ፈልግ

በሰሜናዊ ዌስት ባንክ በምትገኘው ታይቤህ መንደር  የደረሰው የሰፋሪዎች ጥቃት በሰሜናዊ ዌስት ባንክ በምትገኘው ታይቤህ መንደር የደረሰው የሰፋሪዎች ጥቃት 

ክርስቲያኖች በታይቤህ መንደር አዲስ የሰፋሪዎች ጥቃት ቢሰነዘርባቸውም ተስፋ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል

በሰሜናዊ ዌስት ባንክ ውስጥ በምትገኘው እና የክርስቲያኖች መንደር በሆነችው ታይቤህ ውስጥ ህዳር 25 እና 26 ሌሊት ላይ በእስራኤላዊያን ሰፋሪዎች ሁለት መኪኖች መቃጠላቸው እና አንድ ህንፃ የማስፈራሪያ ይዘት ባላቸው በቀለም የተፃፉ መልዕክቶች መበላሸቱ የተነገረ ሲሆን፥ ይህ ክስተት የተፈጠረው በአከባቢው የሚገኘው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን ቁምስና “የገና ምሽቶች” የተሰኙ ክብረ በዓላትን ካስጀመረ ከሰዓታት በኋላ መሆኑ ተነግሯል።

  አቅራቢ ዘላለም ኃይሉ ፥ አዲስ አበባ

በእስራኤል ሰፋሪዎች የተፈፀመው ይህ ጥቃት በንብረት ላይ ጉዳት ቢያደርስም በሰው ህይወት ላይ ምንም ጉዳት እንዳላደረሰ የተነገረ ሲሆን፥ የላቲን ሥርዓተ አምልኮ የምትከተል የታይቤህ ቤተ ክርስቲያን ካህን የሆኑት አባ ባሻር ፋዋድሌህ ችግሩ ከደረሰ በኋላ ብዙም ሳይቆይ ጉዳቱ የደረሰበትን ቤተሰብ መጎብኘታቸውን ገልጸው፥ እዛ በመገኘታቸው እንዳመሰገኗቸው እና በአከባቢው የቤተክርስቲያን መገኘት ትልቅ ክብር እንዳላቸው መግለፃቸውን አስረድተዋል።

ካህኑ አክለውም ህዝባቸውን እና መሬታቸውን ለመጠበቅ ጠንካራ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጸው፥ ታይቤህ በአካባቢው የመጨረሻው የክርስቲያን መንደር መሆኗን ጠቅሰው፥ ለዚህች መንደር ህልውና ዓለም አቀፍ ትብብር እንደሚያስፈልጋቸው አሳስበዋል።

ከክብረ በዓል እስከ ጥቃት
ጥቃቱ የደረሰው ከቅድስት ሀገር ጋር ታሪካዊ ግንኙነት ካላቸው ስምንት ሀገራት የተውጣጡ ዲፕሎማቶች እንዲሁም ራማላህ፣ እየሩሳሌምን እና በአቅራቢያው የሚገኙ ከተሞችን ሲጎበኙ የነበሩ ሰዎች በተገኙበት የደብሩ የገና ዝግጅቶች በተከፈቱበት ማግስት ሲሆን፥ ከእኩለ ሌሊት በኋላ ሰፋሪዎቹ የነዋሪዎቹን ንብረት በማውደም እና በግል ቤቶች ላይ ያልተገቡ ጽሁፎችን መፃፋቸው የገለጹት አባ ፋዋድልህ፥ ‘እነዚህ ያልተገቡ ጽሁፎች በዌስት ባንክ ውስጥ ከተደረጉት ጋር ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው’ መልዕክቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ምንም እንኳን በዚህ ዓመት ብቻ ስድስት ተደጋጋሚ ድርጊቶች መፈጸማቸውን ያስታወሱት የሰበካው ካህን፥ ምንም እንኳን ደህንነት ባይሰማቸውም እዚያው እንደሚቆዩ እና የዕለት ተዕለት ሕይወታችን እንደሚቀጥሉ ገልጸው፥ “የገናን በዓል ማክበራችንን እንቀጥላለን” ብለዋል።

በፍርሃት ውስጥ ተስፋ ማድረግ
እያንዳንዱ አዲስ ጥቃት ጭንቀትን እንደሚጨምር እና አንዳንዶች አከባቢውን ለቀው ለመውጣት እንዲያስቡ እንደሚያነሳሳቸው ካህኑ የጠቆሙ ሲሆን፥ ዓለም አቀፍ ትኩረት እና ዲፕሎማሲያዊ ተሳትፎ ከራማላ በስተምሥራቅ የሚገኙ ተጋላጭ ማህበረሰቦችን ሊደግፍ እንደሚችል ያላቸውን ተስፋ ገልጸው፥ “ተስፋችን አይደበዝዝም፥ ተስፋችን በሦስተኛው ቀን ባዶ ስለሆነው መቃብር፣ የትንሣኤ ተስፋ ነው” ብለዋል።

ከጥር ወር ጀምሮ 1,680 ጥቃቶች መፈጸማቸው
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (OCHA) በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት መሰረት ጥቅምት እና ህዳር ወር ላይ በ88 አከባቢዎች የተፈጸሙ 178 ክስተቶችን ጨምሮ ከዓመቱ መጀመሪያ ጀምሮ 1,680 የሰፋሪዎች ጥቃቶች (በአማካይ በቀን አምስት ጊዜ) ከ270 በሚበልጡ ፍልስጤማዊያን ማህበረሰቦች ላይ መድረሳቸውን እና በተለይም የወይራ ምርት ላይ ትልቅ ጉዳት መድረሱን ይፋ አድርጓል።

08 Dec 2025, 14:14