ፈልግ

የእስያ ቤተክርስቲያን መሪዎች የሰው ሰራሽ አስተውልኾት በምያሳድረው ተጽኖ ላይ ለመናጋገር ተሰበሰቡ! የእስያ ቤተክርስቲያን መሪዎች የሰው ሰራሽ አስተውልኾት በምያሳድረው ተጽኖ ላይ ለመናጋገር ተሰበሰቡ! 

የእስያ ቤተክርስቲያን መሪዎች የሰው ሰራሽ አስተውልኾት በምያሳድረው ተጽኖ ላይ ለመናጋገር ተሰበሰቡ!

በእስያ ጳጳሳት ፌዴሬሽን ኮንፈረንስ የተዘጋጀው በሆንግ ኮንግ የ3 ቀናት ስብሰባ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (ሰው ሰራሽ አስተውልኾት) እና ለሰው ልጅ ነፃነት ጥበቃ ሲባል ትምህርትን እና የሚዲያ እውቀትን ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ መሆኑን በማንሳት ስብሰባ እየተካሄደ እንደሚገኝ ተገልጿል።

የዚህ ዝግጅት አቅራቢ መብራቱ ኃ/ጊዮርጊስ-ቫቲካን

የእስያ ጳጳሳት፣ የኮሙዩኒኬሽን መሪዎች እና የሚዲያ ባለሙያዎች በሆንግ ኮንግ በምያካሂዱት ስብሰባ ጳጳሳት እ.አ.አ 2025ን በኃላፊነት መንፈስ እንዲሸኙ ጥሪ በማቅረብ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱን ጀምረዋል።

በሰብአዊ ክብር፣ በሥነ ምግባር ግንዛቤ እና በቤተክርስቲያኒቱ ተልዕኮ ላይ የቴክኖሎጂ እድገቶችን መሰረት በማድረግ (እ.አ.አ ታህሳስ 10-12/2025) የተዘጋጀው የሶስት ቀናት ስብሰባ በቅዱስ ፍራንችስኮስ ዩኒቨርሲቲ እየተካሄደ ሲሆን ከመላው አህጉሪቱ የተውጣጡ ከ30 በላይ ተሳታፊዎችን አሰባስቧል።

ካርዲናል ቾው፡ ለጋራ ጥቅም እንደ ስጦታ

የስብሰባው መክፈቻ መስዋዕተ ቅዳሴ የመሩት የኢየሱሳዊያን ማሕበር አባል የሆኑት የሆንግ ኮንግ ጳጳስ ካርዲናል እስጢፋኖስ ቾው፣ የእስያ የኮሙኒኬሽን ባለሙያዎች AIን (ሰው ሰራሽ አብርኾት) እንደ “የእግዚአብሔር ስጦታ” እንዲመለከቱት ጋብዛቸዋል፤ አጠቃቀሙም ለሰው ልጅ ጥቅም እና ለፍጥረት እንክብካቤ ማድረግ ላይ ያተኮረ መሆን አለበት ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

“AI ከዲያብሎስ የመጣ እንዳልሆነ አስባለሁ። AI የሚመጣው ከእግዚአብሔር ነው” ሲሉ በስብከታቸው ወቅት ተናግረዋል። “ይህ ስብሰባ እንዲረዳን፣ ነፃ እንዲያወጣን እና እግዚአብሔር ለእኛ የሚፈልገውን በረከት ለማሳካት ከAI ጋር እንድንሰራ እንዲያነሳሳን እጸልያለሁ” ሲሉ ተናግረዋል።

ካርዲናሉ ተሳታፊዎች የቴክኖሎጂ እድገቶችን በተስፋ፣ በጥንቃቄ በማስተዋል እና በሥነ ምግባር ግልጽነት እንዲቀርቡ አበረታተዋል። የካቶሊክ ሚዲያዎች ፈጣን ለውጥ በሚመጣበት ጊዜም ቢሆን የሞራል ተዓማኒነትን መጠበቅ አለባቸው ሲሉ አጽኖት ሰጥተው ተናግረዋል።

“ያለበለዚያ፣ እራሳችንን ካቶሊክ ሚዲያ ብለን እንዴት እንጠራለን?” ሲሉ ጠይቀዋል። “ተስፋችንን በጌታ ላይ ስናደርግ፣ በመጀመሪያ እሱን ማክበር አለብን፣ የገንዘብ ድጋፍ ሰጪ ወኪሎችን ወይም ርዕዮተ ዓለሞችን አይደለም። በዚህ ተለዋዋጭ አውድ ውስጥ የእግዚአብሔርን ለተልእኳችን ያለውን ፈቃድ ማስተዋል አለብን” ሲሉ አክለው ገልጸዋል።

ካርዲናል ቾው ለህሊና ታማኝነት አስፈላጊ መሆኑን አፅንዖት ሰጥተው የተናገሩ ሲሆን “ከህሊናዬ በተናገርኩ ቁጥር፣ ጥቃት ቢሰነዘርብኝም እንኳን፣ አሁንም ሰላም አገኛለሁ” ብለዋል፥ በሲኖዶስ ሂደቶች በተቀረጸ የግል እና የማህበረሰብ ህሊና በመናገር፣ ነፃነትን እና ትክክለኛነትን ያመጣል ብለዋል።

ካርዲናሉ የኢየሱስን ቃላት በመጥቀስ “ቀንበሬ ልዝብ፥ ሸክሜም ቀላል ነው” (ማቴ 11፡30) ሲሉ ላስተባባሪዎቹ የተናገሩት ካርድናል ቾው “በልባችን ስንነጋገር በመንፈስ ስንመራ ቀላልነትን ያገኛሉ” ሲሉ ደምድመዋል።

ዶክተር ሩፊኒ፡ በAI ዘመን ሙሉ በሙሉ ሰው ሆኖ መቀጠል

እ.አ.አ ታህሳስ 10/2025 ዓ.ም ለስብሰባው ተካፋዮች ባደረጉት ንግግር፣ የቫቲካን የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ዋና ጸኃፊ የሆኑት ዶ/ር ፓውሎ ሩፊኒ በበኩላቸው ሲናገሩ ለቤተክርስቲያን እና ለኅብረተሰቡ የAI (የሰው ሰራሽ አስተውልኾት) ተስፋ እና አደጋዎች ሰፊ ነጸብራቅ አቅርበዋል።

ጥልቅ ውሸቶች፣ የማይረጋገጡ ምንጮች፣ የአልጎሪዝም (ስልተ ቀመር) ማጣሪያ እና ዲጂታል መድረኮች የመረጃ ፍሰቶችን የሚቀርጹበት ግልጽ ያልሆነ አመክንዮ እንዳይኖር አስጠንቅቀዋል። እነዚህ ተለዋዋጭ ሁኔታዎች ተጠቃሚዎችን ከእውነት ይልቅ በንግድ ወይም ርዕዮተ ዓለም ፍላጎቶች በሚመሩ “የማጣሪያ አረፋዎች” ውስጥ ሊከቱ እንደሚችሉ ተናግረዋል። በእንግልዜኛው "filter bubbles" ('የማጣሪያ አረፋዎች' ማለት የማህበራዊ ሚዲያ እና የፍለጋ ፕሮግራም ስልተ ቀመሮች በፍላጎታችን እና በቀድሞ የኢንተርኔት መስመር ባህሪያችን ላይ በመመስረት የምናየውን የድረ ገጽ ይዘት ለግል ጥቅም ሲያበጁ የሚፈጠሩት አእምሯዊ እና መረጃዊ ማግለያዎች ናቸው። ይህ ሂደት ለእያንዳንዱ ተጠቃሚ የተበጀ የመስመር ላይ ተሞክሮ ይፈጥራል፣ ነገር ግን ለተለያዩ አመለካከቶች መጋለጥን ይገድባል)።

ዶክተር ሩፊኒ ዋና ዋና የAI ሞዴሎች ብዙውን ጊዜ ፍጥነትን እና ትኩረትን ከጥልቅ እና ትክክለኛነት ይልቅ ቅድሚያ እንደሚሰጡ በመግለጽ የአስተሳሰብ ነፃነትን አደጋ ላይ እንደሚጥሉ እና የህዝብ ንግግርን እንደሚያዛቡ ተናግረዋል።

ከቀድሞ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ፍራንችስኮስ እና ከርዕሰ ሊቀ ጳጳሳት ሊዮ 14ኛ መልዕክቶችን በማስተጋባት፣ ትምህርትን እና የሚዲያ እውቀትን ለሰው ልጅ ነፃነት እንደ መከላከያ መሣሪያ ሆነው ሊያገለግሉ እንድሚችሉ  አፅንዖት ሰጥተው ተናግረዋል። "የሰው ልብ ራሱ" አርቲፊሻል (ሰው ሰራሽ) እንዳይሆን ለመከላከል ወሳኝ አስተሳሰብ፣ ማስተዋል እና መረጃን የመገምገም ችሎታ አስፈላጊ ናቸው ብለዋል።

"አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በፍፁም ሊተካን አይገባም" ሲሉ የተናገሩት ዶክተር ሩፊኒ ቤተክርስቲያን አማኞች አስተሳሰብን፣ ትውስታን እና ባህሪን ሊቀርጽ በሚችል ዲጂታል ዘመን ውስጥ ሙሉ በሙሉ ሰው ሆነው እንዲቀጥሉ መርዳት አለባት ብለዋል።

ሮማኖ ጋርዲኒ በመጥቀስ፣ ከቴክኖሎጂ ኃይል ጋር ተመጣጣኝ የሆነ አዲስ አመለካከት እንዲኖራቸው ጥሪ አቅርበዋል - በህሊና፣ በኃላፊነት እና በእውነት ላይ የተመሠረተ ሲሉ አሳስበዋል።

"የማሰብ ችሎታ አርቲፊሻል ሊሆን አይችልም"

በዶክተር ሩፊኒ ስለ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ስለ ቤተክርስቲያን በሰፊው ከተደርገው ገለጻ እና ማብራሪያ በተለምዶ "አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ" ተብሎ የሚጠራው የስሌት ዓይነት ሆኖ እንደሚቀጥል አጥብቀው ተናግረዋል - ኃይለኛ ግን ውስን ሲሉም አክለው ገልጸዋል።

"እውነተኛ ጥበብ ከማሽኖች እና ስልተ ቀመሮች ሊመጣ አይችልም" ብለዋል። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ሙሉ እውቀትን ሊያቀርብ እንደሚችል በማመን "እንደ እግዚአብሔር የመሆን ፈተና" እንደገና የመድገም አደጋ እንዳለው አስጠንቅቀዋል።

የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እውነተኛ አደጋዎች የሚመነጩት ከሰው ልጅ ውሳኔዎች ነው፡ "ከባለቤቶቻቸው፣ ከፕሮግራማቸው እና ከሚጠቀሙባቸው ነገሮች"። ቴክኖሎጂ አደጋ ሳይሆን እድል እንዲሆን ለማረጋገጥ የስነምግባር ቁጥጥር አስፈላጊ መሆኑን አክለው ገልጸዋል።

ዶክተር ሩፊኒ እውነተኛ የሰው ልጅ መገናኘት አስፈላጊ መሆኑንም አንፀባርቀዋል። በ AI የተፈጠሩ ጽሑፎች፣ ምስሎች ወይም ሙዚቃዎች ኃላፊነት በተሞላበት መንገድ ጥቅም ላይ ካልዋሉ የሰው ልጅ የፈጠራ ችሎታን የግንኙነት ዋጋ ሊቀንሱ እንደሚችሉ ተናግረዋል። ተሳታፊዎች ለማሰላሰል፣ ለመነጋገር እና ለእውነተኛ ግንኙነቶች ጊዜ እንዲሰጡ አበረታተዋል።

ተወካዮች እና ስብሰባዎቻቸው

ሰባት ጳጳሳት እና ከ15 በላይ ካህናት በስብሰባው ላይ እየተሳተፉ ሲሆን በዲጂታል ሚዲያ፣ በእውነታ ማረጋገጫ እና በ AI ልማት እውቀት ካላቸው ምዕመናን ባለሙያዎች ጋር እየተሰበሰቡ ይገኛሉ። ቅድስት መንበር ከቫቲካን የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የተወከሉ በሁለት ከፍተኛ ባለስልጣናት ተወክላለች።

የስብሰባው ክፈለጊዜው “AI እና በሰው ልጅ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ”፤ “AI እና ቤተክርስቲያን”፤ “AI ለካቶሊክ ሚዲያ ያበረከተው አስተዋጽኦ”፤ “የቅዱሳት መጻሕፍት እና የቤተክርስቲያን ሰነዶች የትርጉም ፍለጋ መሳሪያ”፣ “አዲስ የኦንላይን ማረጋገጫ አጠቃቀም”፣ “በወንጌል ስርጭት ውስጥ AI ዘዴዎችን በመጠቀም” የተሰኙ የመወያያ አርእስቶች መካተታቸው ተገልጿል።

እነዚህ ውይይቶች በእስያ የምትገኘው ቤተክርስቲያን የዲጂታል ለውጥን የሐውርያዊ አገልግሎት አንድምታዎች እንድትገመግም ለመርዳት ያለመ ሲሆን በክርስቲያን ግንኙነት እምብርት ላይ ያለውን የግንኙነት ታማኝነትም እንድትጠብቅ ለመርዳት ያለመ ነው።

AI በእስያ ወንጌል ስርጭት

ለሬዲዮ ቬሪታስ እስያ በሰጡት አስተያየት፣ የኢሲያ ጳጳሳት ጉባኤ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሥራ አስፈፃሚ ጸሐፊ እና የRVA የፕሮግራም ዳይሬክተር የሆኑት አባ ጆን ሚ ሼን፣ AI የቤተክርስቲያኒቱን ባለብዙ ቋንቋ ተልእኮ በትርጉም፣ በጽሑፍ እና በይዘት አደረጃጀት የሚደግፍ መሣሪያ እንደሆነ ገልጸዋል።

“AI የሥራ ማቀላጠፊያ መሣሪያ ብቻ ነው። እውነተኛ የመገናኛ ሥፍራ ልብ የሰው ልጅ ሆኖ ይቀራል” ብለዋል። “ግንኙነቶች፣ ማስተዋል እና ትክክለኛነት በሥራ ማቀላተፊያ መሣርያዎች ሊሠሩ አይችሉም” ብለዋል።

በሆንግ ኮንግ በተደርገው ስብሰባ የተነሱት ጭብጦች ባለፈው ወር በፔንጋንግ በተካሄደው የታላቁ የተስፋ መንፈሳዊ ጉዞ ላይ የተነሱትን ነጸብራቆች ያስተጋባሉ፣ የመገናኛ ባለሙያው ኒኮላስ ሊም ሀገረ ስብከቶች አስተማማኝ የካቶሊክ የእውቀት መሠረቶችን እንዲገነቡ ያበረታቱበት እና የAI ውስንነቶችን ያስጠነቀቁበት፣ ይህም ርህራሄ እና መንፈሳዊ ጥልቀት አለመኖርን ጨምሮ ከእነዚህ ጉዳዮች መጠንቀቅ እንደሚገባ ተናግረዋል።

እስያ የሐዋርያዊ እንክብካቤ መተዳደሪያ ደንብ መመሪያዎች

እ.አ.አ ታህሳስ 12/2025 ጳጳሳቱ ብሔራዊ ሪፖርቶችን ለመገምገም እና በእስያ ውስጥ ለሚገኙ የሐዋርያዊ እንክብካቤዎች የሚውል መመሪያ ረቂቅ ላይ ለመተባበር ይሰበሰባሉ፣ ይህም ሀገረ ስብከቶች ለሚመጡ የቴክኖሎጂ ተግዳሮቶች ምላሽ እንዲሰጡ ለመርዳት የታሰበ ነው።

ጉባኤው የሚጠናቀቀው የኢስያ አህጉር የጳጳሳት ጉባኤ የኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት ሊቀመንበር በሆኑት በጳጳስ ማርሴሊኖ አንቶኒዮ ማራሊት በሚመራው የቅዳሴ ሥነ ሥርዓት ሲሆን በዚህ ጊዜ የመጨረሻ መግለጫዎችና ቃል ኪዳኖች ይቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

 

11 Dec 2025, 15:41