተገኙበት የተጀመረ ሲሆን፥ በጉባኤው ብፁዕ አቡነ ተስፋስላሴ የአዲግራት ሀገረስብከት ጳጳስ በወቅታዊ ሁኔታዎች ምክንያት አለመገኘታቸው ተገልጿል።

ጉባኤው በአጀንዳው በመንፈስ ቅዱስ መሪነት በርካታ ጉዳዮችን እንደሚዳስስ የተገለጸ ሲሆን፥ በተለይም የሲኖዶስን የመጨረሻ ሰነድ በተግባር ላይ ለማዋል የሚያስችሉ አቅጣዎችን እንደሚያስቀምጥ የጉባኤው የህዝብ ግንኙነት ተወካይ ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ገልጸዋል።

ጉባኤው የርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛን መልዕክት በማዳመጥ የተጀመረ ሲሆን፥ ይህም ጉባኤው ከቅድስት መንበር ጋር ያለውን ህብረት የሚያመላክት ነው ተብሏል።

ጉባኤው በቀጣይ ቀናት ቀጥሎ እስከ ታህሳስ 2 ቀን የሚቆይ ሲሆን መላው ካቶሊካውያን እና በጎ ፍቃድ ያላቸው ሁሉ በጸሎት እንዲተባበሩ ጥሪ ቀርቧል።

09 Dec 2025, 06:36